Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
DefendTheTruth
Member+
Posts: 9918
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: Rounding up Amhara daily laborers in and around Addis Ababa: The final solution by the Abiy Administration?

Post by DefendTheTruth » 07 May 2022, 07:41

Educator wrote:
06 May 2022, 15:18
Please wait, video is loading...
DefendTheTruth wrote:
06 May 2022, 14:02
ምን አይነት ትርድ ነዉ ይሄኛዉ ደግሞ?

መላቅጡ የጠፋበት፣ አራምባ ና ቆቦ። አንድ የምያደርጋቸዉ ነገር ብኖር አብይ አህመድ ላይ መዉረድ ብቻ ነዉ።

What has Abiy Ahmed not been yet?

Abiy Ahmed this Abiy Ahmed that, Abiy Ahmed here, Abiy Ahmed there, everywhere and for everything: it seems people are literally worshipping him.


ጌታቺን Abiy Ahmed እባኪህ ማረን፣ እግዚዮ ብለናል እባኪህ ማረን።

ሃይማኖታቺዉ አብያንቶች ይባላል።
TN,

Church doctrine and enlightenment have never gone hand in hand in the whole of their long long histroy. When one hand took the upper hand, the other went straight to the bottom and vice-versa. That is why dark age was replaced (if not curshed to the ground) with the era of enlightenment, following which the actors of dark age were forced to taking a backseat.

The Abune seems just resorted to making a political statement to vent his frustration in this regard, after being confined to the backseat ever since the era of enlightenment has took off and flying high until now.


Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4080
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: Rounding up Amhara daily laborers in and around Addis Ababa: The final solution by the Abiy Administration?

Post by Za-Ilmaknun » 08 May 2022, 10:56

የኔ አማራ ይሄንን ይመስላል!!
አሳዬ ደርቤ
▬▬▬▬
አማራዬ ላንተ ጊዜዬን እና ሐሳቤን ቀርቶ ሕይወቴን ለመስጠት የማልሳሳው ለዚህች ‹‹መናኛ አገር›› ወርቅ አበድረህ እብቅ ስትቀበል ስለማይ እንጂ ካንተ የተፈጠርኩ የአማራ ተወላጅ ስለሆንኩ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ያህል፡-

ባንድ ወቅት ባንተ እገዛ ስልጣን የያዙ ኃይሎች ወልቃይትን እና ራያን ቀሙህ፡፡ አንተ ግን በዜግነትህ እንጂ በማንነትህ ማሰብ የማትወድ ሰፊ ሕዝብ በመሆንህ ‹‹ከኢትዮጵያ ወደ ኢትዮጵያ›› በተወሰደው የራያ እና ወልቃይት መሬት በላይ ለብስጭት የዳረገህ ኢትዮጵያ ያለ ባሕር በር መቅረቷ ነበር፡፡

ከዓመታት ባንዱ ዓመትም መሬትህን እና ማንነትህን የቀሙህ ኃይሎች ‹‹መሬታችን ተወረረ›› ብለው እንደ አሸን የምትረግፍበትን ጦር ሜዳ ባድሜ ላይ አዘጋጁልህ፡፡ አንተም የእርዳታ ስንዴ ጭኖ በመጣ ኤነትሪ ተጭነህ ‹‹እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም›› እያልክ ባድሜ ላይ በመገኘት በአጥንትህ እርከን እስኪሠራ ድረስ ሕይወትህን ገበርክላት፡፡ ኢትዮጵያ ተበታትነህ የምትኖርባት አገርህ ብቻ ሳትሆን ተሰባስበህ የምትሞትላት መቃብርህ መሆኗን ገለጽክላት፡፡

ከዚያስ ምን አተረፍክ?
➔በኦሮሞ ዘንድ የተጠላህ ትሆን ዘንድ የአኖሌን ሃውልት ተክለው ጠበቁህ፡፡
➔‹‹ጨፍላቂ፣ አሀዳዊ፣ ትምክህተኛ፣›› በሚል ማለቂያ አልባ ፍረጃ የብሔር ብሔረሰቦች ማስፈራሪያ ጭራቅ አደረጉህ፡፡
➔ሰፋሪ›› በሚል ቃል አገርህን ቀምተው ብሔርህን አስታወሱህ፡፡
➔ዜግነትህን ለመግፈፍ ሲጥሩ ያለህን ብቻ ሳይሆን የነጠቁህን ማንነት አስታወሱህ፡፡

‹‹አማራን እንዳይነሳ አድርጌ ቀብሬዋለሁ›› ሲል የኖረው ሥርዓትም ስለ ወልቃይት ስታወራ የሰማ ቀን ቅስምህን የሚሰብር ሠራዊት ወደ ጎንደር አዘመተ፡፡
በኮሎኔል ደመቀ ጥይትም ደርዘኑን ሠራዊት ከምድር ላይ አጋድመህ በጥልቅ ሲታደስ የከረመው ሥርዓት መበስበሱን ይፋ አደረግክ፡፡ ‹‹የኦሮሞ ደም የኔ ደም ነው›› በሚል አቋምም ጥላቻን በፍቅር ድል ካደረግክ በኋላ በኦሮማራ ጥምረት አሮጌውን ሥርዓት አሽቀንጥረህ፣ ለለውጡ መሪ ድጋፍህን ችረህ ወደ ጎጆህ ተመለስክ፡፡

ከዚያስ ምን ሲደረግ አየህ?
➔የቲም መሪ የነበሩት ፕሬዝዳንት ስለ ዲሞግራፊ ሲያወሩ፣ እሳቸውን የተኩት ፕሬዝዳንት መስቀል አደባባይ ላይ ቆመው የአጼውን ሥርዓት እንደ እንጨት ሲሰባብሩ፣

➔አንተን ባዕድ ሌላውን ዘመድ በሚያደርግ ንግግር 'የቡራዩና የሱልልታ ሰዎች መሪያችን ተነካ' ብለው ወደ አራት ኪሎ ሲያመሩ፣ ኦሮማራን ሲመሩ የነበሩ አክቲቪስቶች ህውሓት ስትራቴጂክ አጋራችን ናት እያሉ ሲያወሩ…

➔ወገኖችህን መጤ ተብለው በጅምላ ሲቀበሩ፣ የትግል መሪያችን ተከበበ ብለው የተቆጡ ኃይሎች ከማታውቀው ቤተ-መንግሥት አስገብተው ‹‹ዳውን ዳውን አማራ›› እያሉ ሲፎክሩ፣

በሌላ መልኩ ደግሞ ከፌደራል ከተባረረ ጊዜ ጀምሮ ‹‹አንተን በጠላትነት በሚፈርጅና የኤርትራ ሕዝብ ወንድም ሕዝብ መሆኑን በሚያውጅ መግለጫው ሲያወግዝህ የከረመው ኃይል ሰሜን እዝን መውጋቱን በጠቅላይ ሚኒስትሩ አንደበት ሲተረክ ሰማህ፡፡ ያን ጊዜም ስትገድልህ ለከረመች አገርህ ሟች ሆነህ ተገኘህ፡፡ ለሠራዊቱ ስንቅ ከማቅረብ ባለፈ በእራስህ ትጥቅ ዘምተህ በአንተ ሕልፈት የአገርን ቀጣይነት እውን አደረግክ፡፡

ከዚያስ ምን አጋጠመህ…?
➔የወለጋ እልቂት፣ የአጣዬ ጥቃት
➔ሽልማት የሚገባው ልዩ ሃይልህ በብልጽግና አመራሮች ሤራ ተገድሎ ከሚሴ ላይ አስከሬኑ ሲገተት
➔ሕይወትህን የሰጠኸው መንግሥት ጠላትህን ከባድ መሣሪያ አስታጥቆ ‹‹አፈግፍግ›› በሚል ትዕዛዝ ጦርነቱን ወደ አንተ ምድር ሲገትት…

ያን ጊዜም ወገንህን ተጣርተህ ብቻህን መሆንህን ተረዳህ፡፡
ያን ጊዜም የአገርህን ሠራዊት ስትጠብቅ ጦርነት ስቦ የጣለብህ መንግሥት ‹‹በዚህ ዘመን የመስኖ መሳቢያ ጄኔሬተር እንጂ ሚኒሽር ተሸክሞ መዞር አይጠቅምም›› እያለ ሲሳለቅብህ ዐየህ፡፡
ያን ጊዜም ታናናሽ ልጆህን መከላከያ ሠራዊቱን እንዲቀላቀሉ መቀስቀሱን ትተህ ‹‹ፋኖ ሁኑ›› ማለት ጀመርክ፡፡

ከዚያስ ምን ተከሰተ?
➔‹‹ጽንፈኛ አማራን እናከስማለን›› የሚል ዛቻ
➔‹‹ፋኖ የሚባል ኢመደበኛ ኃይል ትጥቅ መፍታት አለበት›› የሚል ዘመቻ
➔አንተን ያላካተተ ድርድርና ሚስጢራዊ ውይይት
➔ሃይማኖትን መሠረት አድርጎ አንድነትህን የሚከፋፍል ጥቃት
➔አንድ ከተማ ላይ በተፈጸመ ድርጊት እንደ ሕዝብ አንተን እና ፋኖን የሚያንቋሽሽ አገራዊ ውግዘት፤

እናስ ብአዴን ሆኜ ካልተፈጠርኩ በቀር የሌላ ብሔር ተወላጅ ብሆን እንኳን በዚህ ሁሉ ጥቃትህ አለመታመም እንዴት ይቻለኛል?

Share

Post Reply