አጀንዳ አንድ፤ ሕዝብ፣ አገር፣ መንግስት
(1) የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲባል መስማማት፤
(2) የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰንደቅ አላማ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ መሆኑን መወሰን፤ ሌሎች ሰንደቆች የግል፣ የፓርቲ፣ የሪጅን፣ የቤተ እምነት ያሻቸውን ምልክት ማውለብለብ እንዲችሉ መስማማት፤
(3) የጎሳ ክልሎች በመልካምድር ክልል መለወጥ፤
(4) በጎሳ ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ አደረጃጀት በሕግ መከልከል፣ ከፖለቲካ ውጭ ሰዎች በፈለጉት ሲቪል መደራጀት እንደ ሚችሉ መስማማት
(5) የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ኮንትራት የጎሳ ስምምነት ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ሉዓላዊ ግለሰብ ያቆሙት እንደሆነ መስማማጥ
(6) አንቀጽ 39 ን መሰረዝ
(7) የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም ከጎሳ ፌዴሬሽን ወደ ኢጎሳዊ እስትራክቸር መለወጥ፣ አስፈላጊ ከሆነ የባህልና ቋንቋ የበታች ምክር ቤት ለብቻ መፍጠር
(8) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፌዴራል ተቋማት መከላከያ፣ ፖሊስ፣ ሴኩሪቲ፣ ልዩ ሃይሎች፣ ሚኒስቴሮች፣ ሹመቶች ሁሉ ከጎሳ ኮታ ቀመር ተወግደው በክህሎትና ሜሪት መሰረት ማቋቋም
(9) የክልል ጦር ሃይሎች ሁሉ ወደ ፌዴራል መከላከያ ተዋህደው፣ እንደ ኢትዮጵያ ሰራዊት አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ መስማማት።
አጀንዳ ሁለት፤ ዴማክራሲ፣ ነጻነት፣ ፍትህ
(1) ኤትኖክራሲ ተሽሮ በዴሞክራሲ ለመተካት መስማማት፤
አጀንዳ ሶስት ፤ የመሬት ስሪት
(2) የመሬት ጥያቄን ላንዴም ለሁሌም መፍታት፣ የመሬት ስሪት ከጎሳ ባላባትነት አስወግዶ የግልና የሕዝብ ስሪት መለወጥ፤
አጀንዳ አራት፤ ቋንቋ፣ ባህልና እምነት
(1) መንግስት ከሃይማኖት ውጭ ማድረግ
(2) የቤተ እምነቶች መሬት ይዞታን መፍታት
(3) እያንዳንዱ ጎሳ ቋንቋውና ባህሉን እንዲያሳድግ መተው
(4) ፌዴራል መንግስት መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እሴት ለሆኑ ካልቸራል አሴትና አሴቶች ብሄራዊ ድጋፍ እንዲሰጥ መስማማት ።
በቃ ከሞላ ጎደል እነዚህ ናቸው የብሄራዊ ወይይቱ አጀንዳዎች!
ሆረስ ነኝ