Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 11124
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ --ከዓለም በፊት ቀድማ ሰንደቅ ዓላማ የነበራት አገር ኢትዮጵያ ስትሆን ፤ በአሁን ዘመን በዓለም ላይ ሰንደቅ ዓላማ የሌላት በቸኛ አገር ደግሞ ኢትዮጵያ ናት።

Post by Abere » 18 Jan 2022, 17:18

ፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ --ከዓለም በፊት ቀድማ ሰንደቅ ዓላማ የነበራት አገር ኢትዮጵያ ስትሆን ፤ በአሁን ዘመን በዓለም ላይ ሰንደቅ ዓላማ የሌላት በቸኛ አገር ደግሞ ኢትዮጵያ ናት። ይህ ግራ የተጋባ ትውልድ አገር እና የስነ-ልቦና ስሪት አልባ የውሃ ላይ ኩበት ሁኗል። በጋብቻው የሚደምቅበት፤ በሞት ጊዜ በክብረ-ሞገስ የሚጎናጸፈው ሰንደቅ ዓላማ የለውም። በልመና ስንዴ ተረግዞ፥ በልመና ስንደ አድጎ በዚሁ በልመና ስንደ እና ውራጅ ጨረቅ ጎልምሶ የልጅ ልጅ አይቶ በድህነት ተጨማዶ በመጨረሻም አስከሬኑ እንኳን ለብሶ የሚሸኝበት ሰንደቅ ዓላማ የለውም። የዚህ አይነት ትውልድ ባይረገዝ እና ባይፈጠር ይመረጣል። ምድር እራሷ ምነው ወደዚህ አለም መጣህብኝ ትለዋለች። ክብረ-ዐልባ ትውልድ መብቱን አያውቅ ስለመብቱ አይሟገት ስለ ውርስ ባህል ትውፊቱ አይመራመር - እርሱን ያገኘው ሁሉ በቀሰም ይነፋዋል።