Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: ቻፓ፣ አይዞን፣ ጎተራ ባንክ፣ የዲያስፖራ ገንዘብና የሌብነት ችግር?

Post by Guest1 » 28 Jan 2022, 12:47

ድህነት በሰፈነበት አገር ጉቦ ጣሪያ በነካበት፤ ለገንዘብ ማጭበርበር፤ በገንዘብ መጭበርበር፤ በስርቆትና በህገወጥ መንገድ ራስን ለማበልጸግ መሞከር የማይቀር ነው። ደቡብ አፍሪካ፤ ናይጄሪያ እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። አስፈሪው ግን ይህ አይደለም።

ጦርነቱ አይቆምም። ብዙ ስው አልቆባቸዋል። የከፋም ነገር ሊከተላቸው ስለሚችል፤ ስጋትም ስላላቸው ይቀጥላል። ጦርነቱ በተራዘመ ቁጥር የሚፈጠረው የአገር ውስጥ ቀውስ ቀላል አይሆንም። አጥፍተህ ጥፋ ፍልስፍና ሲጨመርበት የበለጠ አስጨናቂ አሳዛኝና በርግጥም ወዴት እየሄድነው ያሰኛል። አንድ ቀን ይቆማል። እስፈሪው በዝህ መሃል እንደ ላቲን አሜሪካ የሆንን እለት ነው። ላቲን አሜሪካ ዘረፋው በጠመንጃ ነው። ለነገሩ መሃል ከተማ ዘረፋው አንዳንዴ ብቅ ብልም አሁን ዳርዳሩና ጥቅጥጉን በደንብ ተጀመሯል። የጋንግስተር ምድር እንዳትህን ፍራ! የዲያስፓራው ሌባ አያሰጋም። የዲያስፓራው ጊዜያዊ ነው። የተነቃበት ቀን ምንጩ ይደርቅበታል። የተጋለጠ እለት አይቀርለትም ይዋረዳል።

Post Reply