Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

ብልፅግና ቢረክስ (ግጥም)

Post by kibramlak » 15 Feb 2022, 15:23

ብልፅግና ቢረክስ ቢሆን ዋጋ ቢስ፣
ስለተሞላ ነው በጎሳ አጋሰስ
በልቶ እማይጠረቃ ልክ እንደፈረስ

ነገሩ ነው እንጅ ፈረስ ምን በደለ
አለ እንጅ 4 ኪሎ የተደላደለ
ባፉ እሚሸነግል ኢትዮጵያየ እያለ
በብልፅግና ስም ሰው እየገደለ

ያገር ኢኮኖሚ ወድቆ ተንኮታኩቶ
ሰው ወጥቶ እሲኪገባ ዋስትናውን አጥቶ
ፍርደ-ገምድል በዝቶ ፍትህም ተዛብቶ
እንዲያው ታይታ ብቻ ሁሉም እንቶ ፈንቶ
... እያለ ይቀጥላል

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: ብልፅግና ቢረክስ (ግጥም)

Post by kibramlak » 15 Feb 2022, 15:47

ብልፅግና ብለው ደልለው ሰውን፣
አበለፀጉ አሉ የራስ ኪሳቸውን፣

ድንቄም ብልፅግና
ተሸክሞ መጥቶ የእልቂትን ደመና
አላራምድ ብሎ ሰውን በቁመና
መቃብር ያድሳል ሰርቆ በልመና

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: ብልፅግና ቢረክስ (ግጥም)

Post by kibramlak » 06 Mar 2022, 03:37

የጎሰኞች ምሽግ የሌቦች ቡድን፣
ለከት የጠፋበት ለሰው የማይሆን፣
በቁልቁለት አዘቅት ገፋት ኢትዮጵያን፣፣

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: ብልፅግና ቢረክስ (ግጥም)

Post by kibramlak » 06 Mar 2022, 10:01

ዘይት ጣራ ነክቶ ሲሆን እንዳልማዝ
ደልበው ብልግናዎች በህዝብ ሀብት ወዝ
ሀገር ልትፈናዳ ሆናለች እርጉዝ !

Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: ብልፅግና ቢረክስ (ግጥም)

Post by Assegid S. » 06 Mar 2022, 12:51

ሰላም Kibramlak

በግጥምህ ውስጥ የነበረውንና ኣሁን ያለውን ፖለቲካዊ እውነታ ዳሰህበታል። ኣንዳንዴ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለትግራይ የሰጡትን "የጥሞና ጊዜ" ለራሳቸውም ቢገለገሉበት ኖሮ ምንኛ መልካም ነበር እላለሁ። ሰውየው ወደ ሥልጣን በመጡ ወቅት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ከፍተኛ ድጋፍ እንደነበራቸው ማንም አይክድም። ሆኖም … በጣም ጥቂት በሚባል ዓመታት ውስጥ ግን ከነበራቸው ድጋፍ በብዙ እጥፍ የሰላ ተቃውሞና ጥላቻ ማትረፋቸው ለተመልካችም ሆነ ለወደፊቱ ታሪክ አንባቢ እጅግ የሚያስገርም ክስተት ነው። ይህ ነቀፌታና ተቃውም በሀገር ውስጥ ብቻ የተከለለ ሳይሆን ባህርና ድንበርም ይሻገራል። ትልቁ ጥያቄ ግን "ለምን?” የሚለው ይሆናል።

በእርግጥ በግጥምህ መጀመሪያ ላይ:

"ብልፅግና ቢረክስ ቢሆን ዋጋ ቢስ፣
ስለተሞላ ነው በጎሳ አጋሰስ
በልቶ እማይጠረቃ ልክ እንደፈረስ
"

ብለህ እንዳስቀመጥከው ... ለመርከሱ ምክንያት በውስጡ የተሰገሰጉት ጎሰኞች ሊሆኑ ይችላሉ። I have no doubt on that. ከዛም ባለፈ ግን ከግራ ከቀኝ፣ ከውስጥም ሆነ ከውጭ የነበራቸው ተቀባይነት እንዲህ በሚያስገርም ፍጥነት የማጣታቸው ሚስጢር የኣምላክ በትርም (ፍርድም) ነው ብዬ አስባለሁ። አለበለዚያ … የሰው ጥላቻና ተቃውሞ እንዴት እንዲህ ዘር፣ ሀይማኖት፣ ፆታና ዜግነት ሳይገድበው ኣንድ ላይ ተስማምቶ ይጋመዳል? ኣማራ ከሆዳሙ በስተቀር በኣጠቃላይ፣ ትግሬ፣ ቀላል የማይባል ቁጥር ያለው ኦሮሞ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ኦርቶዶክስ፣ ፕሮቴስታንት፣ ወንድ ፣ ሴት … ወዘተ ሁሉም ሽንገላን እንደ መዋቢያ ሸሚዝ በቆጠሩት ግለሰብ ላይ ተቆጥቷል።

No wonder … ሰውም ሆነ ኣምላክ ማስመሰልን አምርረው ይጠላሉ። መፅሐፉም ቢሆን ከኣስመሳይና ኣታላይ ይልቅ ከሀዲ ሰው የተሻለ ነው ይላል፦ ከአታላይቱ ከይሁዳ ይልቅ ከዳተኛይቱ እስራኤል ጸደቀች … ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 3 : 11

የጠቅላይ ሚንስትሩ ብልፅግና "ብልጠት" ብለው ባሰቡት የማስመሰል ብል ተበልታ አልቃለች። ከእንግዲህ ቦኃላ አይደለም ፓርቲያቸውን ቤታቸውን እንኳ በያዙት የማስመሰል ህይወት ሊታደጉት ቢችሉ በጣም ለኣጭር ጊዜ ነው። ኣምላክ ሲያነሳም ሲጥልም እንደ ህልም ነው።

እውነት ለመናገር … ሰውየው ህወሃትን በጥይት ሊያሸነፉአት ችለው ይሆናል፤ ህወሃት ግን ሰውየውን የማስመሰል ካባ አከናንባም ይሁን ገልባ በውስጥም ሆነ በውጭ በጥላቻ ክፉኛ አሸንፋቸዋለች።

Thank you again for your poem.

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: ብልፅግና ቢረክስ (ግጥም)

Post by kibramlak » 06 Mar 2022, 16:13

Selam Assegid S.

አመሰግናለሁ ፣ሰውየው እብሪት እና ማናለብኝነት አዙሪት የገባ ይመስላል፣፣ እብሪት ደግሞ ጠልፎ ይጥላል ፣፣ አንተ እንዳልከው የራሱ የጥሞና ጊዜ ቢሰጥ መልካም ነበር፣ ነገር ግን ሆ ብሎ የደገፈውን ህዝብ መልሶ ለሰቆቃ የሚዳርግ ብቸኛው ባለ ታሪክ ይሆናል ብየ አስባለሁ፣፣ እንዴ እና ሁለቴ ሰው ሊሞኝ ይችላል ከዛ በላይ ሲደጋገም ግን ይገለማል፣፣ ዛሬ በሬድዮ ምን ተብሎ ተዘገበ መሰለህ? "፣ብልፅግና በኢአዴግ ከነበረው ስርአት ስር ነቀል የፖለቲካ ለውጥ ያመጣ" እንደዚህ ይቀልዳሉ፣፣ ልክ ነው ይህ ውድቀት ባደረሰው የህዝብ በደል የተሰፈረ ቁናም ጭምር ነው
ሰላም ሁን

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: ብልፅግና ቢረክስ (ግጥም)

Post by kibramlak » 27 Mar 2022, 04:58

ቅርቃር ውስጥ ሲገባ፣ ሲገኝ አጣብቂኝ፣
እንደገና መጣ እያለ አድኑኝ፣
ከHR6600 ረቂቅ፣ ከጨምዳጁ ስንኝ፣፣

የሰራውን ሰርቶ ህዝብን አስጨርሶ፣
እንዳልሆነ አድርጎ ሀገርን አምሶ፣
ምንም እንዳልሆነ መጣ ተመልሶ፣
አድኑኝ እያለ በቃል ቀረሽ ለቅሶ፣፣

አወይ አለማፈር ውርደት አለማወቅ፣
እንዳልገባው ሳያውቅ ሲወርድ መቀመቅ፣
ከህሊና መዝገብ ከህዝብ ልብ ሲወልቅ፣
ተተፍቶ ተጠልቶ ሲታይ እንደጭራቅ፣፣

Axumezana
Senior Member
Posts: 13508
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ብልፅግና ቢረክስ (ግጥም)

Post by Axumezana » 27 Mar 2022, 09:50

የብልጽግና፥ ችግሩ፥ ከስህተቱ፥ አለመማሩ፥ አይናችሁን፥ ጨፉኑና፥ላሞኞችሁ፥ በሚል፥ ፈሊጥ፥ መመራቱ፥ በአጥፊው፥ኢሳያስ፥ፍቅር፥መነደፉና፥ የጠለፉ፥ጋብቻ፥መፈፅሙ፤ውሽትና፥ሙሱና፥ የባህሪው፥መገለጫ፥ማድረጉ፤ሁሉም፥ ችግር፥ በጉልበት፥ ወይም፥ ጉቦ፥ በመስጠት፥ ለመፍታት፥መሞከሩ፤.......፤

Post Reply