Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: Video News Of:የክርስቲያን ታደለ እና የጋላ-ዓድዋ ፍጥጫ በፓርላማ!!! WEEY GUUD !!!

Post by Assegid S. » 22 Feb 2022, 10:42

የቀድሞ ፓርላማ ጭቅጭቅ "ዜጎች ለምን ይታሰራሉ?” በሚል ነበር፥ የዘንድሮው ፓርላማ ግን "እስረኞች ለምን ይፈታሉ?” በሚል ሀሳብ ላይ መሞገት በመቻሉ ትልቅ ዕድገት ነው … ብሎ ኣድማጭን ለማሳመን መሞከር - "ጨቅላ የህፃን አእምሮ ነው ያላችሁ" ብሎ እንደመሳደብ ይቆጠራል። ምክንያቱም፦ ቀድሞ ንፁህ ዜጋን በማሰር እና ዘንድሮ ወንጀለኛን በመፍታት መካከል ምን መሠረታዊ ልዩነት አለ? መዛኝ አእምሮ ላለው ሁለቱም ስህተትን ከማሳየት ባሻገር የመንግስትን ህዝባዊነት የጎደለው፣ ግለኝነት የሞላውን ውሳኔ እንደ በጐ ተግባር አይተረጉመውም

ለጠቅላይ ሚንስትሩ "ጦርነትን የሚመርጡት የማይጎዱት አካላት ናቸው" የሚል ድምዳሜ የሰጣቸው አእምሮ፥ ድርድርን የሚመርጡትስ በነፍስ፣ በኣካልም ሆነ በንብረት ኣንዳች ያላጎደሉት እንደሆኑ እንዴት ሰወረባቸው? ነገርን አሳምሮ ማውራት እጅግ ቀላል ነው፥ ያሳመሩትን ንግግር አሳማኝ ማድረግ ግን እጅግ ይከበዳል።

ኣራት ሰዓት ገደማ ከፈጀው ስብሰባ ውስጥ፦ ኮይሻን ጎብኙ፣ ጎርጎራን እንዳትረሱ፣ እንጦጦም እንዳያመልጣችሁ ወዘተ ከሚል የጎብኚ-አስጎብኚ ገለፃ ውጭ ምንም ረብ አልሰማሁበትም።

ከዚህ ባሻገር ግን፦ ጠቅላይ ሚንስትሩ ነገር ያሳመሩ እየመሰላቸው ምሳሌ በመጥቀስ ነገር የሚያበላሹበትን አካሔድ ለመተው ሲታገሉ ተመልክቻለሁ። ግን ምን ዋጋ አለው … በስተመጫረሻ … ወደ ግብፅ የሚወርደው ውሃ አሁን ግድቡ ስራውን ከጀመረ ቦኃላም ቢሆን መፍሰሱን አላቆመም "ያውም የሚያምር ጥርት ያለ ውሃ" ሲሉ ሳቱ እንጂ። የግብፅ ስውር ስጋት፦ እንደ ዶሮ አይን ኩልል ብሎ ጠርቶ ከደጇ የሚደርሰው የጠራ ውሃ ሳይሆን፥ እንደ ሰካራም ዓይን ድብልቅልቁ ወጥቶ ደፍርሶ የሚፈሰው ውሃ አሳፍሮ ድንበር የሚያሻግረው … ለእሸቱ ትራስ፣ ለጥጡ ምቹ ፍራሽ የሆነው ለም አፈር መቅረት እንደሆነ ዘንግተውት ይሆን?

ግን ግን … የሀገሪቱ ህገ መንግስት ማንኛውም ዜጋ (የዜጋ ስብስብ) ኣዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመስረት መብት እንደሚሰጠው ሁሉ፥ ኣዲስ ብሔር መመስረትስ ይፈቅድ ይሆን? በዛ ስብሰባ ውስጥ የኣማራው ተወካዮች ነን የሚሉትን የብኣዴን አመራርና አባሎች ስመለከት ድንገት ብልጭ ያለብኝ ከፍተኛ አምሮት ነው

ZEMEN
Member
Posts: 2493
Joined: 27 Jun 2011, 14:37

Re: Video News Of:የክርስቲያን ታደለ እና የጋላ-ዓድዋ ፍጥጫ በፓርላማ!!! WEEY GUUD !!!

Post by ZEMEN » 22 Feb 2022, 10:55

የቀድሞ ፓርላማ ጭቅጭቅ "ዜጎች ለምን ይታሰራሉ?” በሚል ነበር፥ የዘንድሮው ፓርላማ ግን "እስረኞች ለምን ይፈታሉ?” በሚል ሀሳብ ላይ መሞገት በመቻሉ ትልቅ ዕድገት ነው … ብሎ ኣድማጭን ለማሳመን መሞከር - "ጨቅላ የህፃን አእምሮ ነው ያላችሁ" ብሎ እንደመሳደብ ይቆጠራል። ምክንያቱም፦ ቀድሞ ንፁህ ዜጋን በማሰር እና ዘንድሮ ወንጀለኛን በመፍታት መካከል ምን መሠረታዊ ልዩነት አለ? መዛኝ አእምሮ ላለው ሁለቱም ስህተትን ከማሳየት ባሻገር የመንግስትን ህዝባዊነት የጎደለው፣ ግለኝነት የሞላውን ውሳኔ እንደ በጐ ተግባር አይተረጉመውም።
I am amazed by his childish and stupid explanation. he said, i realized them because for sake of lasting peace. really? only when things are done for sake of justice and the rule of law can only insure lasting peace. This guy is dangerously stupid.

tekeba
Member
Posts: 1504
Joined: 17 Dec 2013, 03:03

Re: Video News Of:የክርስቲያን ታደለ እና የጋላ-ዓድዋ ፍጥጫ በፓርላማ!!! WEEY GUUD !!!

Post by tekeba » 22 Feb 2022, 13:08

Tarik, aregit Axgame. There is no question you are on welfare and subsidized by junta, werada subhuman

Post Reply