Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11135
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ብልጽግና ያቋቋመው ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ህገ-ወጥ መሆኑ በጣም ግልጽ ነው፤ ሌላ ዋጋ ይስከፍላል።ስለዚህ ይህ ኮሚሽን መቸ፥እንደት እና እነ ማን ያቋቁሙት? የበኩለዎን ሃሳብ ስጡበት

Post by Abere » 21 Feb 2022, 12:38

ብልጽግና ያቋቋመው ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ህገ-ወጥ መሆኑ በጣም ግልጽ ነው፤ ሌላ ዋጋ ይስከፍላል።ስለዚህ ይህ ኮሚሽን መቸ፥እንደት እና እነ ማን ያቋቁሙት? የበኩለዎን ሃሳብ ስጡበት- ያለውን የወረወረ ፈሪ ወይም ንፉግ አይባልም። የእኔን ሃሳብ በአጭር ላቅርብ።

1) መቼ?

በመጀመሪያ ትህነግ ወያኔ እንደ ድርጅት ሙሉ በሙሉ መፍረስ ወይም መሸነፍ አለበት

2) እንደት?

በፓለቲካ ፓርቲነት የተደራጁ ብቻ ሳይሆኑ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ባለ ድርሻ መሆን ይገባዋል። ኮሚሽኑን የሚመርጠው አካል ገለልተኛ እና ከህዝቡ እና ተደራጅተናል ከሚሉ ፓርቲዎች እንድሁም ባለሙያዎች የተሰበሰበ እና የሁሉን ይሁንታ አግኝቶ የተመረጠ ቡድን ኮሚሽኑን ይመርጣል። ግልጽነት እና ተጠያቂነት ባለው መንገድ ለህዝብ ያሳውቃል። የስራ ድርሻውም በግልጽ በመረጡት አካላት ይደነገጋል - መራጮቹ የህዝብ የመወያያ አጀንዳ ያስጨብጣሉ። ለውይይት የሚቀርቡት አጀንዳዎች አገራዊ እና ህዝባዊ እንጅ አሁን በስልጣን ላይ ይሁን ወይም ሌሎች ፓርቲዎች ምንም አይነት አጀንዳ መስጠት አይችሉም። አገሪቱ ተፈትሾ የወደቀ መርህ ሳይሆን ሌሎች ስኬታማ የሆኑበት ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የሚሄደውን የማብላላት፥የመምረጥ እና የመወሰን አድስ እርምጃ የሚጀመርበት መሆን አለብት - የተሰበረ ፓለቲካ ጋራዥ ውስጥ ገብቶ የሚጠገንበት እና ህዝብ እንባውን ሲያፈስበት እንድኖር አይደልም።

3) እነማን?

ከዚህ በፊት በዘር ማጥፋት እንድሁም ኢሰብዐዊ ስራን በአስከፊ መልኩ የፈጸሙ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የዚህ ውይይት የተጠቃሚነት መብት የላቸውም። በሽብር እና ወንጀላቸው ምክንያት ይህን የዜግነት መብታቸውን የሞራል ህግ ይከለክላቸዋል - ምንም እንኳን አገሪቱ መልክ የያዘ ህግ ባይኖራትም። ህግ በሌለበት የሞራል ህግ እራሱ ህገ-መንግስታዊ ነው። የሞራል ህግ ልዕልና አለው። ከዚህ ውጭ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ተደራጅቶ ይሁን ሳይደራጅ የውይይቱ አካል መሆን መብት ብቻ ሳይሆን አገራዊ ግደታ አለብት።

EPRDF
Member
Posts: 2162
Joined: 26 Jan 2010, 12:58

Re: ብልጽግና ያቋቋመው ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ህገ-ወጥ መሆኑ በጣም ግልጽ ነው፤ ሌላ ዋጋ ይስከፍላል።ስለዚህ ይህ ኮሚሽን መቸ፥እንደት እና እነ ማን ያቋቁሙት? የበኩለዎን ሃሳብ ስጡበት

Post by EPRDF » 22 Feb 2022, 18:07

Abere wrote:
21 Feb 2022, 12:38

1) መቼ?

በመጀመሪያ ትህነግ ወያኔ እንደ ድርጅት ሙሉ በሙሉ መፍረስ ወይም መሸነፍ አለበት
ወንድሜ ጋሽ አብሬ፣

ሕወኃት የክልሉ ስድስት ሚልየን ሕዝብ የኣብላጫውን የድጋፍ ድምፅና ውክልና የያዘ ድርጅት ነው። አንተ ለራስህ ምክንያት ሕወኃትን ስላልወደድክ ወይም ከሕወኃት የሰፋ ልዩነት ስላለህ፣ ሕወኃት ይወገድልኝ ማለት አግባብነት የለውም፣ የሕወኃት ወይም መሰል ድርጅቶችን ማግለል የተናፈቀውን ሰላም አያስገኝም። ስለዚህ፣ በዕውነታውና በምክንያታዊነት እንጂ በስሜታዊነት ከመነዳት መታቀብ ብልሃት ይመስለኛል።
2) እንደት?

በፓለቲካ ፓርቲነት የተደራጁ ብቻ ሳይሆኑ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ባለ ድርሻ መሆን ይገባዋል......
ከላይ ቁጥር ፪ ላይ ከዘረዘርካቸው ነገሮች በአብዛኛው እስማማለሁ። የብሄራዊ ምክክር ዐዋጁም ምንም እንከን የማይወጣለት ይህንኑ መሠረታዊ የሆኑ የብሔራዊ ምክክር መርሆችን ያቀፈ ዐዋጅ ነው ከአንድ የማጭበርበርያ አንቀፅ በስተቀር።

ያም አንቀፅ፣ የጠቅላይ ሚንስትሩ ፅሕፈት ቤት የተመራጮችን ጥቆማ ይቀበላል፣ የኮሚሽኑ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር እንዲሁም የኮሚሽኑ ዓባላትን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሰየሙና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፀድቃል ይላል ጉደኛው አንቀፅ ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅሕፈት ቤትና የተወካዮች ምክር ቤት የብልፅግናዎች መናኸሪያ መሆኑን በመዘንጋት።

ብልፅግና እራሱን ከተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ አክቲቪስቶች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ የኃይማኖት ተቋማትና ታዋቂ ምሁራን ጋር በእኩል እግር በመሰለፍና ትልቅ ሸንጎ በመጥራት ነበር ኮሚሽኑንና መሪዎቹን ማሰየም የነበረበት፣ እራሱ ተጫዋችም አራጋቢና ዳኛ ለመሆን እሩጫ ግን ዓይን ያወጣ ቅጥፈት ነው።

አሁንም ብልፅግና ለተቀረው ጉዞ ቢታረም አልረፈደም፣ አይ የለም አሻፈረኝ የሚል ከሆነ እንግዲህ፣ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት፣ አካታችነት( inclusiveness) የብሔራዊ ምክክር ስኬታማነት ዋነኛው መስፈርት ሲሆን፣ ይህንን መስፈርትና የፕሮጀክቱ ዋነኛ መርህ መጣስ ማለት ደግሞ የብሔራዊ ምክክሩን ፅንስ በእንግሊዝ ጨው ማውረድ ማለት ነው።
3) እነማን?

ከዚህ በፊት በዘር ማጥፋት እንድሁም ኢሰብዐዊ ስራን በአስከፊ መልኩ የፈጸሙ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የዚህ ውይይት የተጠቃሚነት መብት የላቸውም። በሽብር እና ወንጀላቸው ምክንያት ይህን የዜግነት መብታቸውን የሞራል ህግ ይከለክላቸዋል - ምንም እንኳን አገሪቱ መልክ የያዘ ህግ ባይኖራትም። ህግ በሌለበት የሞራል ህግ እራሱ ህገ-መንግስታዊ ነው። የሞራል ህግ ልዕልና አለው። ከዚህ ውጭ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ተደራጅቶ ይሁን ሳይደራጅ የውይይቱ አካል መሆን መብት ብቻ ሳይሆን አገራዊ ግደታ አለብት።
ወደ ቁጥር ሶሶተኛው ሐሳብህ ላይ ስንመጣ፣ ዋናውና ጥንቃቄ የሚሻው ነገር፣ የኮሚሽኑ ዓባላት ከማንኛውም ወንጀል የፀዱ መሆናቸው ነው።
ከዛ በዘለል ኮሚሽኑ በወደፊት ስራው ወንጀለኞች፣ ከጌታቸው አሰፋ እስከ አባ ዱላ፣ ከደመቀ መኮንን እስከ ተፈራ ሽጉጤ፣ አቢይ አህመድን ጨምሮ እንዴት ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ አግባብ ያላውን መንገድ ያመቻቻል። የኮሚሽኑም የብሔራው ምክክርና እርቅ( national dialogue and reconciliation) ተልዕኮ መሳካት በዚያ የሚመዘን ይመስለኛል። ጤና ይስጥልኝ።

Abere
Senior Member
Posts: 11135
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ብልጽግና ያቋቋመው ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ህገ-ወጥ መሆኑ በጣም ግልጽ ነው፤ ሌላ ዋጋ ይስከፍላል።ስለዚህ ይህ ኮሚሽን መቸ፥እንደት እና እነ ማን ያቋቁሙት? የበኩለዎን ሃሳብ ስጡበት

Post by Abere » 22 Feb 2022, 18:39

እኔ በመሰረቱ ወያኔ እና ኦነግ ያወጡት ህገ-መንግስት የእነርሱ የመተዳደርያ የውስጥ ደንብ አድርጌ ነው የማየው። ስለዚህ ይህ ከስር መሰረቱ የተበላሸ ኢ-ህገ መንግስት መሪ ኮምፓስ ሊሆን አይችልም - የድርድር ኮሚሽኑን ለመምረጥ ይሁን ለማመቻቸት አያስፈልግም። አድሱን ወይን በአሮጌው አቅማዳ እንደ መቆጠር ይቆጠራል። ወንጀለኞች ለፍርድ እንጅ ለእርቅ መቅረብ አይገባቸውም።
EPRDF wrote:
22 Feb 2022, 18:07

Post Reply