Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abe Abraham
Senior Member
Posts: 14412
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

የቅዳሜ-እሁድ(ቀዳመ-ሰንበት) ጨወታ !! የቓራቖሽ ፍርድ/ሑክም ቓራቖሽ !!!!

Post by Abe Abraham » 15 Jan 2022, 04:29


  • ኣቡ ሰዒድ ቓራቖሽ ቢን ዓብደላ ኣል-ኣሰዲ በ በሃእ ኣል-ዲን የሚታወቀው በየሰላሕ ኣል-ዲን ኣል-ኣዩቢ (የኩርድ ተወላጅ) ዘመን የግብጽ ገዢ የነበረ ሰው ነው ። ስለ ኣገዛዙ ብዙ ነገር ይነገራል ። ጥሩው መጥፎውና የተጋነነው !!

    ወቅታዊ የሱዳን ሁኔታ ለመከታተል ባለፉት 5 ቀናት ኣንድ በፓሪስ የሚኖር የሱዳን የፖለቲካ ነጣፊ ( ናሽጥ/ኣክቲቪስት ) በዩትዩብ ስከታተል እሱ የሱዳን ያሁኑ ኣመራሩና ኣካሄድ ደስ ስላላለው " ይሄ ሑክም ቓራቖሽ/ የቓራቖሽ ፍርድ " ነው ብሎ ወደ ኣንዲት ተረት-ተረት የላም በረት የምትመስል ትረካው ገባ ። ስውየው ምን ይላል ?

    በዘመነ ቓራቖሽ ኣንድ በገመድ ተንጠንጥሎ ታንቆ ሊሞት የተበየነበት ሰው ወደ ጉዳዩን የሚፈጸምበት ቦታ ተወስዶ - ከህዝብ ብዙ ተመልኻቾች የመጡበት - ቁመቱ እጅግ ኣጭር ስለ ነበረ የተመኮረ ቢሞከር በተዘጋጀው ገመዱ ከፍታ ሊደርስ ስለ ኣልቻለ ቓራቖሽ ጉዳዩ ስለ ኣላስደሰተው ቆይ ብሉ በኣጭሩ ሰው ምትክ ኣጠገቡ ቆሞ የነበረውን ረዘም ያለ ሰው ኣቅርበው ፍርዱን እንዲፈጽሙ ኣዘዛቸው ። ሆነ ደሞ ረጅሙ በርዝመቱ ሞት ተፈርዶበት ሂወቱን ኣጣ ። ስለዚ ኣረቦች " ሑክም ቓረቖሽ " ሲያነሱ ደረት የለሽ በደልና መጠን የለሽ ኢ-ፍትሃዊነት ሲያዩና ሲሰማቸው ማለት ነው ።

    ፋኖ ትጥቁን ማውረድ ኣለበት ሲባል ሑክም ቓራቖሽ ነው ለማለት ይቻላል ወይ ? ፍርዱ ለናንተ ይሁን!!