Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Dawi
Member
Posts: 4311
Joined: 30 Aug 2016, 03:47

አዲሱ የአሜሪካ ስልት በአፍሪካ ቀንድ | የዐብይን መንግስት ከኤርትራ መነጠል | Eritrea/Somalia are considered "UNCOLONIZED" under Ethiopia's shadow

Post by Dawi » 20 Jan 2022, 04:40

"Eritrea/Somalia are considered "UNCOLONIZED" under Ethiopia's shadow!"

You can say that again! :P

Eritreans have proven that during the past Ethiopia's anti colonial struggles and the present internal war VS terrorist TPLF. #




[[ ጥሩ አረዳድ ነው። ነገርግን በደንብ ብታዩት የምለው ጉዳይ አለ። የአሜሪካ አካሄድ የዐብይን መንግስት ከኤርትራ መነጠል ብቻ አይመስለኝም ። የዐብይን መንግስት ከህዝብ ፣ በተለይም ከአማራ የማጋጨት ዓላማም የያዘ ይመስለኛል። ዐብይ የአማራን ድጋፍ ካጣ ወይ ፍፁም የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ ይሆናል ወይም በአጭር ግዜ ይወድቃል ። ይህንን ታሳቢ ያደረገ ትንተና ያስፈልጋል ። እንደ ኤርትራ ሁሉ በዚህ ቁማር ውስጥ ሌላው በደንብ መጤን ያለበት የአማራው ተፅዕኖ ነው። ብአዴን ወይም ብልፅግና ውስጥ ያለውን ካድሬ ሳይሆን የአማራን እውነተኛ ጥያቄዎች የሚያንፀባርቁ ኃይሎች ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብና ከኤርትራ ጋር ግንባር ቢፈጥሩ በህወሃትና ኦነግ ላይ የተመሰረተውን የአሁኑን የአሜሪካ ስሌት ምን ችግር ሊፈጥሩበት ይችላሉ በተለይም ቻይናና ሩስያ በአካባቢው ካላቸው ፍላጎት አንፃር የሚለውንም ብታዩት መልካም ነው።]]

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: አዲሱ የአሜሪካ ስልት በአፍሪካ ቀንድ | የዐብይን መንግስት ከኤርትራ መነጠል | Eritrea/Somalia are considered "UNCOLONIZED" under Ethiopia's sh

Post by kibramlak » 20 Jan 2022, 09:43

አብይ ከአሜሪካ ጋር የፈጠረው ስውር ግንኙነት እና በቅርቡ ሰፊውን ህዝብ ያስቆጥ ውሳኔ መውሰዱ ፣ ከዛም አልፎ የአማራውን ህዝብ ለማስፈራራት የሚያደርገው ሙከራ በአንድ ላይ ሲታይ፣ ሴረኛው አብይ ወደ አሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚነት እየሄደ ሊሆን ይችላል ለማለት ያሰኛል፣፣ መቸም የህውሀት እስረኞች በሱ ምኞት አልተፈቱም፣፣ በአደባባይ የሚያወራው ሁሉ ፍፁም ውሸታም መሆኑን እየተጋለጠ ለመሆኑ የራሱ የተጣረሱ ንግግሮች እና ተግባሮች ማጣቀሻ ይሆናሉ፣፣

እንደዛ ከሆነ የህውሀትን ቦታ ተክቶ ከአሜሪካኖች ጋር ይሰራል ማለት ነው፣፣ ልክ እንደ ህውሀት እሱም የምዕራባውያን ድጋፍ ይዞ አንባገነናዊ ስርአቱን ለመቀጠል ይሞክራል ፣፣ ይህ ግን ብዙም ዘላቂ አይሆንም ፣፣ የሁለቱን አገዛዝ (ህውሀት እና የሱ የጎሳ ቁማር) ግፍ ተቀባይ ስለሚሆን ፣፣

Post Reply