Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12606
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

African Insider: ኢትዮጵያ ወታደሮቿ በትግራይ ጦርነት አልቀው አሁን አዲስ መከላከያ መገንባት ልትጀምር ነው

Post by Thomas H » 21 Jan 2022, 09:57

ማለዳ Media
51m ·
በሁመራ መስመር ከ30ሺህ የሚልቅ ቁጥር ያለው የኤርትራ ሠራዊት መስፈሩ ተነገረ
**********
የአብይ አህመድ መንግስት ከመከላከያ ሠራዊቱና የክልል ተዋጊዎችን ጨምሮ ወደ 400,000 ተዋጊዎችን በትግራይ ጦርነት እንዳጣ ከአዲስ አበባ ወታደራዊ ምንጮች ማግኘቱን ያተተው አፍሪካ ኢንሳይደር ባለፈው ወር አብይ አህመድ የሁመራ መስመር ተጋላጭነት በመስጋት የኤርትራ መከላከያ ሀይል መስመሩን እንዲቆጣጠረው ጥያቄ ማቅረቡን ይፋ አድርጓል።
በዚህ መሠረት አሁን በሁመራ መስመር ሁለት መካናይዝድ እና ሶስት እግረኛ ጦር፡ በድምሩ ከ30 ሺህ የላቀ ቁጥር ያለው የኤርትራ ሠራዊት ሰፍሮ እንደሚገኝ አፍሪካ ኢንሳይደር ከአዲስ አበባ ምንጮች ማረጋገጥ ችሏል።
ማለዳ ሚዲያ