Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Horus » 02 May 2022, 13:54

ኢትዮጵያዊ የሚባሉ ሕዝብ የገጠማቸው የእውቀትና ባህል ችግር እጅግ ግዙፍ ነው ። በዚህ አለም ላይ ተፈጥሮ ወይም ኔቸር የሚባል ነገር አለ። ይህ ሰው የሰራው፣ ሰው የፈጠረው አለም አይደለም። ነገር ግን የሰው ልጅ በዚህ የተፈጥሮ አለም ውስጥ ስለሚኖር የፍጥረትን ጸባይ ማወቅ ግድ ይለዋል ። ከተፈጥሮ ጋር በሰላምና በፍቅር መኖር አለበት ። ያ ካልሆነ ሰው እራሱ ይጠፋል።

ሁለተኛው አለም የሰው ልጅ እራሱ የፈጠረው ካልቸር ወይም ባህል ይባላል። ለምሳሌ መኪና፣ ሃይማኖት፣ ፖለቲካ፣ ዶሮ ወጥ እና ቀሚስ የሰው ስራዎች፣ የሰው ባህል፣ የሰው ካልቸር ናቸው። ሌላው ትልቁ እና አደገኛው ሰው ሰራሽ ነገር ሃሳብ ወይም እምነት ነው። ለምሳሌ አለምን (ኔቸርን) የፈጠረ እራሱ ፍጥረት ሳይሆን አላህ ነው፣ እግዚአብሄር ነው። ጎድ ነው። ጌታ ነው። ያዌ ነው፣ ቡድሃ ነው፣ ዋቃ ነው፣ ወዘተ የሚባሉት የሰው ሃሳቦች ናቸው ። እነዚህን ሃሳቦች የፈጠረው ሰው እራሱ ነው።

በአንድ ቃል እምነት ወይም ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ባህል ነው በቃ! የሰው ልጅን ውድቀት እያስከተለ ያለው የዘመናት ስህተት የሰው ልጅ ኔቸርና ካልቸርን ለያይቶ፣ አንዱ ካንዱ አቃርኖ፣ አንዱ ያንዱ ጠላት አድርጎ የሚደመድም ደደብ ሃሳብ መፍጠሩ ነው። ይህ ልክ እነ ዴካርት የሰው አካልና የሰው አይምሮ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፣ ተቃራኒ ነገሮች ናቸው እንዳሉት ማለት ነው።

የሰው ልጅ አለምን አልፈጠረም። የሰው ልጅ እራሱ በተፈጥሮ የተፈጠረ ነገር እንጂ እራሱ ሕይወትን የፈጠረ ሃይል አይደለም። ካልቸር ወይም ባህል የሰው ልጅ ከፍጥረት የኮረጀው ሞዴል ነው ። ፈረስ አራት እግሮች ስላሉት ሰው አራት ጎማ ያለው መኪና ሰራ። የሰው ችሎታ ተፈጥሮን መኮረጅ ነው። የሰው ልጅ የተፈጥሮን አመክኞ ምን እንደ ሆነ አያውቅም። ፈረስ ለምን አራት እግር እንዳለው አያውቅም።

ስለ እምነትም፣ ስለሃይማኖት፣ ስለሌላ አለማዊ፣ ተፈጥሮአዊ፣ ባህላዊና መለኮታዊ ነገሮች ሁሉ ያለው ግንዛቤ ተመሳሳይ ነው። በኮረጃቸው ነገሮች ያምናል። ያን እምነት ሃሳብ የለዋል። ያን እምነት ስለደጋገመው፣ ደጋግሞ ስላመነው እውቀት ይለዋል ። የሰው ልጅ በራሱ ካልቸር፣ በራሱ ባህል፣ በራሱ ሃሳብ ታስሮ ተቀፍድዶ በራሱ እስር ቤት ውስጥ የሚማቅቅ አሳዛኝ እንሰሳ፣ አሳዛኝ ፍጡር ነው ።

ኢትዮጵያዊያን የጎሳ እምነት፣ የሃይማኖት እምነት፣ የካልቸር እምነት ሁሉም ሰው ሰራሽ ባህሎች፣ ሰው ሰራሽ አርቲፋክቶች መሆናቸውን እስካልገባቸው ድረስ ከዚህ የአመጽ መከራ ሊላቀቁ አይችሉም። ምክንያቱም ካልቸር የአንድ ሰው ማንነት አይደለም። ካልቸር የአንድ ሰው ምንነት አይደለም ። ባህል ወይም ካልቸር የሰው ተግባር፣ የሰው ስራ፣ የሰው ስነምግባር ነው እንጂ የሰው ምንነት አይደለም። ሰው ምንድን ነው? ሲባል መልሱ ሰው ተፈጥሮ የሰራው እንሰሳ ነው ። የሚያስብ እንሰሳ ነው ። ካልቸር፣ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ፖለቲካ፣ ዘፈን፣ ሃሳብ ምንድን ነው? ሲባል መልሱ የሰው ስራ፣ የሰው ተግባር፣ የሰው ቢሄቪየር ነው ።

ታዲያ ኢትዮጵያዊያን እራሳቸው በሰሩት እምነት፣ እራሳቸው ባመኑት እምነት፣ እራሳቸው በፈጠሩት ባህል እርስ በርሳቸው ሲተላለቁ፣ ሲሰቃዩ፣ ሲሰደዱ፣ ሲፈናቀሉ፣ ሲያለቅሱ ከማየት የበለጠ ምን የሚያሳዝን፣ ምን የሚያሳፍር ነገር አለ? አንድ መቶ ሃያ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን በሁለት ሰው ሰራሽ ባህል ተከፋፍለው እንዲህ ሲፋጁ ማየት የሰዎች የማሰብ ችሎታ ዝቅጠት ብቻ ሳይሆን እራሱ የባህሉ፣ የእምነቱ፣ የሃይማኖቱ ደካማነትን ያሳያል። ኢትዮጵያዊያን ከዚህ የጭለማ እምነት ወጥተው ወደ ብርሃን ሃይማኖት ካልገቡ የነገ ሕይወታቸው የመከራ ዘመን እንደ ሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው!

Horus
Senior Member+
Posts: 30901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Horus » 02 May 2022, 14:13

የፍቅርና ሰላም ባህል ያላቸው እመነትና ሃይማኖታቸውም ፍቅርና ሰላም ነው !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Horus » 02 May 2022, 14:27

የፍቅርና ሰላም ባህል ያላቸው እመነትና ሃይማኖታቸውም ፍቅርና ሰላም ነው !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Horus » 02 May 2022, 18:41

"ከትውፊትና ሃይማኖት ትውፊት ይበልጣል" አንድ አቡን በቸግ በዓል ላይ የተናገሩት! ባህል ከሃይማኖት ይበልጣል። ባህል ስነምግባር ነው ። መልካም ስነምግባር በዉሸት ከሚለፈፍ እምነትና ሃይማኖት እጅግ የላቀ ነው ። መልካምና ፍትሃዊ ሰነምግባር የሌለው ባዶ ሃይማኖተኛ ነው። የብዙ ኢትዮጵያዊ በሽታ እየሆነ ያለው ያ ነው ። ስነምግባር አልባ ሃይማኖት ያሸባሪና አክርሪ መፈልፈያ ጎጆ ነው ።

Selam/
Senior Member
Posts: 11828
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Selam/ » 03 May 2022, 09:31

The irony is that most culturally & religiously conservative societies are associated with high crimes, violence & destitution whereas the secular western nations who broke that bondage are prosperous and relatively peaceful. And their success is mainly attributed to the industrial revolution & individual freedom that didn’t taken place in the East. The cultural & religious norms in the West got later superseded by strong education, professionalism & legal and institutional frameworks. But it doesn’t mean abolition of faith is a prerequisite for development or secularism and faith can’t coexist. If that was the case, human societies would have stagnated long ago given 80% of the global population are religious believers. Take US for example, almost half of the population is religious & they belong to a certain congregation. Even the precursor of the ingenuity of Renaissance didn’t need to erase religion but it reformed it.

I don’t think the problem in Ethiopia is associated with too much religion and strong culture. It’s rather the opposite because we have been practicing these same things for thousands of years and sustained as a nation. To me, the issue today is that most people don’t know the basis of their faith & culture at all. In fact, they are bast@rdizing them, and they have become less independent & more dependent on the wisdom of the herd. On top of that the institutional frame work that holds secular societies together is weak or nonexistent.

Horus wrote:
02 May 2022, 13:54
ኢትዮጵያዊ የሚባሉ ሕዝብ የገጠማቸው የእውቀትና ባህል ችግር እጅግ ግዙፍ ነው ። በዚህ አለም ላይ ተፈጥሮ ወይም ኔቸር የሚባል ነገር አለ። ይህ ሰው የሰራው፣ ሰው የፈጠረው አለም አይደለም። ነገር ግን የሰው ልጅ በዚህ የተፈጥሮ አለም ውስጥ ስለሚኖር የፍጥረትን ጸባይ ማወቅ ግድ ይለዋል ። ከተፈጥሮ ጋር በሰላምና በፍቅር መኖር አለበት ። ያ ካልሆነ ሰው እራሱ ይጠፋል።

ሁለተኛው አለም የሰው ልጅ እራሱ የፈጠረው ካልቸር ወይም ባህል ይባላል። ለምሳሌ መኪና፣ ሃይማኖት፣ ፖለቲካ፣ ዶሮ ወጥ እና ቀሚስ የሰው ስራዎች፣ የሰው ባህል፣ የሰው ካልቸር ናቸው። ሌላው ትልቁ እና አደገኛው ሰው ሰራሽ ነገር ሃሳብ ወይም እምነት ነው። ለምሳሌ አለምን (ኔቸርን) የፈጠረ እራሱ ፍጥረት ሳይሆን አላህ ነው፣ እግዚአብሄር ነው። ጎድ ነው። ጌታ ነው። ያዌ ነው፣ ቡድሃ ነው፣ ዋቃ ነው፣ ወዘተ የሚባሉት የሰው ሃሳቦች ናቸው ። እነዚህን ሃሳቦች የፈጠረው ሰው እራሱ ነው።

በአንድ ቃል እምነት ወይም ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ባህል ነው በቃ! የሰው ልጅን ውድቀት እያስከተለ ያለው የዘመናት ስህተት የሰው ልጅ ኔቸርና ካልቸርን ለያይቶ፣ አንዱ ካንዱ አቃርኖ፣ አንዱ ያንዱ ጠላት አድርጎ የሚደመድም ደደብ ሃሳብ መፍጠሩ ነው። ይህ ልክ እነ ዴካርት የሰው አካልና የሰው አይምሮ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፣ ተቃራኒ ነገሮች ናቸው እንዳሉት ማለት ነው።

የሰው ልጅ አለምን አልፈጠረም። የሰው ልጅ እራሱ በተፈጥሮ የተፈጠረ ነገር እንጂ እራሱ ሕይወትን የፈጠረ ሃይል አይደለም። ካልቸር ወይም ባህል የሰው ልጅ ከፍጥረት የኮረጀው ሞዴል ነው ። ፈረስ አራት እግሮች ስላሉት ሰው አራት ጎማ ያለው መኪና ሰራ። የሰው ችሎታ ተፈጥሮን መኮረጅ ነው። የሰው ልጅ የተፈጥሮን አመክኞ ምን እንደ ሆነ አያውቅም። ፈረስ ለምን አራት እግር እንዳለው አያውቅም።

ስለ እምነትም፣ ስለሃይማኖት፣ ስለሌላ አለማዊ፣ ተፈጥሮአዊ፣ ባህላዊና መለኮታዊ ነገሮች ሁሉ ያለው ግንዛቤ ተመሳሳይ ነው። በኮረጃቸው ነገሮች ያምናል። ያን እምነት ሃሳብ የለዋል። ያን እምነት ስለደጋገመው፣ ደጋግሞ ስላመነው እውቀት ይለዋል ። የሰው ልጅ በራሱ ካልቸር፣ በራሱ ባህል፣ በራሱ ሃሳብ ታስሮ ተቀፍድዶ በራሱ እስር ቤት ውስጥ የሚማቅቅ አሳዛኝ እንሰሳ፣ አሳዛኝ ፍጡር ነው ።

ኢትዮጵያዊያን የጎሳ እምነት፣ የሃይማኖት እምነት፣ የካልቸር እምነት ሁሉም ሰው ሰራሽ ባህሎች፣ ሰው ሰራሽ አርቲፋክቶች መሆናቸውን እስካልገባቸው ድረስ ከዚህ የአመጽ መከራ ሊላቀቁ አይችሉም። ምክንያቱም ካልቸር የአንድ ሰው ማንነት አይደለም። ካልቸር የአንድ ሰው ምንነት አይደለም ። ባህል ወይም ካልቸር የሰው ተግባር፣ የሰው ስራ፣ የሰው ስነምግባር ነው እንጂ የሰው ምንነት አይደለም። ሰው ምንድን ነው? ሲባል መልሱ ሰው ተፈጥሮ የሰራው እንሰሳ ነው ። የሚያስብ እንሰሳ ነው ። ካልቸር፣ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ፖለቲካ፣ ዘፈን፣ ሃሳብ ምንድን ነው? ሲባል መልሱ የሰው ስራ፣ የሰው ተግባር፣ የሰው ቢሄቪየር ነው ።

ታዲያ ኢትዮጵያዊያን እራሳቸው በሰሩት እምነት፣ እራሳቸው ባመኑት እምነት፣ እራሳቸው በፈጠሩት ባህል እርስ በርሳቸው ሲተላለቁ፣ ሲሰቃዩ፣ ሲሰደዱ፣ ሲፈናቀሉ፣ ሲያለቅሱ ከማየት የበለጠ ምን የሚያሳዝን፣ ምን የሚያሳፍር ነገር አለ? አንድ መቶ ሃያ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን በሁለት ሰው ሰራሽ ባህል ተከፋፍለው እንዲህ ሲፋጁ ማየት የሰዎች የማሰብ ችሎታ ዝቅጠት ብቻ ሳይሆን እራሱ የባህሉ፣ የእምነቱ፣ የሃይማኖቱ ደካማነትን ያሳያል። ኢትዮጵያዊያን ከዚህ የጭለማ እምነት ወጥተው ወደ ብርሃን ሃይማኖት ካልገቡ የነገ ሕይወታቸው የመከራ ዘመን እንደ ሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው!
Last edited by Selam/ on 03 May 2022, 11:12, edited 3 times in total.

Abere
Senior Member
Posts: 11100
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Abere » 03 May 2022, 10:37

I think talking of religion as culture is dubious. Definitions of certain practices don't have easy definitions and oversimplifications may send inaccurate understandings. Religion is one among these. Although culture is a human product, rationally created as a coping mechanism to the different aspect of life. Only human beings have culture, because of the unique gift of mental faculty and language. God created man in His own image and has given knowledge. In the context of talking the natural world, culture is the fabric of society, but in the context of the Supernatural world, it is totally different. Religion transcends culture; however, humanities show variations in their ritual practice. For instance, now adays, so called social scientists even faced problem of defining marriage - the bond of a man and woman with the intent of sexual gratification (natural), procreation (reproduction) and also economic production. Marriage is a cultural practice; it is also natural although ritual ceremonies are performed in diverse ways culturally. The natural purpose of reproduction is a natural obligation of all living creature ( female and male). Yet, social scientists just like religion are distorting its definition because of the influence of activism of pleasing everyone while going unnatural. These activists are also increasing breaching what are Supernatural as well.

union
Member+
Posts: 6374
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by union » 03 May 2022, 11:35

Listro horus talking to himself again about a crap :lol:
ባህል እና እምነት አንድ ናቸው ይለናል ዛሬ ደግሞ ድብርት ላይ ነው መሰለኝ። ይዘባርቃል

Selam/
Senior Member
Posts: 11828
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Selam/ » 03 May 2022, 11:55

Good point, it’s a fvcked up situation either way. To prove the separation of state & religion and advance individual liberties, secular nations are drifting further away from natural practices. And to satisfy voters, they are doing quite the opposite of what the scriptures teach.

Religious nations on the other hand mix up faith & legal institutions so much that they create contradictions & confusions every step in the way. For example, with the rise of Hindu nationalism in India, the prospect of tolerance let alone unity in diversity is nonexistent. The Islamic fundamentalist are displacing & slaughtering Christian’s and what they call infidels through out the world. And our PM shows up at every major religious events to look friendly and satisfy the congregation. A tough love!

Abere wrote:
03 May 2022, 10:37
I think talking of religion as culture is dubious. Definitions of certain practices don't have easy definitions and oversimplifications may send inaccurate understandings. Religion is one among these. Although culture is a human product, rationally created as a coping mechanism to the different aspect of life. Only human beings have culture, because of the unique gift of mental faculty and language. God created man in His own image and has given knowledge. In the context of talking the natural world, culture is the fabric of society, but in the context of the Supernatural world, it is totally different. Religion transcends culture; however, humanities show variations in their ritual practice. For instance, now adays, so called social scientists even faced problem of defining marriage - the bond of a man and woman with the intent of sexual gratification (natural), procreation (reproduction) and also economic production. Marriage is a cultural practice; it is also natural although ritual ceremonies are performed in diverse ways culturally. The natural purpose of reproduction is a natural obligation of all living creature ( female and male). Yet, social scientists just like religion are distorting its definition because of the influence of activism of pleasing everyone while going unnatural. These activists are also increasing breaching what are Supernatural as well.

Selam/
Senior Member
Posts: 11828
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Selam/ » 03 May 2022, 12:00

የስሙኒ ልጅ ቱስ ቱስ - what you got now? :lol:
union wrote:
03 May 2022, 11:35
Listro horus talking to himself again about a crap :lol:
ባህል እና እምነት አንድ ናቸው ይለናል ዛሬ ደግሞ ድብርት ላይ ነው መሰለኝ። ይዘባርቃል

Horus
Senior Member+
Posts: 30901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Horus » 03 May 2022, 13:45

ሃይማኖት ካልቸር ነው ወይስ አይደለም?

ከላይ እንዳልኩት ያሉን ሁለት አይነት አለሞች ናቸው፤ አንድ ተፈጥሮአዊ (ናቹራል) ሌላው ሰው ሰራሽ ባህላዊ (ካልቸራል) ናቸው። እምነት ወይም ሃይማኖት እንደ ኬሚካሎችና እጸዋት በተፈጥሮ የበቀለ ሳይሆን የሰው አይምሮ የፈጠረው ሃሳብና ስራ ነው ። ፈጣሪ ቃል ነው፣ ቃልም አለምን ፈጠረ ይላል። በእምነትና ሃይማኖት መሰረት አለምን የፈጠረ ሃሳብ ነው ። ሃሳብ የሰው ልጅ የፈጠረው አርቲፋክት ነው። ስሜት (ፊሊንግ) እንሰሳዎች ሁሉ አላቸው። ሌላው ቀርቶ እጸዋት ሁሉ ስሜት እንዳላቸው እየታወቀ ነው ። ነገር ግን እስካሁን ድረስ የሌላውን አለም ምስል ባንጎሉ ወስጥ አስገብቶ በቋንቋ አማካይነት ትርክት፣ ፍልስፍና፣ የነገሮች ንድፈ ሃሳብ፣ የነገሮች ብልሃትና የተግባራት እቅድ የሚያሰላ የሰው ልጅ ነው። ያ ሁሉ የሰው ስራ ነው። ከነዚህ የዘመናት ሰው ሰራሽ እድገት ውስጥ አንዱ እምነትና ሃይሞኖትን መፍጠር ነው ።

አለም ከየት መጣ? ማን ሰራው? ሰው ከየት መጣ? ሲሞት የት ይሄዳል የሚባሉት ህሳቤና ምርምሮች ሁሉ የሰው ህሳቤ ውጤት ናቸው። መጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃል አለምን ፈጠረ፤ ሃሳብ አለምን ፈጠረ ይላል ። ያ ማለት ቃል ዛፍና ጋላክሲን ፈጠረ አይደለም። ቃል ሃሳብን፣ ቃል እምነትን፣ ቃል ፍልስፍናን፣ ቃል ሃይማኖት ፈጠረ ማለት ነው ። ሜታፊዚካል፣ ሱፐርናቱራል ወዘተ የምንላቸው ሁሉ ሃሳብ ናቸው። ሃሳብ ልክ እንደ አንድ ባህላዊ ዕቃ ካልቸር ነው። ካልቸሩ ተለያየ ማለት ሃሳቡ ተለታየ ነው ።

ለምሳሌ በማንኛውም ሃይማኖት ውስጥ ዶግማና ቀኖና አለ ። ዶግማ የእምነቱ ፍልስፍና ወይም ቲኦሪ ነው፤ ዶክትሪን ነው። ቀኖናው ዘዴው፣ ብልሃቱ ወይም ክህሎቱ ነው ። እያንዳንዱ ሃይማኖት በሃሳብም በተግብርም ይለያያሉ። ለምን ቢባል ሃይማኖት ካልቸር ስለሆነ። ነገር ግን አንድ የሰው ሴል ህዋስ ወይም ኦክሲጂ የሚባለው አየር በአለም ሁሉ አንድ ነው ። ለምን ቢባል ተፈጥሮ ስለሆነ። ይህን ለይቶ ማስቀመጥ የመጀመሪያ ጉዳይ ነው ።

ወደ ግለሰቦችና ማህበረ ሰቦች ስንመጣ ያለው ሁለት ነገር ነው ፤ አንዱ ሰው ነው፤ ሌላው የሰው ባህሪ (በሄቪየር) ነው። ይህ ረጅም ነገር ስለሆነ ዝርዝሩ ውስጥ አልገባም። ቁም ነገሩ እምነት የሰው ባህሪ ነው ። ሃይማኖት የሰው ባህሪ ነው። በግለሰብ ደረጃ ሳይኮሎጂም እንበለው ሌላ ስም ያው ቢሄቪየር ነው ። በማህበረሰብ ደረጃ ሶሺያል ሳይኮሎጂ እንበለው ሌላ ስም ያው ቢሄቪየር ነው ። ልብ እንበል ሞራሊቲ፣ ስነምግባር፣ መንፈሳዊነት፣ እስፒሪቿሊቲ የምንላቸው ነገሮች ሁሉ የሰው ባህሪያት ናቸው።

እዚህ ላይ ካልቸር ሁሉ በአመክንዮ (ራሽናሊዝም) ነው የተገነባው ወይስ ባቦ ሰጡኝና በግብታ ወደሚለው አልገባም፤ በሁለቱም ዘዴ ስለተፈጠሩ ማለት ነው። ቁም ነገሩ ግን ይህ ነው ። ካልቸር በመሰረቱ ክህሎት ነው፤ የኑሮ ዘዴ፣ የኑሮ ዘይቤ፣ የኑሮ ብልሃት፣ የኑሮ እስኪል ነው ። እምነትና ሃይማኖትም አንዱ የካልቸር አካል ብቻ ሳይሆን በመሰረቱ እነሱም የኑሮ ዘዴ፣ የስነምግባር ስልት፣ የሞራሊቲ ኮድ ኦፍ ኮንዳክት፣ መመሪያ ክህሎቶች ናቸው ።

ይህን ሳንገነዘብ ስንቀር ነው አይማኖት ለሰው ልጆች ምድራዊና ሰማታዊ ደህንነትና ደስታ መዋል ሲገባቸው የእልቂትና የሃዘን ምንጭ እየሆኑ ያሉት! የካልቸር አላማ ምንድን ነው? የእምነት አላማ ምንድን ነው? የሃይማኖት አላማ ምንድን ነው? እነዚህ ቁልፍ ትያቄዎች ናቸው ። ሃማኖት የተፈጠረው የሰውን ልጅ ከቀውስ አውጥቶ በስርዓትና በሰላም እንዲኖር ነው።
Last edited by Horus on 04 May 2022, 01:33, edited 6 times in total.

Abere
Senior Member
Posts: 11100
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Abere » 03 May 2022, 14:12

Although religion and culture have very entangled relationship;and one can affetcs or shapes the other, it does not mean they are one and the same. If one claims religion is culture, it goes againt the meaning and role of religion it self. Because culture is manmade. Thus, it sounds as if man created God. As to me this illogical. God created man; and man created culture. However, man worships of God and applying this practice of worship enriches culture.

Horus
Senior Member+
Posts: 30901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Horus » 03 May 2022, 14:56

አበረ፣
በቃ ይህ ነውኮ እምነት የሚባለው፤ 'ፈጣሪ ሰውን ፈጠረ' ። ካልቸር ሃይማኖትን በብዙ ሺ ወይም መቶ ሺ አመት ይቀድመዋል ። የሰው ልጅ ጫካና ዋሻ ውስጥ ሲኖር ዛፍ ላይ የተንጠለጠለውን ፍሬ መንካት መድረስ አቅቶት ሌላ እንጨት ሰብሮ በዱላ ፍሬውን በመምታት እጁን ያረዘመ ቀን ነው ሰው ካልቸር ሰው ሰራሽ መሳሪያ መፍጠር የጀመረው! እጅግ እጅግ ድሮ ማለት ነው ። የድንጋይ መሳሪያዎችን መጠቀም፣ እሳትን መጠቀን የጀመረው እጅግ እጅግ ድሮ ነው። ልብ በል እሳት ካልቸር ነው። ካልቸራል አርቲፋክት ነው። እሳት መሞቅ፣ ምግብ መጥበስ በዘመኑ እንደ ዛሬ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ነበር።

ወደ ሃይማኖት ስንምጣ 'ፈጣሪ' የሚለው ቃል ጥንታዊ ግብጾች ለመጀምሪያ ግዜ የፈጠሩት 3100 ቢ ሲ ነው ማለት የዛሬ 5115 አመት ማለት ነው። እንዲያውም እነዚህ የድሮ ግብጾች 3 ሺ አመት ብዙ አይነት ፈጣሪዎች አምልከው ከኖሩ በኋላ ነው የዛሬ 2500 አመት አካባቢ ስለ አንድ ፈጣሪ ፍልስፍና የተጀመረው ። ኦሪት ዘፍጥረት ማለት የፍጥረት መሰረተ ትርክት ወይም ኦሪጅን ሚትዝ ማለት ያ ነው የእምነታችን መቆሚያ አሰምሽን ወይም መሰረት ድንጋይ። ያ የሆነው ቢበዛ የዛሬ 2500 አካባቢ ነው ። ልብ በል ይህ ሁሉ የግብጽ ፒራሚድና የግሪክ ካቴድራሎች ሲሰሩ የሰው ልጅ በአንድ ፈጣሪ አያምንም ነበር ። ክርስትና፣ እስልምና እና ጁዳኢዝም እጅግ አዲስ ሃይማኖትች እንደ ሆኑ አትርሳ።

ሃይማኖት የተወለደው ከብዙ ሺ ዘመናት የሰው ልጅ ባህላዊ (ትውፊታዊ) ካልቸራል እድገት በኋላ ነው ። ሃይማኖት ካልቸርን ኢንፍሉውንስ ማድረግ አይደለም፣ ሰው ፈጣሪውን የሚያመልከው በካልቸሩ አማካይነት ነው ። ካልቸር የሌላቸው ሕዝቦች ሃይማኖት የላቸውም።

ልብ በል ጸሎት ካልቸር ነው። ከበሮ ካልቸር ነው ። መዝሙር ካልቸር ነው። ቅዳሴ ካልቸር ነው ። ስግደት ካልቸር ነው ። የቤተ ክርስቲያ ህንጻ ካልቸር ነው። መስቀል፣ የቀሳውስት አልባሳት ካልቸራል አርቲፋክትስ ናቸው ። ፈጣሪን የምናመልከው በባህላችን ነው።

Horus
Senior Member+
Posts: 30901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Horus » 03 May 2022, 17:49

የቅድመ ክርስትና ፈጣሪ ታሪክ

union
Member+
Posts: 6374
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by union » 03 May 2022, 23:53

Listro horus aka selam aka abere talking to himself :lol:

Abdisa
Member+
Posts: 5758
Joined: 25 Apr 2010, 19:14

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Abdisa » 04 May 2022, 00:02

Horus: The greatest philosopher of our time! It is wise people like you who restore our faith in humanity. This is a masterpiece!
Horus wrote:
02 May 2022, 13:54
ኢትዮጵያዊ የሚባሉ ሕዝብ የገጠማቸው የእውቀትና ባህል ችግር እጅግ ግዙፍ ነው ። በዚህ አለም ላይ ተፈጥሮ ወይም ኔቸር የሚባል ነገር አለ። ይህ ሰው የሰራው፣ ሰው የፈጠረው አለም አይደለም። ነገር ግን የሰው ልጅ በዚህ የተፈጥሮ አለም ውስጥ ስለሚኖር የፍጥረትን ጸባይ ማወቅ ግድ ይለዋል ። ከተፈጥሮ ጋር በሰላምና በፍቅር መኖር አለበት ። ያ ካልሆነ ሰው እራሱ ይጠፋል።

ሁለተኛው አለም የሰው ልጅ እራሱ የፈጠረው ካልቸር ወይም ባህል ይባላል። ለምሳሌ መኪና፣ ሃይማኖት፣ ፖለቲካ፣ ዶሮ ወጥ እና ቀሚስ የሰው ስራዎች፣ የሰው ባህል፣ የሰው ካልቸር ናቸው። ሌላው ትልቁ እና አደገኛው ሰው ሰራሽ ነገር ሃሳብ ወይም እምነት ነው። ለምሳሌ አለምን (ኔቸርን) የፈጠረ እራሱ ፍጥረት ሳይሆን አላህ ነው፣ እግዚአብሄር ነው። ጎድ ነው። ጌታ ነው። ያዌ ነው፣ ቡድሃ ነው፣ ዋቃ ነው፣ ወዘተ የሚባሉት የሰው ሃሳቦች ናቸው ። እነዚህን ሃሳቦች የፈጠረው ሰው እራሱ ነው።

በአንድ ቃል እምነት ወይም ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ባህል ነው በቃ! የሰው ልጅን ውድቀት እያስከተለ ያለው የዘመናት ስህተት የሰው ልጅ ኔቸርና ካልቸርን ለያይቶ፣ አንዱ ካንዱ አቃርኖ፣ አንዱ ያንዱ ጠላት አድርጎ የሚደመድም ደደብ ሃሳብ መፍጠሩ ነው። ይህ ልክ እነ ዴካርት የሰው አካልና የሰው አይምሮ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፣ ተቃራኒ ነገሮች ናቸው እንዳሉት ማለት ነው።

የሰው ልጅ አለምን አልፈጠረም። የሰው ልጅ እራሱ በተፈጥሮ የተፈጠረ ነገር እንጂ እራሱ ሕይወትን የፈጠረ ሃይል አይደለም። ካልቸር ወይም ባህል የሰው ልጅ ከፍጥረት የኮረጀው ሞዴል ነው ። ፈረስ አራት እግሮች ስላሉት ሰው አራት ጎማ ያለው መኪና ሰራ። የሰው ችሎታ ተፈጥሮን መኮረጅ ነው። የሰው ልጅ የተፈጥሮን አመክኞ ምን እንደ ሆነ አያውቅም። ፈረስ ለምን አራት እግር እንዳለው አያውቅም።

ስለ እምነትም፣ ስለሃይማኖት፣ ስለሌላ አለማዊ፣ ተፈጥሮአዊ፣ ባህላዊና መለኮታዊ ነገሮች ሁሉ ያለው ግንዛቤ ተመሳሳይ ነው። በኮረጃቸው ነገሮች ያምናል። ያን እምነት ሃሳብ የለዋል። ያን እምነት ስለደጋገመው፣ ደጋግሞ ስላመነው እውቀት ይለዋል ። የሰው ልጅ በራሱ ካልቸር፣ በራሱ ባህል፣ በራሱ ሃሳብ ታስሮ ተቀፍድዶ በራሱ እስር ቤት ውስጥ የሚማቅቅ አሳዛኝ እንሰሳ፣ አሳዛኝ ፍጡር ነው ።

ኢትዮጵያዊያን የጎሳ እምነት፣ የሃይማኖት እምነት፣ የካልቸር እምነት ሁሉም ሰው ሰራሽ ባህሎች፣ ሰው ሰራሽ አርቲፋክቶች መሆናቸውን እስካልገባቸው ድረስ ከዚህ የአመጽ መከራ ሊላቀቁ አይችሉም። ምክንያቱም ካልቸር የአንድ ሰው ማንነት አይደለም። ካልቸር የአንድ ሰው ምንነት አይደለም ። ባህል ወይም ካልቸር የሰው ተግባር፣ የሰው ስራ፣ የሰው ስነምግባር ነው እንጂ የሰው ምንነት አይደለም። ሰው ምንድን ነው? ሲባል መልሱ ሰው ተፈጥሮ የሰራው እንሰሳ ነው ። የሚያስብ እንሰሳ ነው ። ካልቸር፣ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ፖለቲካ፣ ዘፈን፣ ሃሳብ ምንድን ነው? ሲባል መልሱ የሰው ስራ፣ የሰው ተግባር፣ የሰው ቢሄቪየር ነው ።

ታዲያ ኢትዮጵያዊያን እራሳቸው በሰሩት እምነት፣ እራሳቸው ባመኑት እምነት፣ እራሳቸው በፈጠሩት ባህል እርስ በርሳቸው ሲተላለቁ፣ ሲሰቃዩ፣ ሲሰደዱ፣ ሲፈናቀሉ፣ ሲያለቅሱ ከማየት የበለጠ ምን የሚያሳዝን፣ ምን የሚያሳፍር ነገር አለ? አንድ መቶ ሃያ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን በሁለት ሰው ሰራሽ ባህል ተከፋፍለው እንዲህ ሲፋጁ ማየት የሰዎች የማሰብ ችሎታ ዝቅጠት ብቻ ሳይሆን እራሱ የባህሉ፣ የእምነቱ፣ የሃይማኖቱ ደካማነትን ያሳያል። ኢትዮጵያዊያን ከዚህ የጭለማ እምነት ወጥተው ወደ ብርሃን ሃይማኖት ካልገቡ የነገ ሕይወታቸው የመከራ ዘመን እንደ ሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው!

Horus
Senior Member+
Posts: 30901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Horus » 04 May 2022, 01:20

Abdisa wrote:
04 May 2022, 00:02

አብዲሳ፤
ምስጋናህ ከአቅሜ በላይ የማይገባኝ ነው፤ ሆኖም በእጅጉ አመሰግንሃለሁ !!

Horus
Senior Member+
Posts: 30901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Horus » 04 May 2022, 03:25

የፍቅርና ሰላም ካልቸር ያላቸው ሁሉ ሃይማኖታቸው ፍቅርና ሰላም ይሆናል!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Horus » 05 May 2022, 16:33

ከላይ እንዳልኩት ካልቸርም ሃይማኖትም የኑሮ ዘዴዎች፣ ማህበራዊ ክህሎቶች ናቸው። ከዚህ ቀደም ባጭር ማሰብና በረጅም ማሰብ፣ በፍጥነትና በዝግታ ማሰብ፣ አጭር ተግባር (ታክቲክና) ረጅም ተግባር (እስትራተጂያዊ ተግባር) ያላቸው ትስስርና እንዴት ረጅም ተግባር በአጭር እንደ ሚገነባ አንስተን ነበር። አጭር፣ አሁናዊ፣ እና የችኮላ ህሳቤና ስራዎች ረጃጅም መጥፎ ውጤቶችና መዘዞችን ይወልዳሉ። ይህ ኮመን ሴንስ ዊዝደም ነው ። ለምሳሌ ስልጤን ተመልከቱ። በስሜትና አጭር ችኩል ጸረ ክርስትና ባህሪዎቹ ሳቢያ ገና በግሩ ያልቆመው ዎራቤ ኮሌጅ የተማሪ ንቅናቄ ማዕከል እየሆነ ነው ። ክዚህ በኋላ ይህ ኮሌጅ በተማሪ የተጠላ ይሆናል ። ትግሬን ተመልከቱ ባለፉት 3 አመታት በተደጋጋሚ በሰራው ያጭር ግዜ ችኩል፣ ህሳቤና ችኩት ተግባር እጅር የተወሳሰበ የረጅም ግዜ ችግር ታቅፎ ቁጭ ብሏል ።

ጥሩ ትልቅ ነገርም፣ መጥፎ ትልቅ ነገርም ከትንሽ ሃሳብና ከትንሽ ተግባር ነው የሚያድጉት። የእለት ተለት ባህሪው የተበላሸ ካልቸርና ሃይማኖት የሚያመርቱት የረጅም ዘመን ችግር ነው ። ይህ መርህ ነው!

Horus
Senior Member+
Posts: 30901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ካልቸር ተግባር እንጂ ማንነት አይደለም

Post by Horus » 11 May 2022, 23:29

ሃይማኖትና ካልቸር ያላቸው ዝምድና ምንድን ነው?

Post Reply