Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

አሸባሪዋ ህወሃት "በመንግስት" ታግቶባት የነበረው ቁጥራቸው 38 የሚሆኑ የኤፈርት ኩባንያዎችን ከአንድ አመት እገታ በኋላ ሊለቀቅላት ነው!!

Post by Wedi » 27 Jan 2022, 08:36

አሸባሪዋ ህወሃት "በመንግስት" ታግቶባት የነበረው ቁጥራቸው 38 የሚሆኑ የኤፈርት ኩባንያዎችን ከአንድ አመት እገታ በኋላ ሊለቀቅላት ነው!!
****************
የኤፈርት ኩባንያዎችን በጊዜያዊነት የሚያስተዳድረው ቦርድ ስራውን በፈቃዱ ለቆ ተበትኗል።

ጥር 19/2014
ዋዜማ ራዲዮ- የህወሓት ንብረት የሆኑንት የኤፈርት የንግድ ኩባንያዎች የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ የባንክ ሂሳባቸው ታግዶ መንግስት በሰየመው ቦርድ ሲመሩ የቆዩ ሲሆን በቅርቡ ግን ስባት አባላት ያለው ቦርድ ስራውን በፈቃዱ ለቆ ተበትኗል።

ከአንድ አመት በፊት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የትግራይ ክልልን በሚያስተዳድረው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የፌዴራል መንግስት መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ጠቅላይ አቃቤ ህግ (የአሁኑ ፍትህ ሚኒስቴር) 38 የኤፈርት ኩባንያዎች የባንክ ሂሳብ እንዲታገድ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

ኩባንያዎቹ ከህወሓት ጋር ያላቸውን የወንጀል ግንኙነት ከመመርመር ጎን ለጎንም ጉዳዩ እልባት እስኪያገኝም 38ቱ የኤፈርት ኩባንያዎች በሰባት አባላት የሚመራ ቦርድ ተቋቁሞ እንዲተዳደሩ ተደርጎ ቆይቷል።

የፌዴራል መንግስት ትግራይን ተቆጣጥሮ በቆየበትና ባለፈው አመት ሰኔ ወር ላይ ትግራይን ለቆ ከወጣ በኋላም ሆነ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የኤፈርት ኩባንያዎች ሲተዳደሩ የቆዩት በጸጋዩ በርሄ(ዶ/ር) ሰብሳቢነት በሚመራው ቦርድ ነበር።

ሆኖም ከአንድ ወር በፊት የቦርዱ አባላት መልቀቂያ በማስገባት ከኩባንያዎቹ አስተዳዳሪት መነሳታቸውን ዋዜማ ራዲዮ ሰምታለች። የቦርዱ አባላት ከሐላፊነታቸው ለመነሳት መልቀቂያ ያስገቡበትን ምክንያት ለማወቅ ያደረግነው ጥረት ግን አልተሳካም። የቦርዱ አባላት ከለቀቁም በኋላ ኩባንያዎቹ እየተመሩ ያሉት በራሳቸው ስራ አስኪያጆች ነው።

ሆኖም የፍትህ ሚኒስቴር የኤፈርት ድርጅቶች ጉዳይ ከዳር እስኪደርስ የሚያስተዳድራቸው አካል እንዲሾም ለፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ መሰረት ኮሜርሻል ኖሚኒስ የማስተዳደሩን ስራ እንዲረከብ ትእዛዝ እንደተሰጠው ዋዜማ ራዲዮ ሰምታለች።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የበላይነት የሚመራው ኮሜርሻል ኖሚኒስ የሐብት ንብረት ማስተዳደር ስራዎችን በማከናወን ይታወቃል። የኤፈርት ድርጅቶችን ለኮሜርሻል ኖሚኒስ የማረካከቡ ስራ በመጪዎቹ ሳምንታት እንደሚከናወን ተረድተናል።

በወቅቱ 38ቱ የኤፈርት ኩባንያዎች ሂሳብ ከመታገዱም ባለፈ ከኩባንያዎቱ መካከል የመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ፣የሱር ኮንስትራክሽን እና ሌሎች ኩባንያ አመራሮች ጥቅምት 24 ቀን 3013 አ.ም የመከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ በህወሓት ጦር ጥቃት ሲደርስበትም ሆነ ከዚያ በኋላ በነበረው ጦርነትም ለህወሓት ቀጥተኛ ድጋፍ አድርገዋል በሚል ወንጀል እንዲከሰሱ ተደርጓል።

የኤፈርት ኩባንያዎች ህወሓት መራሹ ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ባስተዳደረባቸው አመታት ግዙፍ የኢኮኖሚ ክንፍ እንደነበሩና ያልተገባ ትርፍ እንዲያገኙ የፖለቲካ ድጋፍ እንደነበራቸው ክስ ይቀርብባቸዋል።።

መስፍን ኢንዱስትሪያ ኢንጂነሪን ፣ ሱር ኮንስትራክሽን ፣ሳባ እምነበረድ ፣ ኢዛና ማእድን ልማት ፣ ሜጋ ማተሚያ ፣ ህይወት እርሻ ሜካናይዜሽን እና ደደቢት ብድርና ቁጠባ በሰፊው ከሚታወቁት የኤፈርት ድርጅቶች ውስጥ ይገኛሉ።

https://ethioheadline.com/2022/01/27/የኤ ... ጊዜያዊነት-የሚ/




--------------------
መንግስት ተብዬው የአሸባሪው ህወሃት ንብርቶች የሆኑትን የኢፈርት ኩባንያዎች ከአንድ አመት በፊት December 24/2020 እንዳገዱ ወስኖ የነበር መሆኑ ያወሳል!!
*******************
EFFORT Corporate Group-Board of Trustees Established

Addis Ababa, December 24/2020(ENA)

The Ministry of Finance and the Federal Attorney General have announced the establishment of the Effort Corporate Group- Board of Trustees.

The announcement was made during a press conference given by Eyob Tekalign, State Minister of Finance and Attorney General Gedion Timothewos, who explained that urgent measures were taken to restitute and ensure the resumption of the operations of the Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray (EFFORT companies) while ongoing investigations against EFFORT continue.

Explaining about the establishment of the Board of Trustees, Eyob Tekalign said the main objective of Board is to address gaps that might be caused due to the absence of leadership and to spearhead the return of EFFORT companies’ operations to normal business.

He further stated that the board is composed of 7 individuals, including those from the public and the companies themselves, and have been elected for integrity, professionalism and political impartiality.

The board members have been appointed by the Federal High Court and added that senior staff from the Ministry of Finance and the Ministry of Trade have been included as members of the board so they can bring in their expertise, it was indicated.

Furthermore, Gedion Timothewos elaborated how the Board of Trustees the corporate offices will prioritize ensuring the companies resume their functions as investigations continue.

He said these companies will focus on rehabilitating and developing Tigray region in line with their initial mission of establishment.

Chairperson of the Board of Trustees, Tsegay Berhe said for his part that the members in the past few weeks have been diligently working to develop by-laws, and assigned responsibilities.

The priority of the Board of Trustees will be to ensure that employees of the companies can resume their work. Accordingly, he said the board will commence its work immediately.

Hawzen
Member+
Posts: 7274
Joined: 07 Jun 2012, 05:03

Re: አሸባሪዋ ህወሃት "በመንግስት" ታግቶባት የነበረው ቁጥራቸው 38 የሚሆኑ የኤፈርት ኩባንያዎችን ከአንድ አመት እገታ በኋላ ሊለቀቅላት ነው!!

Post by Hawzen » 27 Jan 2022, 19:05


Can you tell or show us where exactly in the news it backs your claim that "አሸባሪዋ ህወሃት "በመንግስት" ታግቶባት የነበረው ቁጥራቸው 38 የሚሆኑ የኤፈርት ኩባንያዎችን ከአንድ አመት እገታ በኋላ ሊለቀቅላት ነው!!" ??????

I am waiting ...... :roll: :roll: :roll: :roll:

Dedebit is always dedeb
R.I.P Abay Tigray and TPLF terrorist group

Post Reply