Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Assegid S.
Member
Posts: 593
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

የሳምንቱ ስልኬ XII

Post by Assegid S. » 16 Jan 2022, 09:57

https://www.eaglewingss.com/የሳምንቱ ስልኬ XII

ጤና ይስጥልኝ

አብሮ ይስጠን ሰውየው … ምነው ጠፋህ?

ጠፋሁ አይደል? … በኣንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ገድላለሁ ብዬ ነበር፤ ግን ባየው ባየው የሚሆን ስላልመሰለኝ፥ ሁለቱም ወፎች ሳይበሩ ብዬ ይኸው ተከሰትኩ

ትንሽ በተን አድርገው እስቲ

ጠቅላይ ሚንስትሩ እንደ አርተፊሻሉ ዝናብ ሹመት ሲያዘንቡ ተምልክቼ፥ ለፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የዘነበ ለአንተም ያካፋል ብዬ ጠብቄ ነበር። ያው ዘግየት ብዬ ደውዬ "እንደምን ሰንብተሃል?” ብቻ ሳይሆን "እንኳን ደስ አለህ!" ጭምር ለማለት

ቂል ነህ ልበል?

በል … ግን እኔም "እንዴት?" ልበል?

ወታደር እኮ የሚኖረውም የሚሞተውም ለህዝብ እንጂ ለኣንድ መሪ አይደለም። ስለዚህ የወታደርን የአገልግሎት ዋጋ መተመንም ሆነ መክፈል ያለበት የህዝብ ህሊና ነው። ህዝብ ሥራህን መዝኖ – "ይገባዋል!” ብሎ ካልፈረደ፥ ማንም ተነስቶ "ጥቁር ኣንበሳ" “ነጭ ዝሆን" እያለ ደረት - ትከሻህን በቁራጭ ጨርቅ ቢያስጌጠው፥ ተገልብጦ ከውጭ የተሰፋ ተራ የልብስ tag ከመሆን ባለፈ ምን ጥቅም አለውና ነው ... ብሸለም ... "እንኳ ደስ አለህ!" ልትለኝ የምታስበው? ህዝብ ያልተቀበለው የወታደር ሹመት ... ልክ እንደ ነጠላ ጥለት ልብስ ማድመቂያ እንጂ ጅብዱ መግለጫ - ሞራል ማሞቂያ እንደማይሆን አታውቅም?

በል በል ፊልድ ማርሻሉ ሰምተው ሸዋ ሮቢት field እንዳትወጣ

ሸዋ ሮቢት … ቂሊንጦ … የፈለጉት ቦታ ቢወስዱኝ እውነቱ ይኸው ነው። ህዝብ አምኖ ካልሰጠህ፥ መሪ እንድታምነው የሚሰጥህ የወታደር ማዕረግ እንደ ብጫቂ  garment label  የልብሱን ስሪት እንጂ የለባሹን ሥራ የማሳየት ጉልበት የለውም። ያልተገባ የወታደር ማዕረግ ውበቱ ለልብሱ እንጂ ለለባሹ ከንቱ ሸክም ነው፤ ምክንያቱም ሹመት ስልጣን እንጂ ዕውቀት አይደለምና

ምን ኣይነት የክት ትርክት ይዘህብን መጣህ ደግሞ?

ይኼ የክት ትርክት ሳይሆን የአዘቦት ዕውነት ነው። ኣንድ ባለስልጣን ካልተመቸህ ሹመቱን ነጥቀህ ተራ ሠራተኛ ልታደርገው ትችላለህ፤ ልክ ኣንድን ጄነራል ማዕረጉን ገፈህ ተራ ወታደር ልታደርገው እንደምትችል ማለት ነው። ኣንድን ምሁር ግን ቢመችህም ባይመችህም ዕውቀቱን ነጥቀህ ልታደድበው አትችልም

ቆይ ... ወታደሮቹ ሹመት አይገባቸውም ነበር ነው የምትለኝ?

አልወጣኝም

እና ታዲያ?

ሹመቱ መሰጠት የነበረበት ለተራ ወታደሩ፦ የመድፉን ጩኸት፣ የክላሹን ፉጨት በቅርብ ሜዳው ላይ ለሰማው እንጂ በ40 እና 50 ኪሜ ርቀት ላይ ሆኖ "ሽሽ!” እያለ ሲሸሽ አምሽቶ ኣዲስ አበባ ለገባው መሆን አልነበረበትም ነው የምልህ

አሁን ገባኝ፤ አዛዦቹ ዕድገት አይገባቸውም ባይ ነህ

አዎ! እነሱን ከፈለጉ ጠቅላይ ሚንስትሩ በዕድገትም ይሁን በክህደት ወደ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያዛውሯቸው። ሯጮቹን ያሰልጥኑ። ለነገሩ እሳቸውም ቢዛወሩ ጥሩ ነበር። ወራሪን በአስወራሪ እንዴት ትዋጋዋለህ?

በቃ ተግባብተናል፤ ሀሳቤን አንስቻለሁ

Good. ጥሩ ጓደኛዬ ከሆንክ፦ ከጠቅላይ ሚንስትሩ የትከሻ ማዕረግ ሳይሆን ከኣንዱ በጎ አሳቢ ተራ ክራቫት እንድሸለም ተመኝልኝ

ኧረ በሚገባ! ግዛልኝ አትበለኝ እንጂ ለምኞት ለምኞትማ ክራቫት አይደለም ሙሉ ሱፍ ነው የምመኝልህ

እየቀለድክ ነው?

ለምን እቀልዳለሁ?

ታዲያ እንዴት ነው ሱፍ መብላት በከበደበት ሀገር ሱፍ መልበስ የምትመኝልኝ? ማን ተርፎት ነው የሚያለብሰኝ?

በጣም ይቅርታ! ከኣንድ ሚልዮን በላይ ዲያስፖራ ገብቷል ስትሉ ኢኮኖሚው ትንሽ ነፍስ ዘርቷል ብዬ በማሰብ ነው እንጂ ለቀልድ አልነበረም

እዋይ! አለ ተክላይ። ዲያስፖራው ኢኮኖሚው ላይ ነፍስ ሊዘራ አይደለም ለእራሱም ነፍስ-ግቢ ነፍስ-ውጪ ላይ ነው

ምነው ? ኮሮና ነው?

ኮሮናማ ቢሆን ታሞ በዳነ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ "ና ግባ" ብለው … እንደ ገና ኳስ በዋዜማው በዱላ አንክተው አንክተው ዘረሩት እንጂ

lol … እስረኞቹን ፈተው ነው?

እስረኛማ ጊዜውን ጠብቆ ይፈታል፤ ደንብ ነው። ገዳዮቹን ለቀው በል እንጂ

እንደዚህ ነው አየህ፦ በትንቢት መንገስ ትዕቢተኛ ያደርጋል፤ ህዝብን ያስንቃል። ኣንድ መሪ ከእግዚአብሔር የተላኩ ነኝ ብሎ ሲያስብ አገዛዙ ፍፁም መስሎ ስለሚሰማው በዙሪያው ላለ ድምፅ ጆሮውን ይዘጋል። እርሱ የነካው ሙጃ ... አገዳ፣ ቅጠሉ … ጐመን የሚሆን ስለሚመስለው የሰውን ስሜትና ፍላጎት ለማወቅ አይፈቅድም። አሁንም የሆነው ይህ ነው። ይብላኝ እንጂ ለእርሳቸው … .

ለእኛ በል እንጂ ፤ ከዛሬ ነገ ይሻላል ብለን ስናስብ ጉድ ለተሰራነው። ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ ብለን ዝም ብንል ጭራሽ ጭራውን አቁሞ አይጠ-ሞገጡ መጣ። ደግሞ "ለሀገር ሰላምና ዕድገት ሲባል የተወሰደ እርምጃ ነው" ይባልልኛል። ለሀገር ሰላምና ዕድገት ከታሰበ'ኮ መሪው መጠየቅ ያለበት "ባላገሩ ምን ይላል?” ብሎ እንጂ "ባይደን ምን ይፈልጋል?” ብሎ አልነበረም

ለዛ እኮ ነው … ይብላኝ ለእርሳቸው ያልኩህ። ሀገርህን አርክሰህ ባዕዱን በማዋደድ መንግስትህን የምታፀና ከመሰለህ የዋህ ነህ። የኣንድ አገዛዝ መውደቅ ወይንም መቆም ዕድል ፈንታ የሚወሰነው በምዕራቡ ዓለም ጫጫታ ሳይሆን በህዝቡ ፍቅርና አመኔታ እንደሆነ አሜሪካ ጥግ ሄደን ኩባን፣ አፍሪካ ጫፍ ተጉዘን ዝምባብዌን መመልከት አያስፈልገንም፥ እዚሁ አፍንጫችን ስር ያለቸው ኤርትራ ምስክር ናት። እነርሱም ብልጦች ናቸው ይህን ስለሚያውቁ፥ ሊያጠቁህ ሲፈልጉ መጀመሪያ ከህዝብህ ይነጥሉሀል። እባብ የሆነውን የምዕራቡን ዓለም ያስደሰተውም የእስረኞቹ መፈታት ሳይሆን የጠቅላይ ሚንስትሩ ከብዙ ደጋፊያቸው መፋታት ነው

ያም ቢሆን ለምን "ይብላኝ ለእርሳቸው" ብዬ እኔ እበላለሁ? ሲፈልጉ እራሳቸው ይበሉ እንጂ

ሎል ... ማን ይበላቸዋል ብለህ ነው? ህወሃት?

ምናልባት

አትሳሳት! በዘር ደም ስር ለተወሰወሰ ዘረኛ ፍጡር ሺ ጊዜ ብትጣፍጥ ማስቲካ እንጂ ማር አትሆንም፤ አኝኮ ይተፋሃል እንጂ አላምጦ አይውጥህም። ጠቅላይ ሚንስትሩ ዝም ብለው ነው የደከሙት። ቅኔው ከገባህ 8)

ቅኔውንማ "ህወሃትን በገንዘብ ቀየርነው" ብለው በ 21ኛው ክፍለ ዘመን ወደ "ባሪያ ንግድ" ላሸጋገሩን የመንግስት ደላሎች (ፈንጋዮች) ትተነዋል

ምነው? በእስረኞቹ ሽያጭ በቅርቡ ይገዛል የተባለው "ትልቅ" የሀገር ብልፅግና አልተዋጠልህም?

"ብልፅግና" ነው ያልከው?

አዎ፤ ብልፅግና ... ኣዲስ ምዕራፍ … ማማ …ከፍታ … Pan African-ism … ስንቱን ልዘርዝርልህ

ማን ነበር "የምትበላው የላት … የምትከናነበው አማራት" ያለው?

ያ ተረትማ ዱሮ ቀረ። አሁን "የምትበላው የላት … የተከናነበችውን መሳደብ አማራት" ሆኗል የሚባለው

ማለት?

ባዶ ሆዳን እየተንከባለለች "ፎጣ ለባሽ" ብላ የምትጮህ አላጋጠመችህም?

lol በል ደህና ሰንብት። መጠፋፋት ያረሳሳል ... አስብበት

እሺ አልጠፋም። መልካም ሰንብት

sarcasm
Member+
Posts: 6890
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: የሳምንቱ ስልኬ XII

Post by sarcasm » 16 Jan 2022, 11:30

Assegid S. wrote:
16 Jan 2022, 09:57
የኣንድ አገዛዝ መውደቅ ወይንም መቆም ዕድል ፈንታ የሚወሰነው በምዕራቡ ዓለም ጫጫታ ሳይሆን በህዝቡ ፍቅርና አመኔታ እንደሆነ አሜሪካ ጥግ ሄደን ኩባን፣ አፍሪካ ጫፍ ተጉዘን ዝምባብዌን መመልከት አያስፈልገንም፥ እዚሁ አፍንጫችን ስር ያለቸው ኤርትራ ምስክር ናት።
Thanks Assegid. A really good satire. Let's hope that people in authority do not take Isaias's Eritrea, Castro's Cuba and Mugabe's Zimbabwe as role models of የህዝብ ፍቅርና አመኔታ. Because they are not examples የህዝብ ፍቅርና አመኔታ. Why would over 100k Eritrean's (out of 3.5ml) risk their lives to cross the border in order to to live in refugee camps in Tigray than live in their villages 10s of kilometers away if the relationship between the people and the government is full of የህዝብ ፍቅርና አመኔታ?

I don't think Ethiopians struggled the EPRDF government because they wanted the government / people relationships and economies of Cuba, Eritrea and Zimbabwe. I thought they wanted the economic development brought by EPRDF but they were not happy with the lack of democratic governance. So what Abiy had to do was to keep the pace of the economic growth and work on democratic governance. ፩ ሺ ግዜ "ኢትዮጵያ አትፈርስም" ብሎ ፈክሮ፤ አፍርሷት አረፈው። ሊያፈርሳት እየሰራ እንደነበር ህሊናው ከድቶት ይሆን?

Assegid S.
Member
Posts: 593
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የሳምንቱ ስልኬ XII

Post by Assegid S. » 16 Jan 2022, 15:33

sarcasm wrote:
16 Jan 2022, 11:30

Hello Sarcasm; thanks a lot for the comment. I do see your point but still I believe that the mass exodus in Cuba, Zimbabwe and/or Eritrea is exogenic and deliberately cased by the so called “world powers.” Owing to some unjustified sanctions imposed on these countries, we have seen hyperinflation rates hitting 600% … and even above that led to abandonment of the currency. They do so to alienate the administration from its people. Only then it would be easy for them to topple the local gov’t.

You know that people must secure at least the basic needs in order to survive. Therefore, it is natural to migrate when there is a shortage of resource / basic needs. That is the core reason behind this migration you pointed out, shortage of RESOURCE, not lack of LOVE to their gov’t or country. Otherwise; why do they go back or invest in their “villages” once they attained what they aimed for?

Yet; it doesn’t mean that you are absolutely wrong to challenge me as there are a number of individuals that fled from their homeland for hating the gov’t (for some sort of political or social persecution.) We're live witnesses for that.

በተረፈ ግን "፩ ሺ ግዜ "ኢትዮጵያ አትፈርስም" ብሎ ፈክሮ፤ አፍርሷት አረፈው።" ለሚለው … ኢትዮዽያን ከመፍረስ ለማዳን ሰፊ ዕድል እንዳለ ቢሰማኝም፥ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ስራና ፀባይ ግን "ኢትዮዽያ አትፈርስም!” ብዬ ምድር ላይ እየዳኸ የማየውን አደጋና ስጋት በባዶ ስልጣን፣ በኣጉል ጀብዱ ላቃልለው አልፈቅድም። ከዚህም ሲያልፍ … እኔም አንተም የመጣነው "ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል" ብሎ ከሚተርት ማህበረሰብ ነው።

Stay Safe, Sarcasm.

sarcasm
Member+
Posts: 6890
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: የሳምንቱ ስልኬ XII

Post by sarcasm » 16 Jan 2022, 19:23

Assegid S. wrote:
16 Jan 2022, 15:33
በተረፈ ግን "፩ ሺ ግዜ "ኢትዮጵያ አትፈርስም" ብሎ ፈክሮ፤ አፍርሷት አረፈው።" ለሚለው … ኢትዮዽያን ከመፍረስ ለማዳን ሰፊ ዕድል እንዳለ ቢሰማኝም፥ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ስራና ፀባይ ግን "ኢትዮዽያ አትፈርስም!” ብዬ ምድር ላይ እየዳኸ የማየውን አደጋና ስጋት በባዶ ስልጣን፣ በኣጉል ጀብዱ ላቃልለው አልፈቅድም። ከዚህም ሲያልፍ … እኔም አንተም የመጣነው "ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል" ብሎ ከሚተርት ማህበረሰብ ነው።
You must be optimist. ትዳሩማ ፈርሷል, I think. ፍቺው ግን ገና ግዜ ይወስዳል። Let's hope the divorce is done in a thought out process similar to the UK / EU divorce.

Abere
Member+
Posts: 5126
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የሳምንቱ ስልኬ XII

Post by Abere » 16 Jan 2022, 19:55

የወልቃይቴ ባህላዊ ሽለላ:-

እንረስ ካላችሁ - ተስማምተን እንረስ፤
አናረስም ካልችሁ -ተውት ዳዋ ይልበስ።

የራያ ኮረም ኮረዳ ብዙም ለማትጨነቅለት ጉዳይ በእንጉርጉሮ:-

ወዘፍዘፍ ያለ ነው የግራር አጥር፤
እኔ ለጅል ፍቅር እምብዛም አልጥር።

Meleket
Member
Posts: 1463
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የሳምንቱ ስልኬ XII

Post by Meleket » 17 Jan 2022, 09:33

ወዪ የሳምንቱ ስልክህ ገራሚ እውነታዎችን ኣፍረጥርጧል፤ የተባረከ አእምሮና ብዕር!!!! :mrgreen:
Assegid S. wrote:
16 Jan 2022, 09:57
https://www.eaglewingss.com/
ወታደር እኮ የሚኖረውም የሚሞተውም ለህዝብ እንጂ ለኣንድ መሪ አይደለም። ስለዚህ የወታደርን የአገልግሎት ዋጋ መተመንም ሆነ መክፈል ያለበት የህዝብ ህሊና ነው። ህዝብ ሥራህን መዝኖ – "ይገባዋል!” ብሎ ካልፈረደ፥ ማንም ተነስቶ "ጥቁር ኣንበሳ" “ነጭ ዝሆን" እያለ ደረት - ትከሻህን በቁራጭ ጨርቅ ቢያስጌጠው፥ ተገልብጦ ከውጭ የተሰፋ ተራ የልብስ tag ከመሆን ባለፈ ምን ጥቅም አለውና ነው ... ብሸለም ... "እንኳ ደስ አለህ!" ልትለኝ የምታስበው? ህዝብ ያልተቀበለው የወታደር ሹመት ... ልክ እንደ ነጠላ ጥለት ልብስ ማድመቂያ እንጂ ጅብዱ መግለጫ - ሞራል ማሞቂያ እንደማይሆን አታውቅም?
. . .
ሹመት ስልጣን እንጂ ዕውቀት አይደለም።
. . .

Assegid S.
Member
Posts: 593
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የሳምንቱ ስልኬ XII

Post by Assegid S. » 17 Jan 2022, 14:20

sarcasm wrote:
16 Jan 2022, 19:23
You must be optimist. ትዳሩማ ፈርሷል, I think. ፍቺው ግን ገና ግዜ ይወስዳል። Let's hope the divorce is done in a thought out process similar to the UK / EU divorce.
Hello Sarcasm; thanks again for the comment. አሁን ባለው ሁኔታ ፍቺ የለም። እኔ የማየው ተፋቺ በሌለበት ብዙ የሚደክሙ አፋቺዎችን ነው። በእርግጥ ከፍተኛ የሆነ ቅያሜና ኩርፊያ አለ። ያንን ለማፅዳት ደግሞ ከፖለቲከኞቹ በላይ ብዙ ሚና ሊሰጣቸውና ሊጫወቱ የሚገባቸው የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጎ አሳቢ ተማሪዎች መሆን ይኖርባቸዋል ባይ ነኝ። Have a nice weekdays, Brother.

Assegid S.
Member
Posts: 593
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የሳምንቱ ስልኬ XII

Post by Assegid S. » 17 Jan 2022, 14:31

Meleket wrote:
17 Jan 2022, 09:33
ወዪ የሳምንቱ ስልክህ ገራሚ እውነታዎችን ኣፍረጥርጧል፤ የተባረከ አእምሮና ብዕር!!!! :mrgreen:

Hello Meleket; thank you so much for your encouraging comment. I do really appreciate your constructive participation here. You always hearten people to live up to their top value. That's what I see in your comments on different threads. Thanks again Meleket. Wish you a nice weekdays, Brother.

Assegid S.
Member
Posts: 593
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የሳምንቱ ስልኬ XII

Post by Assegid S. » 17 Jan 2022, 14:46

Abere wrote:
16 Jan 2022, 19:55
የወልቃይቴ ባህላዊ ሽለላ:-

እንረስ ካላችሁ - ተስማምተን እንረስ፤
አናረስም ካልችሁ -ተውት ዳዋ ይልበስ።

የራያ ኮረም ኮረዳ ብዙም ለማትጨነቅለት ጉዳይ በእንጉርጉሮ:-

ወዘፍዘፍ ያለ ነው የግራር አጥር፤
እኔ ለጅል ፍቅር እምብዛም አልጥር።
Hello Abere;
ድሮ ድሮ "ዳዋ" ሲባል የእንስሳ ዘር ይመስለኝ ነበር። ምክንያቱም፦ "ድመት በበላ ዳዋ ተመታ " ሲባል ስለምሰማ። አሁን ግን ካልተሳሳትኩ ጫካ መሳይ የእሾህ፣ ኣረም፣ ወዘተ ስብስብ መሰለኝ። እውነት ለመናገር "ወዘፍዘፍ" የሚለውን ቃል ለመተርጎም ግን አሁንም እቸገራለሁ 8) Have a nice weekdays, Brother.

Post Reply