Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ምድረ ከብድ (ክቡር ምደር) ጉራጌ የአባታችን ቅዱስ አቦ ማረፊያ ገዳም

Post by Horus » 14 Mar 2022, 01:32

በ1460 ዓ/ም በግብጻዊው አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ተመስርቶ ሲወድቅ ሲነሳ ለዘመናት ጽንቶ ለመጨረሻ ግዜ ታላቁ ምኒልክና ጦር አበጋዝ ሃብተ ጎርጊስ ዲነግዴ ውብ አድርገው እንዳደሱት፣ ያባቶቻችን አጽም ማረፊያ !!!!

Tadiyalehu
Member
Posts: 664
Joined: 29 Jul 2014, 09:53

Re: ምድረ ከብድ (ክቡር ምደር) ጉራጌ የአባታችን ቅዱስ አቦ ማረፊያ ገዳም

Post by Tadiyalehu » 14 Mar 2022, 19:35

Horus
አያታችን (የእናታችን አባት) በ1904 ዓም ተወልደው ክርስትና የተነሱበት ደብር ምድረከብድ አቦ ነው። ይህን ታሪክ ከእናታችን እና ከሴቷ አያታችን እየሰማን አድገናል ።
የአያታችንን የትውልድ ደብር እሱ ተመችቶት ሳያሳየን አልፏል። ይህን ታሪካዊ ደብር እና የአያታችንን ሀገር ለእናታችን እና ለአክስት አጎቶቻችን ለማስገብኘት እኛም ሄደን ለማየት ትልቅ ህልም አለን።
አቡዬ ይርዱን!

Horus
Senior Member+
Posts: 30915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ምድረ ከብድ (ክቡር ምደር) ጉራጌ የአባታችን ቅዱስ አቦ ማረፊያ ገዳም

Post by Horus » 14 Mar 2022, 20:07

Tadiyalehu wrote:
14 Mar 2022, 19:35
Horus
አያታችን (የእናታችን አባት) በ1904 ዓም ተወልደው ክርስትና የተነሱበት ደብር ምድረከብድ አቦ ነው። ይህን ታሪክ ከእናታችን እና ከሴቷ አያታችን እየሰማን አድገናል ።
የአያታችንን የትውልድ ደብር እሱ ተመችቶት ሳያሳየን አልፏል። ይህን ታሪካዊ ደብር እና የአያታችንን ሀገር ለእናታችን እና ለአክስት አጎቶቻችን ለማስገብኘት እኛም ሄደን ለማየት ትልቅ ህልም አለን።
አቡዬ ይርዱን!
ታድያለሁ፣
ታስታውስ እንደ ሆነ እንደ ዛሬ ስለምድረ ከብድ አንስቼ ባባቴ ኦሮሞ ነኝ፣ በናቴ ክስታኔ ነኝ እድገቴ አርሲ ነው ብለሀኝ ትንሽ ተጨዋወትንና በሆነ ነገር ሳንስማማ ቀረን ። በአማራ ሕዝብ ላይ ያለ ጥላቻ አይመቸኝም ። እኔ የዘር ፖለቲካ እጠላለሁ እንደ ማንኛውም ጉራጌ፤ የዘር ፖለቲካ ትግሬም ያምጣው፣ ኦሮሞም ያምጣው፣ አማራም ያምጣው፤ ከዚያ ባለፈ እኔ ለትግሬም ኦሮሞም አማራም ሕዝብ ጥላቻ የለኝም፣ እንደ ማንኛውም ጉራጌ ማለት ነው። አንተ ስላማራ የምትጽፈው ሁል ግዜ በውነት ይህ ሰው እናቱ ጉራጌ ልትሆን እንዴት ትችላቸው እያልኩ አስባለሁ! በተረፈ ቅዱሱን ምድረ ከብድ ለመጎብኘት ያብቃ። እንደ ምታቀው ምድረ ከብድ ላይ ቆመን ነው ዝዋይን የምናየው። ጭላሎ ተራራ ቆመህም ምድረ ከብድ አቦን ማየት ትችላለህ ፣ ቅርብ ለቅርብ ናቸው ። ምድረ ከብድ በታሪክ የዉሃ ችግር ነበረበት፤ አሁን ያ ችግር እየተፈታ ዉበቱ እንደ ጥንት እየተመለሰ ነው ። ኬር!

Tadiyalehu
Member
Posts: 664
Joined: 29 Jul 2014, 09:53

Re: ምድረ ከብድ (ክቡር ምደር) ጉራጌ የአባታችን ቅዱስ አቦ ማረፊያ ገዳም

Post by Tadiyalehu » 15 Mar 2022, 15:31

Horus wrote:
14 Mar 2022, 20:07
Tadiyalehu wrote:
14 Mar 2022, 19:35
Horus
አያታችን (የእናታችን አባት) በ1904 ዓም ተወልደው ክርስትና የተነሱበት ደብር ምድረከብድ አቦ ነው። ይህን ታሪክ ከእናታችን እና ከሴቷ አያታችን እየሰማን አድገናል ።
የአያታችንን የትውልድ ደብር እሱ ተመችቶት ሳያሳየን አልፏል። ይህን ታሪካዊ ደብር እና የአያታችንን ሀገር ለእናታችን እና ለአክስት አጎቶቻችን ለማስገብኘት እኛም ሄደን ለማየት ትልቅ ህልም አለን።
አቡዬ ይርዱን!
ታድያለሁ፣
ታስታውስ እንደ ሆነ እንደ ዛሬ ስለምድረ ከብድ አንስቼ ባባቴ ኦሮሞ ነኝ፣ በናቴ ክስታኔ ነኝ እድገቴ አርሲ ነው ብለሀኝ ትንሽ ተጨዋወትንና በሆነ ነገር ሳንስማማ ቀረን ። በአማራ ሕዝብ ላይ ያለ ጥላቻ አይመቸኝም ። እኔ የዘር ፖለቲካ እጠላለሁ እንደ ማንኛውም ጉራጌ፤ የዘር ፖለቲካ ትግሬም ያምጣው፣ ኦሮሞም ያምጣው፣ አማራም ያምጣው፤ ከዚያ ባለፈ እኔ ለትግሬም ኦሮሞም አማራም ሕዝብ ጥላቻ የለኝም፣ እንደ ማንኛውም ጉራጌ ማለት ነው። አንተ ስላማራ የምትጽፈው ሁል ግዜ በውነት ይህ ሰው እናቱ ጉራጌ ልትሆን እንዴት ትችላቸው እያልኩ አስባለሁ! በተረፈ ቅዱሱን ምድረ ከብድ ለመጎብኘት ያብቃ። እንደ ምታቀው ምድረ ከብድ ላይ ቆመን ነው ዝዋይን የምናየው። ጭላሎ ተራራ ቆመህም ምድረ ከብድ አቦን ማየት ትችላለህ ፣ ቅርብ ለቅርብ ናቸው ። ምድረ ከብድ በታሪክ የዉሃ ችግር ነበረበት፤ አሁን ያ ችግር እየተፈታ ዉበቱ እንደ ጥንት እየተመለሰ ነው ። ኬር!
Horus
አመሠግናለሁ።
አዎ! ምድረከብድ ከአርሲ ይታያል። እንደውም እናቴ ስትነግረኝ ... ድሮ የመስቀል በዓል ሊከበር ሶስት ቀን ሲቀረው ከ መስከረም14 ጀምሮ የሚደመር የጉራጌ ደመራ /መስቀል ነበር ይባላል።
በዚህ ወቅት አያቴ... እናቴንና ወንድም እህቶቿን ይዞ አከባቢያቸው ወዳለች ትንሽ ጉብታ ላይ ማታ ማታ እየወጣ ... ተመልከቱ የሀገሬ መስቀል መከበር ጀመረ ይላቸው ነበር አሉ።
ምድረከብድ ከ14 ጀምሮ የሚበራውን ደመራ ማታ ማታ ከአርሲ በሩቅ እያዩት ነው ያደጉት።

ሌላው አማራን ትጠላለህ ስላልከኝ ጉዳይ ....
ብታምነኝም ባታምነኝም እኔ የምጠላው የኢትዮጵያ ብሄር ብሔረሰብ የለም።
የነሱ ጽንፈኞቾ የሚያካሂዱትን ፀረ ኦሮሞ ጥላቻና ፕሮፓጋንዳ ግን ያለምንም ጥርጥር እዋጋለሁ። ይሄንን ላለፉት 15 ዓመታት በላይ ከትምህርት ቤት ጀምሮ የነበርኩበት ነው።
በድጋሜ አመሠግናለሁ !

Post Reply