Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 33231
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

^^^{{{JUST IN}}}^^^Video News Of:አሸባሪው ሕወሓት በድጋሚ በአፋር ክልል ጦርነት መክፈቱን የክልሉ መንግስት አስታውቋል!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 24 Jan 2022, 10:36


----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/
1473ughShp60om9511og6ed ·
አሸባሪው ሕወሓት በአፋር ክልል በኪልበቲ ረሱ ዞን ጦርነት ከፈተ
*********************
(ኢ ፕ ድ)

አሸባሪው ሕወሓት በአፋር ክልል ውስጥ ገብቶ የደረሰበትን ሽንፈት ለማካካስ አሁንም በኪልበቲ ረሱ ዞን ጦርነት መክፈቱን የክልሉ መንግስት አስታውቋል፡፡

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የሽብር ቡድኑ በአፋር ክልል በኪልበቲ ረሱ ዞን በኩል በአብአላና በመጋሌ ወረዳ የከፈተውን ውጊያ አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል፡፡

ምንም አይነት ሰብዓዊነትና ርህራሄ ፈፅሞ የሌለው አሸባሪ ቡድኑ በንፁሀን ዜጎች ላይ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ እያሸበረ ይገኛል ነው ያለው መግለጫው፡፡

ሁሌም ከትንኮሳ አርፎ የማያውቀው የሽብር ቡድኑ ለዘመናት የቆየውን በድንበር የሚዋሰኑ የአፋር እና የትግራይ ክልሎች ህዝቦችን ግንኙነት ከምንም ሳይቆጥረው ሁለቱን ህዝቦች በማጋጨት የማይረባ ትርፍ ለማግኘት ሌት ተቀን እየጣረ ይገኛል፤ እያደረሰ ባለው ጥቃትም የአፋር ንፁሃን ኢላማ በማድረግ የሽብር ተግባሩን በማስፋት ላይ ነው ብሏል፡፡

በዛሬው እለት እንኳን በኪልበቲ ረሱ ዞን በተለያዩ ቦታዎች የአፋር ክልልን ወሰን ጥሶ በመግባት በአብአላ፣ በመጋሌ እና በበራህሌ በኩል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት በመክፈት በርካታ ንፁሃንን ለጉዳት ዳርጓልም ነው ያለው መግለጫው።

ይሁንና ሁሌም በማጭበርበርና በውሸት ፕሮፓጋንዳ እድሜውን የሚያራዝመው ጁንታው በአፋር ክልል በተለያዩ ወረዳዎች በኩል ዘልቆ በመግባት ንፁሀንን የጎዳ ቢሆንም ጥቃት እንደተፈፀመበት አስመስሎ በማቅረብ አሁንም ማደናገሪያውን እየነዛ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

አሸባሪው ሕወሓት በአራት ዞኖች ውስጥ በ21 ወረዳዎች ወረራ በማካሄድ የአፋር ህዝብን በአሰቃቂ ሁኔታ ቢጨፈጭፍም በብዙ ቢሊየኖች የሚገመት ሀብት ንበረት ቢያወድምም፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ እንዲሰደድ ቢያደርግም ለጎረቤት ትግራይ ህዝብ ሰብዓዊነት ሲባል እርዳታ በአፋር አብአላ በኩል እንዲያልፍ እየተደረገ ነበር ብሏል።

ጁንታው ለትግራይ ሕዝብ እንኳን ምንም አይነት ርህራሄ እና ሀዘኔታ የሌለው በመሆኑ በዚሁ ቀጠና ግጭት በመፍጠር አካባቢው የግጭት ቀጠና እንዲሆን እና ሰብአዊ እርዳታ እንዳያልፍ ማድረጉ በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

የትግራይ ሕዝብም የዚህን አሸባሪው ሕወሓት እብደት በቃህ ሊል ይገባል፣ በግልፅ እየወጣ ያለውን ሴራውን እና ተንኮሉን በመረዳት ከሕዝብ የሚበልጥ የለምና እንደ ሕዝብ ሊቃወም ግድ ይላል፤ በውሸት ማወናበጃው ፈፅሞ ባለመታለል ለጥቂት የቡድኑ አባላት ጥቅም ሲባል የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን መገበር አይገባቸውም ነው ያለው መግለጫው።

በአፋር በተለያዩ አካባቢዎች ወረራ አካሂዶ በሁሉም ግንባሮች ሽንፈትን አስተናግዶ የወጣው አሸባሪው ሕወሓት አሁንም እንደ አዲስ በኪልበቲ ረሱ (ዞን) በኩል በከፈታቸው ግንባሮች የምድር ድሮኖቹ አስፈላጊውን መከታና ማጥቃት በማካሄድ የጁንታውን እብደት የሚያመክኑ በመሆኑ አሸባሪው ቡድን ዘልቆ ገብቶ ለመውረር ያስገባውን ሀይሉን አስቀድሞ ሊያወጣ ይገባል ሲል አሳስቧል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን ‼
ዩቲዩብ 👇
https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
ቴሌግራም 👇
https://t.me/ethpress
ትዊተር 👇
https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ 👇
https://www.press.et/ See less