Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

አብይ አህመድ ደም አፋሳሹን ጦርነት ለማስቆም የተለየ ግዴታ አለበት ሲል የሠላም ኖቤል ሽልማት ኮሚቴ አስታወቀ። - ማለዳ ሚዲያ

Post by sarcasm » 16 Jan 2022, 21:24

አብይ አህመድ ደም አፋሳሹን ጦርነት ለማስቆም የተለየ ግዴታ አለበት ሲል የሠላም ኖቤል ሽልማት ኮሚቴ አስታወቀ።
**********


እ.አ.አ በ2019 ለአብይ አህመድ የሠላም ኖቤል ሽልማት ያበረከተው ተቋም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራዩን ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማስቆም የተለየ ግዴታ እንዳለበት ገልጿል።

የኮሚቴው ሊቀመንበር የሆኑት ቤሪት ሪስ አንደርሰን፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ አገሪቱ መሪ እና የሠላም ሽልማት አሸናፊ ጦርነቱን የማስቆም የተለየ ግዴታ አለበት ብለዋል።
አንደርሰን፣ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ተደራሽነት እጅግ አሳሳቢ ነው። እርዳታ በበቂ ሁኔታ እየደረሰ አይደለም። ይህ ተቀባይነት የለውም ሲሉ አክለዋል።

የሂውማን ራይት ዎች ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ከኔዝ ሮዝ በበኩላቸው አብይ አህመድ ሠብአዊ እርዳታ እንዳይደርስ በመዝጋት እየወሰዱ ያሉት እርምጃ የጅምላ ቅጣት ዓይነተኛ ምሳሌ ነው በማለት አብይ እየቀጣ ያለው የትግራይን ህዝብ እንጂ ሠራዊቱን እንዳልሆነ ተናግረዋል። የዘገበው AFP ነው።

ማለዳ ሚዲያ
Please wait, video is loading...