Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Horus
Senior Member+
Posts: 22063
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Horus » 09 Jan 2022, 15:29

የወያኔ ትግሬ አባትና የትግሬ ባንዳ ምንነት ምልክት፣ የስብሃት ቡድን ለምን ተፈታ?

ዛሬ አቢይ ሶስት እርስበርስ የሚጣረሱ በፋክት ያልተደገፉና የማያሳምኑ መልሶች ሰጥቷል ።

አንዱ መልስ እየመረረን የዋጥነው ዉሳኔ ነው የሚል ነው ። ይህ ተገደን የወሰድነው ውሳኔ ነው የሚል ነው ። ማነው የሚትዮጵያ መንግስት ይህን ዉሳኔ እንዲወስድ ያስገደደው፣ ያምበረከከው ሃይል? ይህ አስገዳጅ ሃይል ማን እንደሆነ ለምንድን ነው ለህዝብ የማይገለጸው? ስለዚህ ይህ የሚታመን መልስ አይደለም።

ሌላው የነዚህ ሽማግሎችና በሽተኞች፣ የተሸነፉ የትግሬ ባንዳ አባቶች መፈታት ለኢትዮጵያ አንድነት ወዘተ ጠቃሚ ነው የሚል ነው። ይህ ከትግሬ መገንጠል ጥያቄ ጋር የተያያዘ የመንግስትና የትህነግ ምስጢራዊ ድርድር ጋር የተያያዘ ከሆነ ለምን ድን ነው ከህዝብ የሚደበቀው? ስለዚህ ይህም አሳማኝ መግለጫ አይደለም አሳማኝ መልስ አይደለም ። የስብሃት ነጋ መፈታት ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት እንዴት እንደ ሚጠቅም አቢይ የገለጸው ነገር የለም።

ሌላው ሽማግሎች በእስር ቤት እንዲሞቱ ማድረግ የኢትዮጵያ ባህል አይደለም የሚል ነው ። ስድስቱም ሰዎች ሊሞቱ የደረሱ ሽማግሎች ናቸው ወይ? ይህ ከሆነው ለምንድን ነው በግልጽ ለህዝብ ቀርቦ የህዝብ ሃሳብና ፈቃደኝነት ያልተጠየቀው?

ስለዚህ የዚህ ግዙፍ ስህተት መዘዝ ከዚህ የላቀ ውድቀት በመንግስት ላይ እንዳያስከትል እጅግ ቀላል፣ ንጹህ፣ በቃላት ዳንቴል ያልተወሳሰበ እውነተኛ (ስህተትም ከሆነ ነው ብሎ) መልስ ከይቅርታና ትሁትነትን ያዋሃደ መልስ ባስቸኳይ መስጠት አለበት፣ አቢይ አህመድ ማለት ነው ።

ይህ ውሳኔ ፋይዳው ምን እንደ ሆነ፣ ለምን ዛሬ በገና እለት ፣ ለምን በዚህ ሁሉ የኢትዮጵያዊያን አንድነትና በዓል ላይ እንደ ቦምብ መወርወር እንደ ነበረበት
የገባው ኢትዮጵያዊ የለም። አቢይ አህመድ ይህን የመመለሰ ግዴታ አለበት ።

Assegid S.
Member
Posts: 538
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Assegid S. » 09 Jan 2022, 17:35

አንዱ መልስ እየመረረን የዋጥነው ዉሳኔ ነው የሚል ነው ። ይህ ተገደን የወሰድነው ውሳኔ ነው የሚል ነው ። ማነው የሚትዮጵያ መንግስት ይህን ዉሳኔ እንዲወስድ ያስገደደው፣ ያምበረከከው ሃይል? ይህ አስገዳጅ ሃይል ማን እንደሆነ ለምንድን ነው ለህዝብ የማይገለጸው?
የዚህ ጥያቄ መልስ ... ጠቅላይ ሚንስትሩ ሁሌም እንደሚያደርጉት፣ እኛም ዘወትር እንደምናየው " እኔ ከደሙ ንፁህ ነኝ!" የማለትና በሌላው የማላከክ ነባር ባህሪያቸው መገለጫ ነው። ውሳኔው የራሳቸው የጠቅላይ ሚንስትሩ እንደ ሆነ በሁለት ምክንያቶች ከፍተኛ ጥርጣሬ አለኝ:

1. ውሳኔው ከገና በዓል (የክርስቶስ ውልደት) ጋር ተያይዞ የተወሰደ በመሆኑ ... ጠቅላይ ሚንስትሩ ዘወትር ከሚያሳዩት ፖለቲካን ከሀይማኖት ጋር አጣምዶ በማረስ ፖለቲካዊ ምርት (ትርፍ) ከመሰብሰብ ባህሪያቸው ጋር በደንብ ይዛመዳል።

2. በቅርብ ቀን ከሹመታቸው ይነሳሉ ተብሎ የሚታሰቡትን ኣሜሪካዊውን አደራዳሪ ለማግኘት በተደጋጋሚ ፍቃደኛ ያልነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር፥ በአሸናጋዩ የመጨረሻ ጉዞ ወቅት ግን ፍቃደኛ ሆነው ፊት ለፊት ከተገናኙ ቦኋላ የተሰማ ውሳኔ በመሆኑ … ምናልባትም ጠቅላይ ሚንስትሩ በኢትዮጵያና ሱዳን ስኬት ለራቃቸው አሜሪካዊ አሸናጋይ የሥራ (የሹመት) ስንብት ልክ እንደ face saving token… ለስራቸው ክንዋኔ (CV) የሰጠዋቸው ገፀ በረከት ሊሆን ይችላል። ይህ ደግሞ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን እንደ ግል ንብረታቸው ቆጥሮ በየትኛውም ጉዳይ ላይ ያሻቸውን ውሳኔ በግላቸው ከመወሰን ባህሪያቸው ጋር በደንብ ይጋጠማል።

ከዚህ ባሻገር ግን ... በሀገራቸን ዕጣ ፈንታ ላይ ለመወሰን ከእኛ ከባለሀገሮቹ ውጪ ማንም መብትና ስልጣን ሊሰጠው አይገባም የሚል እምነት ስላለኝ፥ አሜሪካንን እና አውሮፓን ከዚህ vague equation ውስጥ በማውጣት፥ በኣዲሱ የመከላከያ መ/ቤት ህንፃ ምረቃ ሥነስርዓት ላይ ሲናገሩ እንደሰማኋቸው ... ሌላ ታዲያ ማን ነግሯቸው ነው ጠቅላይ ሚንስትሩ "እኛም ለመጀመሪያ ጊዜ ስንሰማ ደንግጠናል" ብለው የተናገሩት? ብዬ ልጠይቅ።

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን? ወይንስ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ? አሁን ነው "አሆ! በል ጅቦ" ማለት። መቼም አቶ ደመቀ መኮንን እንደማይሆኑ እርግጠኛ ነኝ። ምክንያቱም፦ ጎራቸው (ፓርቲያቸው) እንኳን ሌላውን ማስፈታት እራሳቸውም ካሉበት የአሽከርነት እስራት መፍታት ከማይችሉት ብአዴን ከሚሉት በድን ቡድን ነውና
የነዚህ ሽማግሎችና በሽተኞች፣ የተሸነፉ የትግሬ ባንዳ አባቶች መፈታት ለኢትዮጵያ አንድነት ወዘተ ጠቃሚ ነው … የስብሃት ነጋ መፈታት ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት እንዴት እንደ ሚጠቅም ...
ጠቅላይ ሚንስትሩ በዛሬው ንግግራቸው ላይ እኮ ... እነዚህን ግለሰቦች በእስር መጠበቁ ምንም ፋይዳ የለውም፤ ምክንያቱም ባለው አሁናዊ የሀገሪቱ ተጨባጭ ፖለቲካ ላይ የሚጫወቱት ምንም ሚና የለም በማለት ተናግረዋል። ታዲያ እንዴት ነው "ለኢትዮጵያ አንድነትና ወዘተ ጠቃሚ የሚሆኑት?"። ጠቅላይ ሚንስትሩ ነገር አለሙ ሁሉ ተጠቅልሎባቸዋል ወይ አውቀው ጠቅልለውብናል።
... ለምንድን ነው በግልጽ ለህዝብ ቀርቦ የህዝብ ሃሳብና ፈቃደኝነት ያልተጠየቀው?
ይህ እኔም የማስበውና የምጠይቀው ጥያቄ ነው። የተደፈሩት ከሀገራዊ እምነትና ባህላችን ውጪ የተዋረዱት … የምስኪን ኣራሹ ሚስትና ሴት ልጆች እንጂ የጠቅላይ ሚንስትሩ ቤተሰቦች አይደሉም፤ የፈረሰው ... የምሲኪኑ ጎጆ እንጂ የጠቅላይ ሚንስትሩ ቤተመንግስት አይደለም፤ የተቃጠለው ... ምስኪኑ ገበሬ በባዶ ሆዱ አርሶ ጎልጉሎና አርሞ ለእሸት ያበቃው ማሳ እንጂ የጠቅላይ ሚንስትሩ ባለሟሎች ሽንኩርትና በርበሬ የሚሸምቱበት የገበያ አዳራሽ አይደለም። ይቅርታ ማድረግ ካለበት ... ልጁ የተደፈረችበት አባት እንጂ ጠቅላይ ሚንስትሩ አይደሉም። ይቅርታ ማድረግ ካለባት… ህፃናት ልጆቿን ያለ አባት ለማሳደግ የተገደደችባሏ በግፍ የተገደለባት እናት እንጂ ቀዳማዊ እሜቲቱ አይደሉም። ይቅርታ ማድረግ ካለባቸው … የህወሃት አረር ደረታቸውን እንደ ወንፊት በሳስቶት ሜዳ ላይ የቀሩት እግረኛ ወታደር ቤተሰቦች እንጂ በእነሱ ደምና ህይወት ደረታቸውን በከፍተኛ የጦር ሜዳ ጀብዱ ሜዳሊያ ያስጌጡት የዛሬዎቹ ተሽላሚዎች አይደሉም።

ስለዚህ፦ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢያውቁበት ኑሮ፥ ዛሬ እንደሰበሰቡት የጦር ሠራዊት፥ የጦር ጉዳተተኛና ቤተሰቦቻቸውንም ከመላው ሀገር ሰብስበው ሲያበቁ፤ እስረኛና ምርኮኛ የህወሃት አመራሮችና ድጋፍ ሰጪዎችንም በዛው መድረክ ላይ በማቆም … " በሉ ይቅርታ ጠይቁ" ብለው ለበደላቸው ምህረት ከተጎጂዎቹ እንዲለምኑ ካደረጉ ቦኋላ ነበር፥ " እሺ ... እናንተስ ምን ትላላችሁ? የበደል ስርየት ምልጃቸውን ትቀባላላችሁ?” ብለው መጠየቅና ማጠያየቅ የነበረባቸው። እሳቸው ግን … ሀገሩን ሁሉ ንቀው፣ የፈሰሰውን ደም፣ የተሰበረውን አጥንት እና ቅስም አራክሰው፥ ክስ አቋራጭ - ምህረት ሰጪ ሆኑ።
Last edited by Assegid S. on 10 Jan 2022, 07:39, edited 1 time in total.

TGAA
Member
Posts: 3900
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by TGAA » 09 Jan 2022, 19:12

የኢትዮጵያ መሪዎች ከመንግስቱ አንስቶ እስከ አብይ ያሉትን ሁሉ ማድረግ መቻላቸውን እያረጋገጡ በሄዱ ቁጥር ህዝቡ ላይ ያላቸው ንቀት እየገዘፈ ይመጣል ፤ ከመንግስቱና ከመለስ አብይ ለየት የሚል አቀራረብ ይዞ ነው መድረክ ላይ የቀረበው ፤ ትሁት ፤ ህዝብ አክባሪ ፤ ለህዝብ ተቆርቋሪ በዚህ ላይ ቃላት መግመድ ይችላል ፤ በሄደበት የተለያዩ ኢትይጵያዊያን የሚፈልጉትን በመንገር ስሜት መጎንተሉን ይችልበታል፤ ነገር ግን አብይ ከፖለቲካው ሂሳብ ውጭ ለሰው ህይወት ፤ ግድ የለሺ ነው፤ ፍትህ ፤ርትህ ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ እኩልነት ጽንሰ ሀሳቦች የመድረክ ማሸብረቅያ እንጂ ከዚያ ያለፈ ዋጋ የላቸውም ፤ ትልልቅ ስህተቶች በሰራ ቁጥር ከመሪት ጋር የመይገናኝ የሀሳብ ዳመና ላይ ሰውን እያንሳፈፈ ፤ ከመሬት ያለውን እውነታ ለማስረሳት ይዳዳል ፤ አሁን እነአቦይንስብሀትን የለቀቀበትን ዝባዝንኬ ምክንያትን እንኳን እድሜ ሙሉ ሰው ህጻንነትን ማታለል የሚችልበት አይደለም ፤ ግን የአብይን ማንነት በደንብ ለማወቅ እሰርኞችን ከመልቀቁ በፊት ያደረገውን ንግግር በደንብ ማዳመጥ ብቻ ይበቃል ፡፡1) ከኔ በላይ አዋቂ የለም ብሎ በጣም ተኮፍሷል 2) እኔ በመንግስቴ ውስጥ የሚካሄደውን ኢፍትሀዊነት አላውቅም ብሎ የህግ ስርአቱን ተጽይፎ ጻዲቅ ሆኖ ሲናገር ሲያዩት በጣም አሳፍሪ ካጅነት ነው፤ ሶስተኛ ሁልግዜም የርሱን መጥፎ ግምገማ የሚያልመው የአማራ ክልል ላይ ነው የጥሩ ስራ ምሳሌ ደግሞ የኦሮምያ ክልል ነው ፡፡ ጦርነቱ ሊነሳ አካባቢ በአማራ ግዛት እየተዘዋወረ ወኔ ቀስቃሽ ንግግር አድራጊው አብይ ነበር ከየትኛውም ክልል ይበልጥ ፤ጦርነቱ የተነሳው ወያኔ ፌደራል ላይ በከፈተው ጦርነት መሆኑ እየታወቀ፤ የትግራይ ጎረቤት አስተዳደሮችን መከላከል ያለበት ፌደራሉ መሆኑ እየታወቀ በንህዝላል አወጣጡና የካባ ውሸቱ የተነሳ የአማራና የአፋር ህብረተሰብ እንዳይጠነቀቅ አድርጎ በንብረቱ ፤ በህይወቱ ፤ ካሰከፈለው በኋላ ፤ የጦርነቱና የውድመቱ ዋና አሳሪ የሆኑትን ስብሀትን የህጉ ጉዞ ሳያልቅ ፤ የሰሩት ግፍና ክህደት ለህዝቡ ሳይዘረዘር በተሸፋፈን ሁኔታ ሽማግሌ ስለሆኑ ብሎ የዚህን የአረመኔ ወያኔ እኩይ ታሪክ በምንጣፍ ስር መደበቅና የፍርድ ስርአት አቆርጦ መልቀቅ ፤ ከዚያ ደግሞ በምንም የማይገናኝ ተረት ተረት በማውራት ይህንን የሞራል ውድቀት ለመደበቅ መሞከር ከህዝብ ንቀት የሚመጣ ትእቢት ነው ፤ አብይ ከዚህ በኋላ ልጓሙ የተፈታ ፈረስ ነው ፤ ስለዚህ ሁሉም ለራሱ ዘብ የሚቆምበት ግዜ ነው ፤ በአሁኑ ሰአት አብይ ማንም የሚፈልገው የለም ፤ ይህንን ስለሚያውቅ አደገኛ ስራዎችን ለመስራት ይዳዳዋል ፤ ስለዚህ ሁሉም ተጠንቆ መቆም ያለበት ወቅት ነው፤ ክሁሉም ደግሞ የአማራው ህብረተሰብ አመራሮች ፤ ከኦሮሞ ወንድሞቻቸው ተምረው ፤ የነሱን ፍኖተ ካርታ ተከትለው ፤ ካልሰሩ አደጋው ለመላው ሀገር ትልቅ ነው የሚሆነው ለምን ቢባል በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ አጀንዳ እንደ ሽፋን ነው እንጂ ለእውነት እየተሰራበት እንዳልሆነ ፍንትው ብሎ እየታየ ስለሆነ፤በተመጣጣኝ ጉልበት መመለስ የሚችልም ይህ ህብረተሰብ ስለሆነ ፤በቁጥር ብዛቱ የተነሳ፤ አብይ የተካነው ነገር ቢኖረ ከአንድ እርካን ወደ ሌላ መሸጋገር አድሮ መጠቀሚያ እንጂ ቃሉን ጠብቆ በቆመበት የሚገኝ ሰው አይደለም ፤ ለኤርትራም ሆነ ትልቅ መስዋእትነት ለከፈሉት የአፋርና ለአማራ ብሄረሰብ ደጋግሞ አሳይቷል ፡ጎል ደርሶ ኳስ ለወያኔ የሚያቀብል ብኩን ሰው ከዚህ አስመሳይ አምሮ ምን እንዳለ መገመት አይቻልም ፡፡

Wedi
Member+
Posts: 5205
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Wedi » 09 Jan 2022, 19:22

Horus wrote:
09 Jan 2022, 15:29
"የእነ ስብሃት ነጋር ከእስር መፈታት ዜና በሰማን ግዜ እኛም ተደናግጠን ነብር" አብይ አህመድ ዛሬ የተናገረው

Horus አብይ አህመድ ለምን እና ምን ለማለት ፈልጎ ይህን እንደናገረ ገብቶሃል? :P :oops:

Abere
Member
Posts: 4241
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Abere » 09 Jan 2022, 20:08

"የእነ ስብሃት ነጋር ከእስር መፈታት ዜና በሰማን ግዜ እኛም ተደናግጠን ነብር" አብይ አህመድ

ታዲያ ምን ችግር አለበት አንተ ካልሰማህ ተመልሰው እስር ቤት እንድ ገቡ ማድረግ ነው እንጅ። ከስር ቤት አምልጠው ከሆነ ወንጀላቸው ይጨምራል፥ ያስመለጣቸውም በህግ ይጠየቃል። ምን አይነት ፉዞ ነው እባካችሁ ደግሞ ሰው እኮ ሊያጭበረብር ይሞክራል። አንዳ አንድ ውታፍ ነቃይ ዩቲዩብ ቱልቱላዎች ማስተጋባት ጀምረዋል። ሂሳብ ተቀብለዋል ለማስተጋባት።

ለመሆኑ መለስ ዜናዊ እነ ስዬ አብርሃ ከእስር ቤት ተለቀው መንገድ ላይ እያሉ ነበር እኮ ተመልሰው እስር ቤት እንድ ገቡ ያደረገው። ስለዚህ በስህተት እነ ስብሃት ከወጡ ተመልሰው መታሰር አለባቸው ማለት ነው። ስልክ መደወል ብቻ እኮ ነው ለፓሊስ - እንድ ታሰሩ ለማድረግ።

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 11291
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Abe Abraham » 09 Jan 2022, 20:22

Abere wrote:
09 Jan 2022, 20:08"የእነ ስብሃት ነጋር ከእስር መፈታት ዜና በሰማን ግዜ እኛም ተደናግጠን ነብር" አብይ አህመድ

ታዲያ ምን ችግር አለበት አንተ ካልሰማህ ተመልሰው እስር ቤት እንድ ገቡ ማድረግ ነው እንጅ። ከስር ቤት አምልጠው ከሆነ ወንጀላቸው ይጨምራል፥ ያስመለጣቸውም በህግ ይጠየቃል። ምን አይነት ፉዞ ነው እባካችሁ ደግሞ ሰው እኮ ሊያጭበረብር ይሞክራል። አንዳ አንድ ውታፍ ነቃይ ዩቲዩብ ቱልቱላዎች ማስተጋባት ጀምረዋል። ሂሳብ ተቀብለዋል ለማስተጋባት።

ለመሆኑ መለስ ዜናዊ እነ ስዬ አብርሃ ከእስር ቤት ተለቀው መንገድ ላይ እያሉ ነበር እኮ ተመልሰው እስር ቤት እንድ ገቡ ያደረገው። ስለዚህ በስህተት እነ ስብሃት ከወጡ ተመልሰው መታሰር አለባቸው ማለት ነው። ስልክ መደወል ብቻ እኮ ነው ለፓሊስ - እንድ ታሰሩ ለማድረግ።
Abere,

https://www.reuters.com/world/africa/su ... 021-11-01/

Bashir-era Sudanese ruling party head Ghandour re-arrested - family source
KHARTOUM, Nov 1 (Reuters) - Ibrahim Ghandour, head of Sudan's disbanded former ruling National Congress Party and a former foreign minister under deposed President Omar al-Bashir, was re-arrested on Monday less than a day after he had been released from jail, according to a source from his family.

The release of Ghandour and several other Bashir allies in recent days, following a military coup last week, had come under criticism from opponents of military rule.

Ghandour had previously been detained under orders of a taskforce intended to dismantle and prevent the return of Bashir'sthree-decade rule, which ended in 2019.

He had been released on Sunday night, along with two former intelligence officials under Bashir. Two other Islamist Bashir allies, including businessman Abdelbasit Hamza, had also been released on Saturday, judiciary sources said.

Sudan's public prosecutor was also dismissed Sunday night.

The government spokesman's office, still aligned with civilian authorities who were removed last week, said in a statement that the releases of the Bashir-era figures "represent a setback against the state of institutions and the rule of law."

"This step makes clear the political cover for the coup and its real ideological orientation," the office said in a Facebook post.

Horus
Senior Member+
Posts: 22063
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Horus » 09 Jan 2022, 20:46

TGAA
ባለስልጣኖች ድጋፍ ባገኙ ቁጥር ሕዝብ እየናቁ ይሄዳሉ የሚለው የማይስት የፖለቲካ ማክሲም ነው። በእንግሊዝኛ 'familiarity breeds contempt' ወይም አወቅሁሽ ናቅሁሽ ይባላል። ጉዳዩ ያቢይ ፐርሰናሊቲ አይደለም ፤ በፖለቲካ ሳይንስ ውስጥ በስልጣን የማይባልግ አንድም ፖለቲከኛ የለም። አቢይ ድጋፉን በከንቱ ያባከነ፣ የሚያባክን ፖለቲከኛ ነው።
Wedi
አቢይ ከላይ ያለው አው ቁጣችሁና ንዴታችሁ ተሰምቶኛል ብሎ ልብ ለመብላት ነው ፤ ተሳስችሃለሁ ይቅርታ አድርጉልኝ የማለት ድፍረትና ብስለት ስለሌለው ነው። የመሪነት እምብርት ካሬጅ (ጽናት) ነው ። አሁንም ከዚህ አሳዛኝ ስህተት መውጪያ መንገድ አንድ ነው ፤ እንደ መሪ ቆሞ እንደ ሰው ስህተት መስራቱን አምኖ ይቅርታ መጠየቅ ነው ያለበት ።
Last edited by Horus on 10 Jan 2022, 04:21, edited 1 time in total.

kibramlak
Member
Posts: 1729
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by kibramlak » 10 Jan 2022, 03:58

ቁልፍ እይታ ነው ! ይህን ሳስብ ነበር
በተለይ አማራው አካባቢ ሌላ ቁማር እና የበቀል ስራዎች ሊሰራ ይችላል፣፣ አንዳንዶቹ የሚገመቱ ናቸው
TGAA wrote:
09 Jan 2022, 19:12
,............... በአሁኑ ሰአት አብይ ማንም የሚፈልገው የለም ፤ ይህንን ስለሚያውቅ አደገኛ ስራዎችን ለመስራት ይዳዳዋል ..............
ከዛ ውጭ ሰውየው ዋሽቷል ሁሉም እሱ ሳያውቀው የሚሆን ነገር የለም፣፣ አስታውሱ እስክንድርን ሊበላ ሲያስብ እንዴት ያን ያህል ወርዶ እሳት ልብሶ እሳት ጎርሶ ከአንድ በወቅቱ አክቲቪስት ከነበረ ግለሰብ ጋር ሲነታረክ እንደነበር ችግሩ የፖለቲካ ሳይሆን እስክንድር የአዲስ አበባን የህዝብ ድጋፍ ያሳጣኛል እንደ ኦሮሙማ የሚሰራውንም ጉድ በማጋለጥ ይቀጥላል በሚል እንጅ እስክንድር እንደነ ጃዋር ሰው አስገድሎ ንብረት አስወድሞ አደለም፣፣ ስለዚህ አብይ ለስልጣን ሲል ማንኛውንም ቀፋፊ ነገር ከማድረግ ወደ ሁዋላ አይልም
ሌላ የማናውቀው ተአምራዊ ነገር ከሌለ በስተቀር አሁን ለሰራቸው ሸፍጥ እና ሴራ የሚፈታ ልብ ያገኛል ብየ አላምንም፣፣

Assegid S.
Member
Posts: 538
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Assegid S. » 10 Jan 2022, 07:39

kibramlak wrote:
10 Jan 2022, 03:58
ቁልፍ እይታ ነው ! ይህን ሳስብ ነበር
በተለይ አማራው አካባቢ ሌላ ቁማር እና የበቀል ስራዎች ሊሰራ ይችላል፣፣ አንዳንዶቹ የሚገመቱ ናቸው
TGAA wrote:
09 Jan 2022, 19:12
,............... በአሁኑ ሰአት አብይ ማንም የሚፈልገው የለም ፤ ይህንን ስለሚያውቅ አደገኛ ስራዎችን ለመስራት ይዳዳዋል ..............
ከዛ ውጭ ሰውየው ዋሽቷል ሁሉም እሱ ሳያውቀው የሚሆን ነገር የለም፣፣ አስታውሱ እስክንድርን ሊበላ ሲያስብ እንዴት ያን ያህል ወርዶ እሳት ልብሶ እሳት ጎርሶ ከአንድ በወቅቱ አክቲቪስት ከነበረ ግለሰብ ጋር ሲነታረክ እንደነበር ችግሩ የፖለቲካ ሳይሆን እስክንድር የአዲስ አበባን የህዝብ ድጋፍ ያሳጣኛል እንደ ኦሮሙማ የሚሰራውንም ጉድ በማጋለጥ ይቀጥላል በሚል እንጅ እስክንድር እንደነ ጃዋር ሰው አስገድሎ ንብረት አስወድሞ አደለም፣፣ ስለዚህ አብይ ለስልጣን ሲል ማንኛውንም ቀፋፊ ነገር ከማድረግ ወደ ሁዋላ አይልም
ሌላ የማናውቀው ተአምራዊ ነገር ከሌለ በስተቀር አሁን ለሰራቸው ሸፍጥ እና ሴራ የሚፈታ ልብ ያገኛል ብየ አላምንም፣፣
ይህንን ሐቅ የትላንት እና የትላንት ወዲያው የጦር ሠራዊቱ ሹመት በግልፅ አስቀምጦታል። የትኛውም መንግስት በኣብዛኛው መመዘኛ ወቅታዊ ያልሆነ ሹመትና ሽረት ሲያደርግ ምክንያቶቹ ሁለት ናቸው: ለመንግስቱ ግዛት እየታየ ያለን የስጋት ደመና መግፈፍ ወይንም ደግሞ መንግስቱ ሊከውነው ያሰበውን ኢህዝባዊ ተግባር ማሳካት ነው። በሌላ አባባል ... ጦር ሠራዊቱን መደለል። የኣምባገነን አገዛዝ ወታደራዊ ክፍሉን በማስደሰት ይጀመራል - ይፀናል።

ከዚህ ባለፈ ግን Horus, December 20 / 2021 ፖስት ባደረከው "discussion thread" ላይ ከነበረህ "Abiy has the power who to jail, who to free!!" የሚል ምልከታህ ወጥተህ ይህንን አቋም መያዝህ እጅግ መልካም ነው።

Tiago
Member
Posts: 717
Joined: 30 Jul 2018, 02:09

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Tiago » 10 Jan 2022, 08:17

Neamin Zeleke
@NeaminZeleke
·
Jan 9, 2022
A bad decision & timing that threw a grenade amidst the Unity of #Ethiopians. People feel betrayed by PM Abiy's govt & support should not be taken for granted. No compelling reason & a flawed process to release the arch #TPLF genociders. Peace can’t be sustained without justice.

Meleket
Member
Posts: 1175
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Meleket » 10 Jan 2022, 09:37

የ2022 ምርጥ አባባሎች መድረክ ላይ ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል! ድንቅ እይታ ነው! :mrgreen:
Assegid S. wrote:
10 Jan 2022, 07:39
kibramlak wrote:
10 Jan 2022, 03:58
ቁልፍ እይታ ነው ! ይህን ሳስብ ነበር
በተለይ አማራው አካባቢ ሌላ ቁማር እና የበቀል ስራዎች ሊሰራ ይችላል፣፣ አንዳንዶቹ የሚገመቱ ናቸው
TGAA wrote:
09 Jan 2022, 19:12
,............... በአሁኑ ሰአት አብይ ማንም የሚፈልገው የለም ፤ ይህንን ስለሚያውቅ አደገኛ ስራዎችን ለመስራት ይዳዳዋል ..............
ከዛ ውጭ ሰውየው ዋሽቷል ሁሉም እሱ ሳያውቀው የሚሆን ነገር የለም፣፣ አስታውሱ እስክንድርን ሊበላ ሲያስብ እንዴት ያን ያህል ወርዶ እሳት ልብሶ እሳት ጎርሶ ከአንድ በወቅቱ አክቲቪስት ከነበረ ግለሰብ ጋር ሲነታረክ እንደነበር ችግሩ የፖለቲካ ሳይሆን እስክንድር የአዲስ አበባን የህዝብ ድጋፍ ያሳጣኛል እንደ ኦሮሙማ የሚሰራውንም ጉድ በማጋለጥ ይቀጥላል በሚል እንጅ እስክንድር እንደነ ጃዋር ሰው አስገድሎ ንብረት አስወድሞ አደለም፣፣ ስለዚህ አብይ ለስልጣን ሲል ማንኛውንም ቀፋፊ ነገር ከማድረግ ወደ ሁዋላ አይልም
ሌላ የማናውቀው ተአምራዊ ነገር ከሌለ በስተቀር አሁን ለሰራቸው ሸፍጥ እና ሴራ የሚፈታ ልብ ያገኛል ብየ አላምንም፣፣
ይህንን ሐቅ የትላንት እና የትላንት ወዲያው የጦር ሠራዊቱ ሹመት በግልፅ አስቀምጦታል። የትኛውም መንግስት በኣብዛኛው መመዘኛ ወቅታዊ ያልሆነ ሹመትና ሽረት ሲያደርግ ምክንያቶቹ ሁለት ናቸው: ለመንግስቱ ግዛት እየታየ ያለን የስጋት ደመና መግፈፍ ወይንም ደግሞ መንግስቱ ሊከውነው ያሰበውን ኢህዝባዊ ተግባር ማሳካት ነው። በሌላ አባባል ... ጦር ሠራዊቱን መደለል። የኣምባገነን አገዛዝ ወታደራዊ ክፍሉን በማስደሰት ይጀመራል - ይፀናል።

ከዚህ ባለፈ ግን Horus, December 20 / 2021 ፖስት ባደረከው "discussion thread" ላይ ከነበረህ "Abiy has the power who to jail, who to free!!" የሚል ምልከታህ ወጥተህ ይህንን አቋም መያዝህ እጅግ መልካም ነው።

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 11291
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Abe Abraham » 10 Jan 2022, 09:54

There is no threat of any nature coming from the army. The prime minister has nothing to fear from them. He has still " the power who to jail, who to free. " If he is going to make concessions to the Junta it will be done with the co-operation and willingness of the Amhara elites around him like the most pro-TPLF elements in the government. If I am not wrong Timotheos is Amhara.

Abere
Member
Posts: 4241
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Abere » 10 Jan 2022, 09:59

---ትክክለኛው እርምጃ መሆን ያለበት ስብሃት ነጋ እና አብረውት የተፈቱትን ወንጀለኞች እስር ቤት ማስገባት ብቻ ነው። መንግስት ነኝ ባይ ክሱን ቢያቋርጥም የኢትዮጵያ ህዝብ አቤቱታውን እያሰማ ነው። በተጨማሪም በርካታ ግለሰቦች እነ ስብሃት ነጋን በእራሳቸው ከሰው በህግፊት ለማቆም እየተነሳሱ ነው። በእነ ስብሃት ወንጀል ምክንያት የተጎዱ ቤተሰቦች እና ግለሰቦች በእራሳቸው ተነሳሽነት የመክሰስ መብታቸውን ሊጠቀሙ እየተገደዱ ነው- መንግስት ንጹህ ናቸው ብሎ ቢለቃቸውም። በእርግጥ ህግ ስለሌለ ተፈጻሚ ላይሆን ይችላል ሆኖም ግን ይቅርታ የማይገባችው ወንጀለኞች በመሆናቸው በሰለጠነው አለም ደግሞ እንደ እነዚህ አይነት ወንጀለኞች ከ 200 እስከ 300 አመት እስራት ፍርድ የሚፈረድባቸው ናቸው። እንድሁ እንደ ተራ ኪስ አውላቂ ሌባ የገና እለት ምህረት የሚደረግላቸው ሰዎች አይደሉም። የአብይ አህመድን የአእምሮ ዘገምተኛነት ወይ እኩይ ሴራ እና ወንጀለኛ ተባባሪነት ከማሳየት ውጭ የተደረገው ስራ ሌላ ምንም ሊባል አይችልም። አንዳንድ ውታፍ ነቃዮች አብይ አህመድ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ይጠይቅ ይላሉ። በጣም ያሳዝኑኛል ገና የእርሱን ትውከት ይልሳሉ። ምንም አይነት ይቅርታ አይመልሰውም። ይቅርታ መጠየቅ እራሱ የኢትዮጵያን ህዝብ ሞኝ ወይም ሆዳም አላማ ቢስ አድርጎ መቁጠር ነው። ስልጣን ሲወጣ በወያኔ ስም ለተሰራው 27 አመታት ወንጀል ይቅርታ ጠየቀ ተባለ። ያ እራሱ በጣም ይስቃል። ልክ በአንድ ቀን ትውውቅ ብቻ እግሯን እንደ ምትሰቅል ልጃ ገረድ የኢትዮጵይ ህዝብ ዝም ብሎ ለድንገተኛ ሰው ሁሉ ልቡን ይከፍታል ማለት ነው። አብይ አህመድ ያለው አማራጭ ወይ በእብሪተኝበቱ መቀጠል ወይም እነ ስብሃትን መልሶ እስር ቤት መዝጋት።

--- ሱዳን ተከሳሹን እንደ ገና እስር ቤት የማስገባቷ እርምጃ አስፈላጊ ስለመሰላት ትክክል ነው። ሰው በስህተት ይፍታል፤ በስህተትም ይታሰራልል፡ በስህተት የተፈታ መልሶ ይታሰራል፡ ይህ ግን የሚሆነው በእራሱ የሚተማመን መንግስት ባለበት አገር ነው። ህዝብ ምን ይለኛል ብሎ የሚጨነቅ እንጅ ህዝብ የሚንቅ ደካማ መሪ ይህን አያደርግም።
Abe Abraham wrote:
09 Jan 2022, 20:22
Abere wrote:
09 Jan 2022, 20:08"የእነ ስብሃት ነጋር ከእስር መፈታት ዜና በሰማን ግዜ እኛም ተደናግጠን ነብር" አብይ አህመድ

ታዲያ ምን ችግር አለበት አንተ ካልሰማህ ተመልሰው እስር ቤት እንድ ገቡ ማድረግ ነው እንጅ። ከስር ቤት አምልጠው ከሆነ ወንጀላቸው ይጨምራል፥ ያስመለጣቸውም በህግ ይጠየቃል። ምን አይነት ፉዞ ነው እባካችሁ ደግሞ ሰው እኮ ሊያጭበረብር ይሞክራል። አንዳ አንድ ውታፍ ነቃይ ዩቲዩብ ቱልቱላዎች ማስተጋባት ጀምረዋል። ሂሳብ ተቀብለዋል ለማስተጋባት።

ለመሆኑ መለስ ዜናዊ እነ ስዬ አብርሃ ከእስር ቤት ተለቀው መንገድ ላይ እያሉ ነበር እኮ ተመልሰው እስር ቤት እንድ ገቡ ያደረገው። ስለዚህ በስህተት እነ ስብሃት ከወጡ ተመልሰው መታሰር አለባቸው ማለት ነው። ስልክ መደወል ብቻ እኮ ነው ለፓሊስ - እንድ ታሰሩ ለማድረግ።
Abere,

https://www.reuters.com/world/africa/su ... 021-11-01/

Bashir-era Sudanese ruling party head Ghandour re-arrested - family source
KHARTOUM, Nov 1 (Reuters) - Ibrahim Ghandour, head of Sudan's disbanded former ruling National Congress Party and a former foreign minister under deposed President Omar al-Bashir, was re-arrested on Monday less than a day after he had been released from jail, according to a source from his family.

The release of Ghandour and several other Bashir allies in recent days, following a military coup last week, had come under criticism from opponents of military rule.

Ghandour had previously been detained under orders of a taskforce intended to dismantle and prevent the return of Bashir'sthree-decade rule, which ended in 2019.

He had been released on Sunday night, along with two former intelligence officials under Bashir. Two other Islamist Bashir allies, including businessman Abdelbasit Hamza, had also been released on Saturday, judiciary sources said.

Sudan's public prosecutor was also dismissed Sunday night.

The government spokesman's office, still aligned with civilian authorities who were removed last week, said in a statement that the releases of the Bashir-era figures "represent a setback against the state of institutions and the rule of law."

"This step makes clear the political cover for the coup and its real ideological orientation," the office said in a Facebook post.

Meleket
Member
Posts: 1175
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Meleket » 10 Jan 2022, 10:14

ጠርጥር ጠርጥር ጠርጥር . . . :mrgreen:

የሥዩምን የአባዪንና የኣስመላሽን መደበቂያ የጠቆሙት ራሳቸው እነ እንቶኔ ነበሩ ማለት ነው። ለዚያ ወደር የለሽ ሥራቸውም ዛሬ በድርድር መልክ እንዲወጡ መደረጉ ብዙም ኣይደንቅም ብለህ ጠርጥር . . . መጠርጠሩ አይከፋም . . . “ወያኔን ወያኔ ቢሰርቀው እንዴት ይደንቀው”! የሚያስብል ሳይሆን ይቀራል ሰሞንኛው ኵነት!

ለማንኛውም ወጣቱ ጠቅላዪ ምህረት ማድረጉ ካልቀረ ታድያ ለምን ጐንደሬውን በረከት ስምዖንን አይፈታም? :mrgreen: ሚጮህለት ስለሌለ ነውን? እሱ በኅሊናው ለእናት አገሩ ለጦቢያ በሙሉ ልቡ ከስብሓት ነጋ እኩል አልደከመላትምን? ይህ የሚያሳየው አሁንም ድረስ የሕወሓትን ፈርጣማነትና የብአዴንን (የአብንን) ደካማነት ነው። ሊያስብል ይችላል።

“ኢጦቢያ ኣገራቸው ሞኝ ነሽ ተላላ፡
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” የተባለው ለካ . . . እንዲህ ያጋጠመ ለታ ነው!
:mrgreen:

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 3210
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Za-Ilmaknun » 10 Jan 2022, 13:44

Abe Abraham wrote:
10 Jan 2022, 09:54
Assegid S. wrote:
10 Jan 2022, 07:39
kibramlak wrote:
10 Jan 2022, 03:58
ቁልፍ እይታ ነው ! ይህን ሳስብ ነበር
በተለይ አማራው አካባቢ ሌላ ቁማር እና የበቀል ስራዎች ሊሰራ ይችላል፣፣ አንዳንዶቹ የሚገመቱ ናቸው
TGAA wrote:
09 Jan 2022, 19:12
,............... በአሁኑ ሰአት አብይ ማንም የሚፈልገው የለም ፤ ይህንን ስለሚያውቅ አደገኛ ስራዎችን ለመስራት ይዳዳዋል ..............
ከዛ ውጭ ሰውየው ዋሽቷል ሁሉም እሱ ሳያውቀው የሚሆን ነገር የለም፣፣ አስታውሱ እስክንድርን ሊበላ ሲያስብ እንዴት ያን ያህል ወርዶ እሳት ልብሶ እሳት ጎርሶ ከአንድ በወቅቱ አክቲቪስት ከነበረ ግለሰብ ጋር ሲነታረክ እንደነበር ችግሩ የፖለቲካ ሳይሆን እስክንድር የአዲስ አበባን የህዝብ ድጋፍ ያሳጣኛል እንደ ኦሮሙማ የሚሰራውንም ጉድ በማጋለጥ ይቀጥላል በሚል እንጅ እስክንድር እንደነ ጃዋር ሰው አስገድሎ ንብረት አስወድሞ አደለም፣፣ ስለዚህ አብይ ለስልጣን ሲል ማንኛውንም ቀፋፊ ነገር ከማድረግ ወደ ሁዋላ አይልም
ሌላ የማናውቀው ተአምራዊ ነገር ከሌለ በስተቀር አሁን ለሰራቸው ሸፍጥ እና ሴራ የሚፈታ ልብ ያገኛል ብየ አላምንም፣፣
ይህንን ሐቅ የትላንት እና የትላንት ወዲያው የጦር ሠራዊቱ ሹመት በግልፅ አስቀምጦታል። የትኛውም መንግስት በኣብዛኛው መመዘኛ ወቅታዊ ያልሆነ ሹመትና ሽረት ሲያደርግ ምክንያቶቹ ሁለት ናቸው: ለመንግስቱ ግዛት እየታየ ያለን የስጋት ደመና መግፈፍ ወይንም ደግሞ መንግስቱ ሊከውነው ያሰበውን ኢህዝባዊ ተግባር ማሳካት ነው። በሌላ አባባል ... ጦር ሠራዊቱን መደለል። የኣምባገነን አገዛዝ ወታደራዊ ክፍሉን በማስደሰት ይጀመራል - ይፀናል።

ከዚህ ባለፈ ግን Horus, December 20 / 2021 ፖስት ባደረከው "discussion thread" ላይ ከነበረህ "Abiy has the power who to jail, who to free!!" የሚል ምልከታህ ወጥተህ ይህንን አቋም መያዝህ እጅግ መልካም ነው።
There is no threat of any nature coming from the army. The prime minister has nothing to fear from them. He has still " the power who to jail, who to free. " If he is going to make concessions to the Junta it will be done with the co-operation and willingness of the Amhara elites around him like the most pro-TPLF elements in the government. If I am not wrong Timotheos is Amhara.
Tim is from the South. :mrgreen: However, I have to agree with you on the assessment that the ADP leaders are always the most cowards who never will stand to promote the aspirations of their people. The good thing is the majority of the people have now somehow a real time test of TPLF and its barbarism and therefore, won't be willing partners in this grand scale crime. The PM seems to be in awe of the awakening of the Ethiopianism sentiment which doesn't sit well with the tribalism politics of his base. :mrgreen:

Horus
Senior Member+
Posts: 22063
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Horus » 10 Jan 2022, 14:05

እኔ ሆረስ ብዙ ቃላት መፍለጥ አይመቸኝም። የትግሬ ችግር ምንድን ነው? የትግሬ ችግር ምን ፈጠረው? ማን ፈጠረው? የትግሬ ችግር መፍትሄ ምንድን ነው?

የትግሬ ችግርን የፈጠረው የብሄር ጥያቄ የሚባለው ዉሸት ነው ። ከዚህ የብሄር ጥያቄ ዉሸት ጀርባ ያለው የመሬት እና ሃብት ፍላጎት ነው። ምን ማለቴ ነው?

መጀመሪያ ትግሬዎችና አማራዎች ኢትዮጵያዊያን ናቸው ወይ ብለን እርግጠኛ መልስ መያዝ አለብን ። የዚህ ጥያቄ መልስ አዎ ከሆነ የሚቀጥለው ጥያቄ ...

ትግሬዎች እና አማራዎች የሚኖሩበት መሬት የማን ነው? ማነው ባለቤቱ? ማነው ባለንብረቱ? ብለን መጠየቅ ግዴታ ነው ። መልሱ የኢትዮጵያ መሬት ነው፤ ባለቤቱ፣ ባለንብረቱ ኢትዮጵያ ናት የሚለ ነው ።

የትግሬ ችግር መፍቻ ቁልፍ ወይም ፍሬምወርክ ይህ ነው ።

የትግሬ ችግር የተወለደው የትግሬ መሬት፣ ያማራ መሬት ተብሎ ድምበር እና ካርታ በዉሸት የተቀመረ ግዜ ነው። ዛሬ ይህ ችግር በፈጠረው የክልል ካርታ ፍሬምወርክና የዉሸት ቲኦሪ ላይ ቆመው እነ አቢይ፣ እነ ጌታቸው ረዳ የትግሬን ችግር ሊፈቱ ይባክናሉ ። በዚህ መንገድ የሚፈታ ነገር የለም።

እንዲያም ይህን ሞዴል ይዘው አመሪካኖች አቢይን ና ትግሬዎችን እስከ ዘወሩ ድረስ ምንም የሚመጣ መፍትሄ የለም፤ ከአንድ ጦርነት ወደ ሌላ አይነት ጦርነት ከመሄድ ባለፈ ።

አማራና ትግሬን እንደ ሁለት ሉዓላዊ አገሮች ወስዶ ስለድምበራቸውና ኢኮኖሚ ክፍፍላቸው ማሰብን የሚያክል በድንቁርና የታጀበር አመለካከት የለም!

የምናወራው ስለትግሬ ወይም አማራ ተገንጥሎ አገር ስለመሆን ከሆነ አው የትግሬ ድምበር የት ነው ማለት እንችላለን! ላማራም እንዲሁ። የሚፈለገው ሪያሊቲ ይህ ካልሆነ ...

የመፍትሄው ሃሳብ የክልልነት ሞዴል ማፍረስና የክልል ድምበር ጥያቄ እስከነአካቴው መሻር የመጀመሪያ የምፍትሄ ሃሳብ ነው ። ክልልነት የፈጠረውን ግዙፍ ችግር በክልልነት ሞዴልና ፍሬምወርክ ለመፍታት መሞከር ጅልነት ብቻ ሳይሆን ለማሰብ አለመቻል ነው ። ክልሎች እስካሉ ድረስ በትግሬና አማራ መሃል ያለው ጦርነት አይቆምም ።

ስለዚህ የትግሬም ሆነ ያማራ መሬት ላይ ገዥና ወሳኝ መሆን ያለባል ኢትዮጵያ ነች ። ያኔ ብቻ ነው የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ የሚፈታው።

በሌላ አነጋገር አቢይ አህመድ አሜሪካኖችና አውሮፓዊያን ከሰጡር ወጥመድና ሞዴል እስካልወጣ ድረስ በከንቱ ነው የኢትዮጵያዊያንን ጉልበትና ሃብት የሚያባክነው ።

አስባለሁ፣ ችግር እፈታለሁ የሚል ከሆነ ቅኝ ገዦች ከሸነሸኑት የጎሳ ክልሎች ካርታና ድምበሮች ዝባዝንኬ እራሱን ማላቀቅ አለበት ። የጎሳ ክልሎችና ድምበሮች (አሜሪካና ወያኔ የፈጠሩት) የተሻሩ እለት መፍትሄዎቹ ወለል ብለው ይታያሉ ።

የእኔ ፍርሃት ግን የትግሬ፣ አማራና ኦሮሞ የጎሳ ከበርቴዎች የየጎሳቸውን መሬትና ሃብት ለመሮጣጠርና ለመበዝበዝ ሲሉ ክልሎቹን እንደ ወርቅና አልማዝ ይፈልጓቸዋል። ለዚህ ሁሉ የከበርቴዎች ፍላጎትና ሌብነት እይተማገደ እንደ ቆሻሻ የሚጣለው የደሃውና የምስኪኑ ገበሬ ልጅ ነው ።

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 11291
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Abe Abraham » 13 Jan 2022, 19:10

Za-Ilmaknun wrote:
10 Jan 2022, 13:44
Abe Abraham wrote:
10 Jan 2022, 09:54
Assegid S. wrote:
10 Jan 2022, 07:39
kibramlak wrote:
10 Jan 2022, 03:58
ቁልፍ እይታ ነው ! ይህን ሳስብ ነበር
በተለይ አማራው አካባቢ ሌላ ቁማር እና የበቀል ስራዎች ሊሰራ ይችላል፣፣ አንዳንዶቹ የሚገመቱ ናቸው
TGAA wrote:
09 Jan 2022, 19:12
,............... በአሁኑ ሰአት አብይ ማንም የሚፈልገው የለም ፤ ይህንን ስለሚያውቅ አደገኛ ስራዎችን ለመስራት ይዳዳዋል ..............
ከዛ ውጭ ሰውየው ዋሽቷል ሁሉም እሱ ሳያውቀው የሚሆን ነገር የለም፣፣ አስታውሱ እስክንድርን ሊበላ ሲያስብ እንዴት ያን ያህል ወርዶ እሳት ልብሶ እሳት ጎርሶ ከአንድ በወቅቱ አክቲቪስት ከነበረ ግለሰብ ጋር ሲነታረክ እንደነበር ችግሩ የፖለቲካ ሳይሆን እስክንድር የአዲስ አበባን የህዝብ ድጋፍ ያሳጣኛል እንደ ኦሮሙማ የሚሰራውንም ጉድ በማጋለጥ ይቀጥላል በሚል እንጅ እስክንድር እንደነ ጃዋር ሰው አስገድሎ ንብረት አስወድሞ አደለም፣፣ ስለዚህ አብይ ለስልጣን ሲል ማንኛውንም ቀፋፊ ነገር ከማድረግ ወደ ሁዋላ አይልም
ሌላ የማናውቀው ተአምራዊ ነገር ከሌለ በስተቀር አሁን ለሰራቸው ሸፍጥ እና ሴራ የሚፈታ ልብ ያገኛል ብየ አላምንም፣፣
ይህንን ሐቅ የትላንት እና የትላንት ወዲያው የጦር ሠራዊቱ ሹመት በግልፅ አስቀምጦታል። የትኛውም መንግስት በኣብዛኛው መመዘኛ ወቅታዊ ያልሆነ ሹመትና ሽረት ሲያደርግ ምክንያቶቹ ሁለት ናቸው: ለመንግስቱ ግዛት እየታየ ያለን የስጋት ደመና መግፈፍ ወይንም ደግሞ መንግስቱ ሊከውነው ያሰበውን ኢህዝባዊ ተግባር ማሳካት ነው። በሌላ አባባል ... ጦር ሠራዊቱን መደለል። የኣምባገነን አገዛዝ ወታደራዊ ክፍሉን በማስደሰት ይጀመራል - ይፀናል።

ከዚህ ባለፈ ግን Horus, December 20 / 2021 ፖስት ባደረከው "discussion thread" ላይ ከነበረህ "Abiy has the power who to jail, who to free!!" የሚል ምልከታህ ወጥተህ ይህንን አቋም መያዝህ እጅግ መልካም ነው።
There is no threat of any nature coming from the army. The prime minister has nothing to fear from them. He has still " the power who to jail, who to free. " If he is going to make concessions to the Junta it will be done with the co-operation and willingness of the Amhara elites around him like the most pro-TPLF elements in the government. If I am not wrong Timotheos is Amhara.
Tim is from the South. :mrgreen: However, I have to agree with you on the assessment that the ADP leaders are always the most cowards who never will stand to promote the aspirations of their people. The good thing is the majority of the people have now somehow a real time test of TPLF and its barbarism and therefore, won't be willing partners in this grand scale crime. The PM seems to be in awe of the awakening of the Ethiopianism sentiment which doesn't sit well with the tribalism politics of his base. :mrgreen:
What about Daniel Bekele ?

Horus
Senior Member+
Posts: 22063
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Horus » 13 Jan 2022, 19:30

እኔ አቢይ ማሰርና መፍታት ይችላል ስል አምባገነን ይሁን ማለቴ አለነበረም። የፖለቲካ፣ ፖሊስና ጦር ሃይል ያለው ሪጂም ቁንጮ ስለሆነ ለፖለቲካ አስሮ ለፖለቲካ ሲል ሊፈታ ይችላል ማለቴ ነበር ። ይህው እነጃዋር፣ እስክንድር፣ ስብሃትኮ ታሰሩ ተፈቱ ። ይህን ፋክት መግለጼ ነበር። ማንም እስቴት ፓወር የሚያደርገው ያ ነው። አንድ አገር በሕግ ሳይሆን በሰዎች እስከ ተገዛ ድረስ ያለው ሃቅ ያ ነው ።

ኢትዮጵያ ዛሬ በሕግ ልትገዛ አትችልም። በጎሳዎች ስልጣን ሽሚያ፣ በጎሳ የሰው ቁጥር፣ በጦርና ሚሊሺያ ብዛት ላይ የሚወላገድ መንግስት ወይም እስቴት በፍጹም በሕግ ሊስተዳደር አይችልም። ዛሬኮ ያለው በዳቦ ስም የሚጠራ የዘመነ መሳፍንት ስርዓት ነው! በቃ!

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 3210
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: የአቢይ አህመድ መልስ አልባ መልስ

Post by Za-Ilmaknun » 13 Jan 2022, 19:44

Abe Abraham wrote:
13 Jan 2022, 19:10
Za-Ilmaknun wrote:
10 Jan 2022, 13:44
Abe Abraham wrote:
10 Jan 2022, 09:54
Assegid S. wrote:
10 Jan 2022, 07:39
kibramlak wrote:
10 Jan 2022, 03:58
ቁልፍ እይታ ነው ! ይህን ሳስብ ነበር
በተለይ አማራው አካባቢ ሌላ ቁማር እና የበቀል ስራዎች ሊሰራ ይችላል፣፣ አንዳንዶቹ የሚገመቱ ናቸው
TGAA wrote:
09 Jan 2022, 19:12
,............... በአሁኑ ሰአት አብይ ማንም የሚፈልገው የለም ፤ ይህንን ስለሚያውቅ አደገኛ ስራዎችን ለመስራት ይዳዳዋል ..............
ከዛ ውጭ ሰውየው ዋሽቷል ሁሉም እሱ ሳያውቀው የሚሆን ነገር የለም፣፣ አስታውሱ እስክንድርን ሊበላ ሲያስብ እንዴት ያን ያህል ወርዶ እሳት ልብሶ እሳት ጎርሶ ከአንድ በወቅቱ አክቲቪስት ከነበረ ግለሰብ ጋር ሲነታረክ እንደነበር ችግሩ የፖለቲካ ሳይሆን እስክንድር የአዲስ አበባን የህዝብ ድጋፍ ያሳጣኛል እንደ ኦሮሙማ የሚሰራውንም ጉድ በማጋለጥ ይቀጥላል በሚል እንጅ እስክንድር እንደነ ጃዋር ሰው አስገድሎ ንብረት አስወድሞ አደለም፣፣ ስለዚህ አብይ ለስልጣን ሲል ማንኛውንም ቀፋፊ ነገር ከማድረግ ወደ ሁዋላ አይልም
ሌላ የማናውቀው ተአምራዊ ነገር ከሌለ በስተቀር አሁን ለሰራቸው ሸፍጥ እና ሴራ የሚፈታ ልብ ያገኛል ብየ አላምንም፣፣
ይህንን ሐቅ የትላንት እና የትላንት ወዲያው የጦር ሠራዊቱ ሹመት በግልፅ አስቀምጦታል። የትኛውም መንግስት በኣብዛኛው መመዘኛ ወቅታዊ ያልሆነ ሹመትና ሽረት ሲያደርግ ምክንያቶቹ ሁለት ናቸው: ለመንግስቱ ግዛት እየታየ ያለን የስጋት ደመና መግፈፍ ወይንም ደግሞ መንግስቱ ሊከውነው ያሰበውን ኢህዝባዊ ተግባር ማሳካት ነው። በሌላ አባባል ... ጦር ሠራዊቱን መደለል። የኣምባገነን አገዛዝ ወታደራዊ ክፍሉን በማስደሰት ይጀመራል - ይፀናል።

ከዚህ ባለፈ ግን Horus, December 20 / 2021 ፖስት ባደረከው "discussion thread" ላይ ከነበረህ "Abiy has the power who to jail, who to free!!" የሚል ምልከታህ ወጥተህ ይህንን አቋም መያዝህ እጅግ መልካም ነው።
There is no threat of any nature coming from the army. The prime minister has nothing to fear from them. He has still " the power who to jail, who to free. " If he is going to make concessions to the Junta it will be done with the co-operation and willingness of the Amhara elites around him like the most pro-TPLF elements in the government. If I am not wrong Timotheos is Amhara.
Tim is from the South. :mrgreen: However, I have to agree with you on the assessment that the ADP leaders are always the most cowards who never will stand to promote the aspirations of their people. The good thing is the majority of the people have now somehow a real time test of TPLF and its barbarism and therefore, won't be willing partners in this grand scale crime. The PM seems to be in awe of the awakening of the Ethiopianism sentiment which doesn't sit well with the tribalism politics of his base. :mrgreen:
What about Daniel Bekele ?
I haven't given much thought about his identity before. Now that you ask, we will dig and spill the beans. He most likely is from... :lol:

Post Reply