Page 1 of 1

Shocking: የክልል መለያ ከተሽከርካሪዎች ሠሌዳ ተሰርዞ በ "እምዬ ኢትዮጵያ " ታርጋ ሊተካ ነው

Posted: 23 Jan 2022, 12:32
by Thomas H



Esayas Hailemariam
4h ·
የፌደራሊዚም መቋጫ: አሃዳዊ (ወጥ) የመኪና ታርጋ::
አሃዳዊው የፋሺስት አብይ ስርኣት፣ አሁን በስራ ላይ ያለው የክልሎችን ስም የያዘውን የመኪና ታርጋ በማንሳት ወጥ "እምዬ" ታርጋ ለመቀየር ረቂቅ አዋጅ ወደ ሕገ-ወጡ ፓርላማ መርቷል። የታርጋው መቀየር ጉዳያችን ባይሆንም፤ የአንድ ቡድን አግላይ-ጠቅላይ የቅኝ ግዛት ደባ ያልገባቸው ወይም ገብቷቸው አንገታቸውን ደፍተው የሚገዙት ብሄር ብሄረሰቦች ከ እንቅልፋቸው እንዲነቁ የመጨርሻ ደወል ለማሰማት ነው።
አሜሪካ ውስጥ፣ ሁሉም ስቴቶች (ክልሎች) በራሳቸው ስም የተሰየመ የመኪና ታርጋ ሲኖራቸው፣ ዩ.ኤስ.ኤ (USA) የተጨመረበትን ብቸኛ ታርጋ የምትጠቀመው ኒው ሜክሲኮ (New Mexico state) ብቻ ነች (ከ ሀገረ ሜክሲኮ ጋር እንዳይምታታ)።