Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 10889
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

<ጦርነት አልቋል፤አቁመናል> ብልፅግና <የቂላቂል ቀልድ፤እኛ አላቆምንም።ፋሽሽት ዐብይ አህመድ ስለ ፈራ እና ስለተጨነቀ ብቻ አቆሜያሁ ይበል ። > ትህነግ

Post by Abere » 24 Jan 2022, 11:48

<ጦርነት አልቋል፤አቁመናል> ብልፅግና <የቂላቂል ቀልድ፤እኛ አላቆምንም።ፋሽሽት ዐብይ አህመድ ስለ ፈራ እና ስለተጨነቀ ብቻ አቆሜያሁ ይበል ። > ትህነግ

ትህነግ ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ የህልውና ስጋት መሆኑ እየታወቀ፥ መንግስት ተብየው ያዝ ለቀቅ እያደረገ የሰው ህይወት እንደ ቀላል በነጻ ያበላሻል። ትህነግ ሙሉ በሙሉ ያለ አቅም ተጠቅሞ ከምድረ ገጽ እንደማጥፋት አንድ ጊዜ ሽብርተኛ ተብሎ ይታወጅበታል፥ሌላ ጊዜ ደግሞ ተደራዳሪ የጠረንጴዛ ዙርያ ጓደኛ ይደረጋል- በብልጽግና። ይኸ ሁሉ የሚሆነው በነጻ የንጹሃን ደም እና ህይወት ነው። በስንት ሽዎች ኢትዮጵያዊያን መስዋዕትነት (እንደ እንቦሳ ጥጃ በመንግስት ተባባሪነት ከኮረም ደብረሲና ተለቆ የፈነጠዘው ወያኔ) ተሸንፎ ተግርፎ ከወሎ እና ሰሜን ሸዋ ከተባረረ በኋላ የብልጽግናው መሪ በእራሳቸው ፈቃድ ጦርነት አቆምን ከእንግድህ ከእነስብሃት ጋር ውይይት ልንጀምር ነው አሉን። ውሸታቸው በዚህ አላቆመም የአፍሪካ መንግስታት ስብሃት ነጋ ካልተፈታልን አዲስ አበባ ስብሰባ አናደርግም ሌላ አገር መቀመጫ እናደርጋለን ብለው ትልቅ ውሸት ጎመዱልን። በእውነት ስብሃት ነጋ የአፍሪካ ህብረት መስራች መካከል አንዱ አይደለም። ስብሃት አንድ ተራ የፍየል እረኛ ከዚህ ግባ የማይባል ሽፍታ በመጨረሻም በስርቆት የአንድ አገር ህዝብ ኢኮኖሚ በግል ሂሳብ ደብተሩ ያስቀመጠ፥የሚልዮኖች ህይወት ያስቀጠፈ ወንጀለኛ። ግርም የሚለው የአፍርካ ህብረት ለዚህ ተራ ሰው ምን ጉዳየ ብሎ ነው - በጎ እድርጎት ተዋቂ ሰው አይደል፤ በታዋቂ አህጉራዊ ሽምግልና ዝነኛ አይደል፤ ተራ የፍየል ጠባቂ ሰው ነው። ዐብይ አህመድ ግን እርሱን ባንፈታ ብዙ እናጣ ነበር ብሎት አረፈ። ይፈታ ያሉት እነርሱም ሌባ መሆን አለባቸው ማለት ነው።

--ወደ ዋናው ነጥብ ስመለስ። አቁምናል፤ጦርነቱን በበላይነት አሸንፈናል ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ፡ ውሸት ነው ወያኔ ተመልሶ ይመጣል መከላከያን ገና ያንከሳክሰዋል ብለን ነበር። እንዳልነውም ይኸው አሁን ያን የፈረደበትን የወሎ ህዝብ ድጋሜ በሰፊው በመውረር ላይ ነው። ፋኖ እግር በእግር እያባረርነው መቀሌ እንግባ ሲል አይሆንም ተብሎ ከዚያም ይባስ መሳሪያ ፍቱ ቤታችሁ ግቡ ተባሉ - ገብተው ሳይጨርሱ ወያኔ አሁን ወሎ እና አፋርን ወራለች። በእርግጥ አፋር እና ጎንደር ላይ መከላከያ 100% ሃይሉን ስለሚጠቀም ወያኔ አይሳካላትም። ያው በመንግስት ለወያኔ የተሰጣት ሂሳብ ማወራረጃ የወሎ ቤተ-አማራ ነው። 2ኛው ምፅዐተ ጥፍት ለወሎ ህዝብ ተጀምሯል። ለማንኛውም የወሎ ቤተ-አማራ እራስህን ከበፊቱ በተሻለ ጠብቅ - የብልጽግና መከላከያ እና ጠባቂዎችን አትመናቸው። ደግመው ደጋግመው በቢላዎ ደንደስህን አርደውሃል። ግብር ትከፍላለህ እንጅ አንተ የምትጠበቅበት መሳርያ ገዘተው አንተን አይጠብቁም ሲፈልጉ አንተን ይገድሉበታል ሳይፈልጉ ለወያኔ ያከፋፍላሉ - ሁሉም አንተን ለማጥፋት ነው።

Abere
Senior Member
Posts: 10889
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: <ጦርነት አልቋል፤አቁመናል> ብልፅግና <የቂላቂል ቀልድ፤እኛ አላቆምንም።ፋሽሽት ዐብይ አህመድ ስለ ፈራ እና ስለተጨነቀ ብቻ አቆሜያሁ ይበል ። > ትህነግ

Post by Abere » 25 Jan 2022, 10:34

መቸም የዐደባባዩ በጆሮ ሆነ እንጅ፤ ብርሃኑ ጁላ (የማዕረግ ኪራይ ሰብሳቢው ፊልድ ማርሻል) በጓሮ በር ከእነ ጌታቸው ረዳ እና ደብረጽዮን ጋር በመተባበር የአፋር እና አማራ ህዝብን ድጋሜ በማጥቃት ስራ ላይ ተጠምዷል እየተባለ ነው። ለመሆኑ ደግሞ ሌላ የወታደር የማዕረግ ደረጃ ይኖር ይሆን? ግፍ አይሆንም ወይ መቶ ሺዎችን ድጋሜ ለማስጨረስ ሌላ ሴራ ማራመድ። በመሰረቱ የአሁኑ የኦሮሙማ ብልጽግና እና ትህነግ ድብቅ ሽርክና ለኢትዮጵያ ህዝብ ትህነግ ለድርድር ጫና እያሳደረ ነው የሚል የተሳሳተ መልዕክት ለማስተላለፍ ነው። መቼም ብልጥ ኦሮሙማ ብቻ ነው። ስብሃት ነጋን የተፈታው የአፍሪካ ህብረት እርሱ ካልተፈታ እኛ አዲስ አበባ አንሰበሰብም ስለአሉ ነው ተብላናል እኮ iii :lol: ስብሃት ብሎ ሰው አፍሪካዊ ተፅእኖ ፈጣሪ :lol: የአፍሪካ አባት :mrgreen: የኦሮሙማ ገልቱዎች እነርሱ ብቻ አሪፎች ናቸው። ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል ይባላል - የወደቀ ህዝብ አግኝተው ልዩ ላይ ውሸት ይሸኑበታል።

ለማንኛውም ይህ አሁን የ3ኛው ዙር የወያኔ ጦርነት እንደ በፊተኞቹ ሁሉ የሽርክና ጦርነት ነው። በተጭበረበረ ጦርነት የህይወት መስዋዕትነት መክፈል ያለ አግባብ ነው። የጦርነቱን አላማ እና ግብ መወሰን ያለበት የአፋር እና አማራ ህዝብ እንጅ አዲስ አበባ የተቀመጠው የስልጣን እና ማዕረግ ኪራይ ሰብሳቢው ኦሮሙማ ብልጽግና መሆን አይገባው። የአማራ ህዝብ በተለይ በጥንቃቄ ማየት ያለበት ከፊቱ ገጥሞ የሚዋጋው ወያኔ እና ከኋላው በደፈጣ እና ተንኮል የሚወጋው ኦሮሙማ መከላከያ መሆኑን ነው። እየተዋጋህ ያለኸው በእራስህ መሬት ላይ ከትህነግ እና ኦነግ ጋር ነው ማለት ነው። ጣምራ ጥላት ገጥሞሃል። ለአፍታም ቢሆን አሁን ያለውን መንግስት ነኝ የሚልህን አሸባሪ እና አጭበርባሪ ቡድን ልታምነው አይገባም።

Post Reply