Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

በኦሮሚያ ክልል ስምንት ዞኖች በተከሰተው ድርቅ ከ800 ሺ በላይ ሰዎች ለተረጂነት ተጋልጠዋል EBC

Post by sarcasm » 26 Jan 2022, 10:01

******************
በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ስምንት ዞኖች በዝናብ እጥረት በተከሰተው ድርቅ ምክንያት 800ሺ 244 ሰዎች ለተረጂነት መጋለጣቸውን የኦሮሚያ አደጋ ስጋትና ልማት ተነሺዎች አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ በመኖ እጥረት ምክንያት ከብቶች እየሞቱ መሆኑን ገልጿል።
ኦሮሚያ አደጋ ሥጋትና ልማት ተነሺዎች አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙስጠፋ ከድር ጉዳዩን አስመልክተው ለኢትዮጵያ ፕሬስ እንደገለጹት፤ በዝናብ እጥረት ምክንያት በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ስምንት ዞኖች በተከሰተው ድርቅ 800 ሺህ 244 ሰዎች ለተረጂነት ተጋልጠዋል።
እንደ ኮሚሽነር ሙስጠፋ ገለጻ፣ ድርቁ ለሶስት ወራት እንደሚቆይ ተረጋግጧል።

መንግሥት የሰውን ሕይወት ከማዳን ጎን ለጎን በድርቁ ምክንያት ከብቶች እንዳይሞቱ እየሰራ ቢገኝም ከ6 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ እንስሳት መኖ ማቅረብ በመንግሥት አቅም ብቻ የሚቻል ባለመሆኑ ችግሩ ኣሳሳቢ መሆኑን ጠቁመዋል።

መንግሥት ችግሩን ለመፍታት የተለያዩ መፍትሄዎችን ወስዷል። እስካሁን ድረስ የሰውን ሕይወት ለማዳን 197 ሺ 896 ኩንታል እህል በድርቅ ለተጎዳው ለቦረና ዞን ብቻ እንዲደርስ ተደርጓል።
በአጠቃላይ የመኖ ችግር ለመፍታት 507 ሺህ 151 ቤል ሣር (በማሽን የሚታሰር የእንስሳት መኖ) እና የውሃ ችግር ለመፍታት ከተለያዩ ተቋማትና ባለሀብቶች ጋር በመተባበር 96 ቦቴዎችን ማቅረብ ተችሏል።

ኮሚሽነር ሙስጠፋ እንዳብራሩት እስካሁን በተደረገው ምልከታ ድርቁ ለሶስት ወራት እንደሚቆይ የደመናው ሸፋን ያሳያል።
በመሆኑም ድርቁ በእንስሳት ላይ የከፋ ጉዳት እንዳስከትል በኦሮሚያ የሚገኙ 21 ዞኖች እና 18 ከተሞች የድርሻቸውን መኖ (ሣር) በማምረት እንዲያግዙ በክልሉ መንግሥት አቅጣጫ ተቀምጧል።
በተጨማሪም በድርቁ ምክንያት ለከፋ አደጋ የተጋለጡትን እንስሳት ወደ አጎራባች ዞኖች በማዘዋወር ማሰጠለል እንደ ተጨማሪ መፍትሔ ተወስዷል።
በዝናብ እጥረት ምክንያት ድርቅ በተከሰተባቸው ስምንት ዞኖች በተጨማሪ በሰላምና ጸጥታ ችግር ምክንያት ለተረጂነት የተጋለጡ 4 ሚሊዮን 976 ሽህ 981 ሰዎች እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን አያይዘው ገልጸዋል።
መንግሥት እነዚህን ዜጎች ለመታደግ 1 ሚሊዮን 587 ሺህ 694 እህል እገዛ አድርጓል።
እህል ማድረስ በማይቻልባቸው አካባቢዎች 51 ሚሊዮን 755 ሺህ ብር በጥሬ ገንዘብ እንዲከፈላቸሳ ተደርጓል።
ችግሩ በመንግሥት አቅም ብቻ የሚቀረፍ ባለመሆኑ ባለሀብቱ፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የእንስሳት መኖ በማምረትና በማጓጓዝ እንንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች በተረጅነት ስር የወደቁ ዜጎችን በመ,ደገፍ የድርሻቸውን እንዲወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።
Please wait, video is loading...