Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ጎሳ፡ ያላዋቂዎች የዉሸት አምላክ!

Post by Horus » 14 Jan 2022, 14:09

ጎሳ የሚባለው የዉሸት እግዚአብሄር

ድፍን አራት የኢትዮጵያ ትውልዶች ከዘመነ ሃይለ ስላሤ እስከ ዘመነ አቢይ አህመድ ያሉት ዛሬ ተመልሰው አንድ ሆነዋል! ዛሬ በሙሉ ድፍረትና ኩራት ማለት የሚቻለው ቃል ኢትዮጵያ የሚባለው ዘላለማዊና የሰው ልጅ ቅርስ የሆነው ሃሳብና ማህበር ነው ።

እስቲ በጥሞና ለ50 እና ለ60 የብሄር ጥያቄ ላይ የሞቱት እስከ 1 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች፤ ለ60 አመታት በብሄር ጥያቄ ላይ የወደመ የሰው ሃይል፣ የቁስ እና የቴክኖሎጂ፣ የሰው እስኪል፣ እና ሃብት በስንት ትሪሊዮን እንደ ሚለካ አስቡት ። ለ60 አመታት ሳይሰራ የቀረው እድገት፣ ከጥቅም ውጭ ሆኖ ሞቶ የበሰበሰው የሰው እውቀትና ክህሎት እስቲ አስቡት!

ዛሬ ላይ ቆመን ያለፈውን ዘመነ ብክነትና እና ዘመነ እብደት ብናጤን አንድ ግልጽና ነዋሪ ፋይዳዊ ለውጥና እድገት መሬት ላራሹ መደረጉ ብቻ ነው። ሌላው በሙሉ ባዶ ነገር ነው ። ዛሬ አራት የኢትዮጵያ ትውልዶች ተዋህደው አንድ የኢትዮጵያ አጀንዳ ሲዘምሩ ለማንም ምንግዜም ግልጽ ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ በብሄር ጥያቄ የጭለማና መድረሻ አልባ ሃሳብ ፋይዳ ቢስነት፣ አውዳሚነት፣ ጎታችነት እና ሲብስበትም እብደት መሆኑን ነው።

ለዚህ ሁሉ የመጨረሻው ግዙፍ ምሳሌ በትግሬ ህዝብ ላይ ላለፉት 50 አመታት የሰፈነው ጭለማና የደረሰው ሰቆቃ ነው ። አንድም የኢትዮጵያ ጎሳ የትም የሄደ የትም የደረሰ የለም፤ እዚያው ሰቆቃው ውሰጥ ነው የሚማቅቀው! በብሄር ጥያቄ አራት ትውልድ ያስፈጁት ብሄረተኞች ምን አተረፉ? ህዝባቸው ምን እድገት ላይ ደረሰ?

ከወሎ ረሃብ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ትግሬ በልመና ስንዴ ነው የሚማቅቀው! ይህን አስቦ የማያፍር የትግሬ ልሂቅ እንዴት ሊኖር ይችላል? ይህ የጭለማ ጉዞ ሄዶ ሄዶ አሁን ትግራይ ትስዕር ለሚባል ትርጉሙን እንኳ ለማያውቁት ቃል እንደ ቆሻሻ በየሙጃው ውስጥ የቀረው ስንት የትግሬ ጨቅላ አንጎል ነው? ትስዕር ፣ ስርዕየት ፣ መሰረዝ ከአንድ ነገር ነጻ መሆን የሃጢያታችን መሰረዝ ማለት ነው እንጂ ማሽረንፈ ማለት አይደለም! የትግሬ ሕዝብ በመቶ ሺዎች የሚሞተው ትርጉሙን እንኳ ለማያወቀ ቃል ነው! ከዚህ የላቀ ስካርና እብደት ምን አለ!

የብሄር ጥያቄ የሚባል የደንቆሮ ዘፈን እና ነጻ አውጪ ጦርነት የሚባል ስካር ባይኖር የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዛሬ የት በደረሱ!

ለምሳሌ አሜሪካንን ተመልከቱ ለ75 አመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ሲባክኑ ይህን ሲረዱ ያንን ሲከዱ ዛሬ ሃ ብለው ከኢትዮጵያ ጋራ መጀምር አለባቸው!
ግዜ ሁሉን ነገር ይበላል! ግዜ የሁሉም ነገር ድክመትና ውድቀት እንደ ብርሃን ፍንትው አድርጎ ያሳየናል ! ግዜ አይዋሽም ! ግዜ አያዳላም!

ገና የብርሃን መወለድ ነው። ብርሃን እውቀት ነው። እውቀት እውነትን ከዉሸት የመለየት ብቃትና ስጦታ ነው።ስህተት ማለት አንድ የያዝነው እውነት (እምነት) ዉሸት ሆኖ ሲገኝ ነው። ለምሳሌ የብሄር ጥያቄ እንደ እውነት ያመንነው ዉሸት ነው ። የብሄር ጥያቄ ዉሸት ነው። የብሄር ጥያቄ የሚባል እወት የለም ። ይህን ዉሸት ነው ዛሬ በአዲስ ብርሃን፣ በአዲስ እውቀት መታረም ያለበት ግዙፍ፣ እጅግ ግዙፍ የርዕዮት፣ የሃሳብ፣ የእምነት፣ የካልቸርና የፖለቲካ ቀውስ! ይህ ጉዳይ አንድ የዶክቶራል ዲሰርቴሽን ሳይሆን አስር መጻህፍት ይወጣዋል። ለምሳሌ ...

(1) በትግሬ የመጀምሪያው ወያነ አመጽ ስንት ትግሬ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?
(2) በመንግስቱ ነዋይ መፈንቅለ መንግስት ስንት አዋቂ፣ ምሁርና ወታደር ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?
(3) በሁለቱ የሱማሌ ጦርነቶች ስንት ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?
(4) ለ30 አመት በተካሄደው የኤርትራ ነጻነት ጦርነት ስንት ሰው፣ ስንት ምሁር ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?
(5) ከሜጫ ቱለማ ማህበር እስከ ዋቆ ጎቱ እስከ ኦነግና ቄሮ ስንት ስንት ወጣት፣ ስንት አዋቂ፣ ስንት ምሁር ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?
(6) ከየካቲት አብዮት እስከ ደርግ መፍረስ ስንት ብርቅዬ የኢትዮጵያ ወጣት፣ ልሂቅ፣ ምሁር፣ መሪ ሞተ(1) በትግሬ የመጀምሪያው ወያነ አመጽ ስንት ትግሬ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?
(7) ከ1975 እስከ ዛሬ 2022 በትግሬ በቀጠለው አላማ ቢስ ጦርነት ስንት ወጣት፣ ወንድ ሴት፣ ምሁር፣ ጨዋ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?
(8) በባድመ ጦርነት ስንት ሰው ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?
(9) የትግሬ የዘር አገዛዝ ስልጣን ከያዘበት 1990 እስከ ዛሬ 2022 ድረስ በመላ ኢትዮጵያ በጎሳ፣ በክልል፣ በዘር፣ በቋንቋ ሳቢያ ስንት ሚሊዮን ሕዝብ ተፈናቀለ፣ ተሰደደ፣ ተበተነ፣ ደሀየ፣ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?
(10) ከ1960ው የመንግስቱ ነዋይ መፈንቅል ጀምሮ እስከ አሁኑ 2022 ቅጽበት ድረስ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ተሰደደ፣ በረሃ በላው፣ ዉሃ በላው፣ በሽፍታ ተገደለ፣ አካሉ ተሸጠ፣ ስንት ወጣት ሴት በስደር ተደፈረች፣ ሞተት፣ ሞተ? ስንት ንብረት ወደመ? ያ ሁሉ ህይወት፣ እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት እድገት ላይ ቢውል ውጤቱ ምን ይሆን ነበር?
(11) ከ1960 እስከ ዛሬ 2022 ድረስ ኢትዮጵያ ስንት መቶ ሺ ምናልባት ሚሊዮን የተማረ፣ የሰለጠነ የሰው ሃይሏ ወደ ውጭ ፈልሶ በአንጎል ሽሽት (ብሬይን ድሬይን) ተበላ? ያ ሁሉ እውቀትና ክህሎት ኢትዮጵያ ላለፉት 60 አመት ተጠቅማ ቢሆን ዛሬ ምን እንደርስ ነበር?

እነዚህና መሰል እንቅልፍ ነሺ ጥያቂዎችን የማያነሳ የዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊ ምሁር ገና የሪያሊቲ ንቃተ ህሊና ደረሰ ለማለት አይቻልም!

በትክክል አንድ የታሪክ ተማሪ ወይም ተመራማሪ እነዚህ 11 የታሪክ ኩነቶችን በትንሹም ቢሆን አጥንቶ...
(1) የሞተው ሰው ቁጥር
(2) የቆሰለው ሰው ቁጥር
(3) በሰው መሞትና መቁሰል የተጎዱት ቤተሰቦች ቁጥር
(4) የወደመው የሰው ሃይል ልክ
(5) የወደመው የእውቀት መጠን
(6) የወደመው የአዋቂዎች፣ ምሁራን፣ጥበበኞች ልምድ መጠን በአመታት ቢለካ (measured in years of experience)
(7) እነዚህን ጦርነቶች ላይ የወደመው ግዜ እድገት ላይ ባለመዋሉ የጠፋው እድል (opportunity cost)
(8) እነዚህ ጦርነቶች እና ውደመቶች ተከትሎ የተከሰተው ድህነት፣ በሽታ፣ የሳይኮሎጂ ቀውስ፣ሌሎች የተከፈሉ እዳዎች
እና ሌሎችም እንደ ስዕል የሚያሳይ ጥናት መደረግ ይኖርበታል ። ይህ እስካልሆነ ድረስ ሕዝባችንም በጭለማ ውስጥ ይኖራል ፣ ከታሪካችንም ምንም ነገር ሳንማር ያንኑ ስህተት ስንደግም እነኖራለን !

በ. አ. (ሆረስ)
Last edited by Horus on 14 Jan 2022, 14:50, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ETHNICITY: THE FALSE GOD OF THE IGNORANT

Post by Horus » 14 Jan 2022, 14:46

የአንድ ታላቅ አገር ተባያት ምንድን ናቸው?

1. የሕዝብ አንድነት
2. ጠምካራ መንግስት
3. ጠንካራ ጦር
4. ጠምካራ ኢኮኖሚ
5. መረጋጋት
6. ነጻነት
7. ፍትሃዊነት
8. ብልጽግና
9. እውቀት
10. ፈጠራ
11. እርቅ
12. ክብረ ህይወት
13. ባለአደራነት
14. እዝነት
15. መንፈሳዊነት
16. ሞራልዊነት
17. መልካምነት

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰዋስው

የጥቅሞች ዝርዝር
• የኢትዮጵያ ጥቅም፤ ይህ የኢትዮጵያ አጀንዳ የሚባለው ነው ። ኢትዮጵያን የአፍሪካ መሪ፣ የቀጠናችን ሃያል አገር፣ ብሄራዊ አንድነት፣ ጠንካራ መንግስት፣ ጠንካራ የጦር ሃይል፣ ዴሞክራሳዊ፣ የበለጸገች አገር ፣ ወዘተ ያካተተ ነው የኢትዮጵያ አጀንዳ።
• የመንግስት ስልጣን ላይ ያሉት ፓርቲዎች ወይም የነሱ የስልጣን ጥቅም ነው። ስለዚህ አቢይ ስልጣኑን በሌላ ስልጣን ፈላጊ ላለመነጠቅ መታገሉ የእሱን ክፉነት የሚያሳይ ሳይሆን የፖለቲካ ሳይንስ ህግ ነው ።
• የልዩ ልዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥቅም
• የህዝብ የጋራ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጥቅም
• የኦርቶዶክስ፣ የሙስሊምና የቴንጤዎች ጥቅም
• የትግሬ ጥቅም
• የአማራ ወልቃይትና ራያ ትቅም
• የልዩ ልዩ ጎሳዎች ክልል ጥቅም
• የአሜሪካ ጥቅም
• የቻይና ጥቅም
• የአውሮፓ ጥቅም
• የቱርክ ጥቅም
• የአረቦች ጥቅም
• የግብጽ ጥቅም
• የቀጠናው አገሮች ጥቅም
• የዲያስፖራ ጥቅም

የኢትዮጵያ ፖለቲካ የነዚህ ሁሉ ሰዋስው ነው ። በትንሹ እነዚህ 15 የጥቅም ቡድኖች የኢትዮጵያን ፖለቲካ በራሳቸው መነጽርና ከራሳቸው ጥቅም አንጻር ብቻ ሲመለከቱ ሁሉም እርስ በርስ የሚጋጩ፣ የሚቃረኑ ነገሮች ስለሆኑ እያንዳንዱ ቡድን ተነስቶ የእኔ ጥቅም ነው ከሁሉም የላቀውና ትክክል ቢል ትርፉ ቀውስ ብቻ ነው ። ይህን የእኔ ብቻ፣ እኔ ነኝ ባለጉልበት ወዘተ ትግሬዎች ሞክረውት ብዙ ደምና ሃብት አባክነው አሁን ወደ ምድራዊ ሃቅ እየወረዱ ነው ። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰዋስው እየገባቸው ነው ።

እኔ አሁን ባለው የአቢይ መንግስትም ሆነ ሌሎች ትላልቅ የፖለቲካ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚ ክስተቶችን ስናስተውል ቆም ብለን ምን ላይ ቆመን ነው ይህን የፖለቲካ ስዕል የምናየው እያልን መጠየቅና ማሰብ አለብን። ሁልግዜ ትክክለኛ አቋምና መልስ ላይ የሚወስደን ዘዴ የኢትዮጵያ ጥቅም፣ የኢትዮጵያ አጀንዳ፣ የኢትዮጵያ ፐርፐዝ መነጽር ነው!

የትግሉ ተዋንያን አሜሪካ ሆነ ቻይና፣ ቱርክ ሆነ ግብጽ፣ አማራ ሆነ ትግሬ፣ ኦሮሞ ሆነ ሱማሌ። ኤርትራ ሆነች ሱዳን ... ሁልግዜ መጠየቅ ያለብን ይህ ክስተት፣ ይህ ፖሊሲ፣ ይህ እርምጃ ለኢትዮጵያ አጀንዳ ምን ፋይዳ አለው ብለን እንጠይቅ!

ኢትዮጵያን አንድ ያደርጋል ወይስ ይከፋፍላል?
ኢትዮጵያን ያጠነክራል ወይስ ያዳክማል?
አገራችንን ያረጋጋል ወይስ ያቃውሳል?
ዴሞክራሳዊ ነው ወይስ አምባገነናዊ?
ፍትሃዊ ነው ወይስ ኢፍትሃዊ?
ሕዝባችንን ያበለጽጋል ወይስ ያደህይል?
ወጣቱን ያስተምራል ወይስ ያደኖቅራል?
ለሰዎች ጤና ይሰጣል ወይስ ያሳምማል?
ካልቸራችንን ያለመልማል ወይስ ያፈርሳል?
መንፈሳዊ ሕይወታችንን ያጠነክራል ወይስ እምነት አልባ ሞራል አልባ ፍጡራን ያደርገናል?

እያልን በመጠየቅ በቀላሉ እጅግ ትክክልኛ የፖለቲካና የፍስልፍና እውቀት ብቻ አይሆን ንቃተ ህሊና ላይ እንደርሳለን!
ይህ ሳናደርግ ብንቀር ጉዞና ሃሳባችን ሁሉ የጨረባ ይሆናል ።
የግል ምኞትና ፍላጎታችን የዩኒቨርስ እውነት አይደለም።
የአንዱ ወገን ትቅም ብቻ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰዋስው ሊሆን የፖለቲካ ሳይንስ አይፈቅድም፣ ሊኖር አይችልም ።

ይህን መሰረታዊ እውነትና ሳይንስ ያልተገነዘቡ ናቸው በነሲብ እየተነሱ በጦርነትና በትግል ህይወትና ሃብታቸውን የሚያወድሙት! ድንቁርና ያስከፍላል! የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሰዋስው ምን እንደሆነ መማር ለአንድ ፖለቲካ ሰው የፊደል ገበታን ይዞ ሃ ሁ ሂ ሃ ! አቡ ጊ ዳ እንደ ማወቅ ነው !
የአቢይ ባህሪም፣ የአሜሪካ ጨዋታም፣ የቻይና እርምጃም፣ ሌላውም ሌላውም በዚህ ሜቱዶሎጂ እንመርምር!

በ. አ. (ሆረስ)

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጎሳ፡ ያላዋቂዎች የዉሸት አምላክ!

Post by Horus » 14 Jan 2022, 15:56

ጎሳ፣ ክልል፣ ጎሳ፣ ክልል ቢወቅቱት እምቦጭ !!

Horus
Senior Member+
Posts: 30668
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጎሳ፡ ያላዋቂዎች የዉሸት አምላክ!

Post by Horus » 14 Jan 2022, 21:04

ሺመልስ አብዲሳ ፤ ጎበዝ! የአሜሪካ ስንዴ ለኢትዮጵያ ለማስወገድ የምታደርገው ጥረት በጣም ይመቸኛል! የምዕራብ ባንዳ እየሆኑ ኢትዮጵያን ያስቸገሩ ሰርተውየማይበሉ ፣ አርሰው የማያበቅሉ ጥገኞችና ለማኞች ናቸው !


Post Reply