Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Revelations
Senior Member+
Posts: 33729
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

"የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሄጄ ብጠይቅም የለም ብለውኛል"

Post by Revelations » 05 May 2022, 02:35

‹‹የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሄጄ ብጠይቅም የለም ብለውኛል››፦ የጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ጠበቃ




ዕረቡ ሚያዚያ 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከመኖርያ ቤቱ ባሳለፍነዉ እሁድ በመንግስት አካላት ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ቢወሰድም እስካሁን ያለበትን ለማወወቅ አለመቻላቸውን ጠበቃው አዲሱ አልጋው ገለፁ፡፡

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ሚያዝያ 23/2014 ጠዋት 4 ሰዓት ላይ በአዲሰ አበባ ከተማ አሰተዳደር ሀያት ባቡር ጣቢያ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች መወሰዱንና የት እንዳለ ማወቅ እንዳልተቻለ ጠበቃዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የራዲዮ ጣቢያ ተናግረዋል፡፡

ስምንት የሚሆኑ ሲቪል የለበሱ የመንግስት አካላት ነን ብለው የመጡ ሰዎች ለጥያቄ ነው የምንፈልገው ብለው መወስዳቸውን አስታውሰው፣ የት እንደታሰረ ባላውቅም ምናልባት ፍ/ቤት ሊያቀርቡት ይችላሉ በሚል ተሰፋ ትላንት ሚያዚያ 25/2014 ጠዋት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርቦ ከሆነ በሚል ለማጣራት ከ3 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ድረስ ቆይቼ ነበር ብለዋል ጠበቃዉ፡፡

‹‹ነገር ግን አንድም መርማሪ ፖሊስ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን በችሎቱ አላቀረበውም›› ሲሉ የጋዜጠኛው ጠበቃ የሆኑት አዲሱ አልጋው ለራዲዮ ጣቢያው ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ይህ አልሆን ሲል ‹‹የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሄጄ ብጠይቅም የለም ብለውኛል›› ሲሉም ገልፀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሥራ ባልደረቦቹ ወደ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ቅሬታ ለማቅረብ መሄዳቸውን አስታውስው፤ ያንን ተከትሎም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሸን ጉዳዩን አጣርቶ መግለጫ አውጥቷል ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ በበኩሉ ጋዜጠኛው ያለበትን ሁኔታ እና የታሰረበትን ቦታ ለማወቅ ጥረት ያደረገ ቢሆንም፣ መረጃ ማግኘት ባለመቻሉ የጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ጉዳይ እንዳሳሰበው መግለፁ ይታወሳል፡፡

መንግስትም ጉዳዩን በአፅኖት ተመልክቶ ምላሽ እንዲሰጥበት ማሳሰቡን በማንሳት መንግስትም በፍጥነት ምላሽ ይሰጥበታል ብለው እንደሚምኑ አንስተዋል፡፡

የጋዜጠኛው ጠበቃ አክለውም እነዚህ አማራጮችን ተጠቅመው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ ካልታወቀ፣ ወደ ፍትሕ ሚኒስቴር መሄዳቸው እንደማይቀርም ገልፀዋል፡፡




Revelations
Senior Member+
Posts: 33729
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: "የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሄጄ ብጠይቅም የለም ብለውኛል"

Post by Revelations » 05 May 2022, 13:31

Please wait, video is loading...






Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: "የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሄጄ ብጠይቅም የለም ብለውኛል"

Post by Ethoash » 07 May 2022, 13:19

ምን አይነት ስም ነው ጎሜኔ ሲሳይ
እና የጠበቃው ስም ይባስ አዲሱ አልጋዬ

ሁለቱንም ወደ ጦር ሜዳ ነበር መላክ በስመ ጡፉነት ብቻ

Revelations are speaking to yourself I feel sorry and I reply I hope this might help with your condition

Abere
Senior Member
Posts: 11101
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: "የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሄጄ ብጠይቅም የለም ብለውኛል"

Post by Abere » 07 May 2022, 13:57

አፋኖች ጎበዜን (Man of courage) አርሱን እንጅ የሀሳቡን ርትዕነት እና ራዕዩን ማፈን አልቻሉም - አይችሉም። አንተን ግን ከድቅድቅ ጥላቻ እና የድንቁርና እስርቤት ማን ያስፈታሃል?

አንድ ምክር ብቻ አለኝ - ከፕሮፌሰር ሀረገወይን 101 Introduction to civility የሰዋዊነት ትምህርት እንድትወስድ ምኞቴ ነው። You are an untamed soul to live up to the standard of being human of any human society. You should be taken out of the harmful culture of Woyane and be rinsed off. An individual is the product of his culture. Unfortunately, you are the product of the wrongful ones, it is not your fault it is defect of the culture that made you who you are – a bad soul.

Ethoash wrote:
07 May 2022, 13:19
ምን አይነት ስም ነው ጎሜኔ ሲሳይ
እና የጠበቃው ስም ይባስ አዲሱ አልጋዬ

ሁለቱንም ወደ ጦር ሜዳ ነበር መላክ በስመ ጡፉነት ብቻ

Revelations are speaking to yourself I feel sorry and I reply I hope this might help with your condition

Right
Member
Posts: 2820
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: "የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሄጄ ብጠይቅም የለም ብለውኛል"

Post by Right » 07 May 2022, 18:50

Addisu Alegaye and Gobeze Sisay
Good old traditional Amharic names.

If you don’t like it then too bad.
You better waste your time on something else.

Post Reply