Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ባለፉት 4 ዓመታት በአማራ ክልል በክልሉ ሙስሊሞች ላይ ከሞጣ እስከ እስቴ፥ ከጃራ ገዱ እስከ ቢቸና፥ ከጭልጋ እስከ ጎንደር ከ30 በላይ መስጊዶች ተቃጠሉና ተጠቁ" አሕመዲን ጀበል

Post by sarcasm » 04 May 2022, 07:55

ከለውጥ ወዲህ ብቻ በነበሩት ባለፉት 4 ዓመታት በአማራ ክልል ስልጣን ላይ በነበሩ አምስት የክልሉ ፕሬዝዳንቶች ዘመን በክልሉ ሙስሊሞች ላይ ከሞጣ እስከ እስቴ፥ከጃራ ገዱ እስከ ቢቸና፥ ከጭልጋ እስከ ጎንደር በተደጋጋሚ ጊዜ ሃይማኖትን መሠረት ባደረገ መልኩ ከሠላሣ በላይ መስጊዶች ሲቃጠሉና ሲጠቁ፥የሙስሊሞች ሱቆችና ቤቶች ተለይተው ሲዘረፉና በርካቶች በተገደሉበት በንጹሃን ሙስሊሞች ላይ የሽብር ጥቃቶች ሲፈጸሙ «ለእውነት፥ለፍትህ፥ ለዲሞክራሲና ለሕግ የበላይነት ቆመናል» የሚሉት የደሴቷ ናፋቂ ሚዲያዎች ፥አክቲቪስቶች፥ጋዜጠኞች፥ የክልሉ ባለስልጣናት፥ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ሌሎች አካላት ጭምር አንዳቸውም ቢሆኑ የለበጣ «ድርጊቱ አስነዋሪ ነው።»፥ «እኛም አውግዘነዋል።»፥«የድርጊቱ ፈጻሚዎች ሕዝቡን አይወክሉም።» ፣«ከተማችን ወደ ቀድሞ ሰላሟ ተመልሳለች።» ወዘተ በማለት ለማድበስበስ ይሠራሉ።ዋናው ጥያቄና ጭብጥ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ማንን ይወክላሉ! የሚለው ሳይሆን ለፈጸሙት የሽብር ወንጀል ተጠያቂ ተደረጉ ወይ የሚለው ነበር።

ሆኖም ከጅምሩ ዓላማቸው የችግሩን መጠን ማቃለል፣ለወንጀለኞቹ ሽፋንና ከለላ መስጠት፣ ለእውነትና ፍትህ ከመወገን የራስን የጠለሸ ስም ማደስ በመሆኑ የተፈጸሙት ወንጀሎች በተደጋጋሚ ጊዜ ሆነ ተብለው ተድበስብሰው ቀሩ።

ከዚያ ሁሉ ባለሚዲያ፣አክቲቪስት፣የመብት ተሟጋች፣ጋዜጠኛ፣ታዋቂ ሰዎችና ሰባኪያን መካከል «የሽብር ጥቃቶቹ ጉዳዩ ሳይድበሰበስ በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ወንጀል ፈጻሚዎቹ ላይ አስተማሪ የሆነ ፍርድ ሊያገኙ ይገባል» ብሎ ለተግባራዊነቱ እስከመጨረሻው የሞገተና ለእውነት የቆመ አንድም አካል አላየንም። እንዲያውም ከፊሎቹ የሐሰት ዉንጀላዎቹን በመደገፍ ላይ ተጠምደው ተገኙ። በአንዱም የሽብር ጥቃት ላይ እንኳን የተሳተፉ ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ዉለው ፍርድ አግኝተው አለማወቃቸው በራሱ ችግሩ የተቀናጀና መዋቅራዊ መሆኑን ያስገነዝበናል። ለዚህም ነው በአሁኑ የጎንደር የሽብር ጥቃት ፈጻሚዎችም በተለመደው መንገድ «በቁጥጥር ስር ዋሉ» የሚለው ዘገባም የሽብር ፈጻሚዎቹ ጉዳይም እንደከዚህ ቀደሞቹ በዚያው በአማራ ክልል የሚታይ ከሆነ ዜናው ማስተኛ ኪኒን ከመሆን አይዘልም።
ለነዚህ ጥቃቶቹ ሁሉ ሽፋን ሲሰጡ፥ ጉዳዩቹን ለማቃለል ሲተጉ፥ ችግሮቹን ዉጫዊና የጠላት ሴራ አድርገው በማቅረብ ራሳቸውን ንጹህ ሲያደርጉ ለተበዳዮቹ ድምጽ በመሆኔ «አጋለጠን»፥«ልናፍነው የፈለግነውን ድምጽ እንዲስተጋባ አድረገ» በሚል ቁጭት የገዛ ወገኖቻቸው እስኪታዘቧቸው ድረስ እኔኑና መስሊሞችን መልሰው ለመወንጀል ተፍጨረጨሩ። እንደለመዱት የኔን ስምና ገጽታ ለማጠልሸት የፈጠራ ዜናዎችን በየጓዳዎቻቸው እየፈበረኩ በሚዲያዎቻቸው ተቀባበሉ።አሰራጩ።
በተቆጣጠሩዋቸው ሚዲያዎቻቸው በኩል በለመዱት የሀሰት ክስ ጋጋታ ላይ ተንተርሰው ጠልፎ የመጣል ዘመቻቸውን ጀመሩ።የማታውም ዶኪዩመንተሪ ተበዳይን የመክሰስ፣የጎንደሩን ጥቃት የማቃለልና የችግሩን ሥረ መሠረትን ከዋናው ሥፍራ ለማራቅ ዓላማን ያነገበና ከዚሁ የሚዲያ ጦርነት ጎራ የሚመደብ ነው።
ሚዲያውን የተቆጣጠሩት አካላት በዘገባዎቻቸውም ሆነ ዘጋቢ ፊልሞቻቸው፣ ስለጉዳዩ መግለጫ የሚሰጠው የመንግስት አካልም ለጎንደሩና መሰል የሙስሊሞች ጥቃቶችን ስላነሳሱት የሽብር ቅስቀሳዎች ከስር ባለው የቴሌግራሜ ቻናል( https://t.me/ahmedin99/4273 ) ላይ ስለተያያዙት ቪዲዮዎች እያወቁ እንዳላዩ ማለፍን መርጠዋል።ተሳክቶላቸው ጥቂት ወደነዚህ የሽብር ቅስቀሳዎች ቀረብ የሚል የጥቂት ሰከንዶች የኔን ቪዲዮ ወይም ድምጽን ቢያገኙ የዘወትር ጸሎት ያክል ደጋግመው ለሕዝባቸው ባሰሙም ነበር።

የቴሌግራም ቻናሌ ላይ የተያያዘውን ቪዲዮ ሊንኩን በመጫን ይመልከቱ። 👇
https://t.me/ahmedin99/4273
Please wait, video is loading...