Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ጎንደር ላይ ልቅሶ አንጂ የዒድ በዓል እንዲኖር አልተፈቀደም! | አማራ ክልል ለሙስሊም ነዋሪዎቹ የሰላምና ደህንነት ቀጠና ሊሆን አልቻለም።

Post by sarcasm » 04 May 2022, 19:27

ጎንደር ላይ ልቅሶ አንጂ የዒድ በዓል እንዲኖር አልተፈቀደም!

አማራ ክልል ለሙስሊም ነዋሪዎቹ የሰላምና ደህንነት ቀጠና ሊሆን አልቻለም። ባለፉት 4 ዓመታት በክልሉ ባሉ በሁሉም ዞኖች ሙስሊሞችን ዒላማ ያደረጉ ግድያዎች፣ የመስጂድ ቃጠሎዎችና ትንኮሳዎች፣ የሙስሊም የንግድ ድርጅቶችን እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ ዘረፋና ሀብት ማጋበስ፣ የጅምላ እስሮች፣ የመብት ክልከላዎች ወዘተ ሲፈጸሙ ነበር። ከቀናት በፊት በጎንደር የተፈጸመው የአክራሪ ታጣቂዎችና የመሥተዳደሩ የተቀናጀ ጥቃት በክልሉ ያለው ሙስሊም-ጠልነት፣ በጥቅሉ ደግሞ አናሳዎች-ጠልነት መፈታት ከማይችለበት ደረጃ ላይ መድረሱን አመላካች ነው።

አሳዛኙ ነገር በክልሉ ሙስሊሞችና ሌሎች አናሳዎች ላይ ለተፈጸሙ አሰቃቂ ወንጀሎችና ሽብር ድርጊቶች በአንዳቸውም ላይ ተጠያቂ ተደርጎ የታሰረና የተፈረደበት አካል የለም። ከዚህም ብሶ ጅራፍ ''ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሀል'' እንደሚባለው፣ በደል ባደረሱባቸው ላይ በሞኖፖሊ በተቆጣጠሩት የአማርኛ ሚዲያ ወንጀለኛ አድርገው ዘመቻ ይከፍቱባቸዋል። አሁን የጎንደር ሙስሊም ማኅበረሰብ ከፍተኛ የደህንነተ ሥጋት ውስጥ ነው ያለው። ከቤቱ ወጥቶ ስኳር እንኳን መግዛጥ የሚችልበት ጥበቃ የለውም። በመሆኑም ማኀበረሰቡ የነገን ዒድ በዓል ከተቆለፈበት ቤቱ፣ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሥጋህ ነን በሚሉት አካል የደረሰበትን አሰቃቂ ክህደትና ጥቃት እያሰበ በልቅሶና በሀዘን ያሳልፈዋል።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአማራ ክልል ለሚገኙ አናሳዎች አጋርነቱን ያሳይ።



Please wait, video is loading...