Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11135
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የኢትዮጵያ ችግር የሚፈታው የአማራ ህዝብ ችግር ሲፈታ ብቻ ነው። ከዚያ ወጭ አለባብሰው ቢይርሱ በአረም ይመለሱ ነው። የኦነግ እና ወያኔ የውሸት ለቅሶ፤ የዐብይ አህመድ ሿሿ ዘለዓለማዊ ሲዖል

Post by Abere » 24 Feb 2022, 10:18

የኢትዮጵያ ችግር የሚፈታው የአማራ ህዝብ ችግር ሲፈታ ብቻ ነው። ከዚያ ወጭ አለባብሰው ቢይርሱ በአረም ይመለሱ ነው። የኦነግ እና ወያኔ የውሸት ለቅሶ ፥ የዐብይ አህመድ ሿሿ የሁሉንም የሲዖል ጉድጓድ እያደር ጥልቅ ያደርገዋል።

ይኸ ሁሉ ከ30 አመታት በላይ ያስቆጠረ ምስቅልቅል በአማራ ህዝብ ላይ በተፈጸመ ደባ ምክንያት ነው። ለወያኔ መንከራተት እና ከአድስ አበባ መንከሳከስ ምክንያቱ ዋነኛው የአማራህብ መገፋት ነው። የአማራ ህዝብ የተለየ ፍላጎት የለውም የተለየ ግፍ ግን ይቃወማል። በትህነግ እና በኦነግ ብቸኛ መንግስትነት አማራ በማኒፌስቶ የተወገዘ፥ በህገ-መንግስት የተገለለ ብቻ ሳይሆን እንድ ገደል እንድፈናቀል እንድሸማቀቅ የተፈረደብት ህዝብ በመሆኑ ይህ ህዝብ ደግሞ በቁጥር ግዙፍ ብቻ ሳይሆን በአገራዊ ግንባታ አስተዋጽዖው ረገድም ከፍተኛ ድርሻ ያለው ነው። ይህን ህዝብ ተጭኖ ይሁን አታሎ መኖር የሚችል አንድም ሃይል የለም። ይህ እውነት ነው ኦነጋዊያን እናትህነጋዊያን ያለተረዱት - በምናብ እና ጥላቻ ብቻ ታውረው የሚኖሩት - እነርሱም እያለቁ ሌላውንም የሚያውኩት የአገር እና የትውልድ ጊዜ በከንቱ የሚያባክኑት። የሚያሳዝነው በአማራ ህዝብ ትግል ጫንቃ ስልጣን የበቃው አብይ አህመድ እንኳን በተደጋጋሚ ያሳያቸው ክህደቶች ይህን መሰረታዊ እውነት አለመቀበል መቻሉን እና እርሱም የውድቀቱን ጉድጓድ እየቆፈረ መሆኑ ነው። ማንም ሰላም የፈለገ በአማራ ጀርባ ላይ ታዝሎ ወይም ሴራ ሰርቶ ሳይሆን የአማራን ህዝብ አሳታፊ እና የአማራን ችግር የፈታ ሲሆን ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ እያንዳንዱ ሲያለቅስ ይኖራል። ወያኔ ይህን ሰምቶ በነበር አሁን ከሲዖል ጉድጓድ ውስጥ ባልጮኸ ነበር። ሲፈርድበት ትህነግ አንድ ብሎ አማራን በመጥላት እና በመግደል ትግሉን ጀመረ - ለእራሱ የሞት ፊርማውን አስቀመጠ። ትግሬ ያለ አማራ አይደለም አገር ሊመራ ጦር መርቶ አሸንፎ አይገባም።