Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abe Abraham
Senior Member
Posts: 11599
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ሌላው የግብጽ ተስፋየ ገብረ-ኣብ ውድ ነፍስ-ሄር ወሒድ ሓምድ ፥ ሙሰልሰል(series) ኣል-ጃማዓ (The Brotherhood) season 1,Episode 1

Post by Abe Abraham » 24 Jan 2022, 16:47

ኣል-ጃማዓ SEASON ONE, Episode 26
ኣል-ጃማዓ SEASON ONE, Episode 27Abe Abraham
Senior Member
Posts: 11599
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ሌላው የግብጽ ተስፋየ ገብረ-ኣብ ውድ ነፍስ-ሄር ወሒድ ሓምድ ፥ ሙሰልሰል(series) ኣል-ጃማዓ (The Brotherhood) season 1,Episode 1

Post by Abe Abraham » 26 Jan 2022, 12:23


ውድ ተመልኻቾች ፡ ኣል-ጃማዓ የሚል ስም የያዘ የተከታተልነው የ ብራዘርሁድ ሲሪስ እንደ ሰንሰለት ከወሰድነው 28 ቀለቤቶች ያቀፈ ነበር ። ዋናው የሙሰልሰሉ ገጸ-ባህርይ ሓሰን ኣል-በና ከህጻንነቱ ጀምሮ የስነ-ምግባርና የሃይማኖት ስሜት ስለ ነበረው ባደገበት መንደር ህብረተ-ሰቡን የኣላህ መንገድ እንዲከታተሉ ይገፋፋ ነበር ። ኣንዳንድ ጊዜ መንገዱን ጥሰዋል ለሚላቸው ሰዎችን ስም-የለሽ የመስፈራራት መልእክት ልኮ ኣንዳንድ ሰዎችን ቢያስደነግጥም ባብዛኞቹ የመንደሩ ነዋሪዎች ደህና ተቀባይነት ኣግኝቶ ነበር ።

ሆኖ ደሞ ቀስ በቀስ እንቅስቃሴውና የዳዕዋ (የሃይማኖት ጥሪ ) ስራው ከመንደሩ ውጭ ተስፋፍቶ ኣገር-ኣቀፍ ሊሆን በቃ ። ከዚያ የድርጅት ቅርጽ ይዞ " ጃማዓት ኣል-ኢኽዋን ኣል-ሙስሊሚን '' የሚል ስም ተሰጠው ። በኣል-ኢኽዋን የሚታወቁ የእንቅስቃሴው ጓዶች/ወንድማሞች ና መሪያቸው ሓሰን ኣል-በና በመጀመርያ ጊዜ እስከሚጠነክሩና ጠላት እንዳያበዙ -- በተለይ ከመንግስት -- ከፖለቲካ ርቀው በየዳዕዋ ስራ ብቻ እንዲሰማሩ ወሰኑ ።

ሆኖ ግን እንቅስቃሴው እያደገ በሄደ ቁጥር ሓሰን ኣል-በና እስልምና " ዲን ዎ ዳውላ " (ሃይማኖትና መንግስት/ኣስተዳደር እንበለው ...ወይም ምድራዊና መንፈሳዊ ) ከሚል ኣስተሳሰብ ተነስቶ ወደ የፖለቲካ ዓለም ለመግባት ወሰነ ። ይህ ኣቋም በድርጅቱ ኣለመግባባት ፈጥሮ መከፋፈል ኣስከተለ ። የዳዕዋ ብቻ ሰዎች መንገዳቸው ይዘው ሲሄዱ ሌሎች ግን ሓሰን ኣል-በና ራሱ ሊያስቆማቸው በማይችል ኣካሄድ የብራዘርሁድ የድብቅ ወታደራዊ ድርጅቱን ( ኣል-ተንዚም ኣል-ሲሪ ) ተቆጣጥረው የመንግስት ጥላቻ የሚጋብዙ የግድያ ተግባሮች ፈጸሙ ።

ለምሳሴ ኣል-ተንዚም ኣል-ሲሪ ከሓሰን ኣል-በና -- ማንኛውም የድርጅቱ ኣባል እንዲሰማውና እንዲታዘዘው ( ኣል-ሰምዕ ዎ ኣል-ጣዓ ) ቃል የገባለት ሰው -- ቀጥታዊ ትእዛዝ ሳይሰጣበት ኣሕመድ ኻዚንዳር የሚባለው ዳኛ/ጃጅ ገደለ ። የኣል-ተንዚም ኣል-ሲሪ መሪ ለምን ያለ ቀጥታዊ ትእዛዝ ዳኛውን ገደላችሁ ተብሎ ሲጠየቅ "ሓሰን ኣል-በና ብዙ የብራዘርሁድ ኣባሎችን የረዘመ የእስራት ፍርድ ለሚሰጠው ዳኛ "ከዚ ሰው የሚያላቅቀን ቢገኝ ጥሩ ነበር " ብሎ ሲናገር በመስማቴ ቀጥታዊ ትእዛዝ መሆኑን ስለተረዳኝና መታዘዝ እንዳለብኝ ግዴታየ መሆኑን ስለተገነዝብኩ ጉዳዩ እንዲፈጸም ኣደረግኩ ። "

የኻዚንዳር ግድያ መንግስትና ህዝብ ስላስቆጣ ኣንዳንድ የብራዘርሁድ ኣማካሪዎች ሓሰን ኣል-በናን ጉዳዩን ለማስረሳት ለምን ትልቅ ጸረ-እንግሊዝና ጸረ-ኣይሁድ ስራ ኣንሰራም የሚል ሃሳብ ኣቀረቡለት ። ሓሰን ኣል-በና ሃሳቡ ተቀብሎ በኣንድ መልእክት ኣቀባይ ለመንግስት የህዝባዊ ሰራዊት ጉዳይ ላከ ። የመንግስት ተወካይና የመልእክት ኣቀባይ ንግግር እንደዚህ ነበር ፥


መልእክት ኣቀባይ ፥ ኣል-ኢኽዋን የመንግስትን የፓለስታይን ጦርነት ለመደገፍ ከየመንግስት ሰራዊት ጎን ለጎን የሚዋጋ ህዝባዊ ሰራዊት ለማቅረብ ዝግጁ ነን ይላሉ ።

የመንግስት ተወካይ ፥ ትጥቁ ከማን ይሆናል ?

መልእክት ኣቀባይ ፥ ከራሳቸው ።

የመንግስት ተወካይ ፥ ከራሳቸው ከሆነ ሰራዊቱ የእርሳቸው እንጂ የህዝብ ሊባል ኣይችልም ። ከዚህ ባልተለየ ውግያ ገብተው ኣሸንፈው ወይም ተሸንፈው ቢመጡሳ ሰራዊቱ እዚ ተመልሶ ምን ያደርጋል ?

መልእክት ኣቀባይ ፥ ኣዎ ያን ኣላሰብኩለትም ።


ከዚያ ኣል-ተንዚም ኣል-ሲሪ ብዙ ሳይቆይ በግብጽ በሚገኙ የኣይሁዳውያን የቢዝነስ/ንግድ ተቋማት ላይ የቦምብ ጥቃቶች ይፈጽምና ድፍረቱ በፕራይም ምኒስተሩ ኑቕራሺ ባሻ ግድያ ያከትመዋል ። የዚህ መዘዝ ምን ነበር ? ብራዘርሁድን ኣግደህ በጨለማ እንዲንቀሳቀሱና የባሰ ኣደጋ እንደሚሆኑ ከማድረግ እንዳሉ ለቁጥጥር በሚመች ብንተዋቸው ይሻላል የሚሉ ሰዎች ስለ ተዳከሙ ኑቕራሺ ባሻን የተካ ሰው ብራዘርሁድን ህገ-ወጥ ድርጅት ብሎ እንዲኮንን ኣስገደደ ።

በ28 ቀለቤት መደምደምያ ኣንድ ወጣት የብራዘርሁድ ኣባል ሓሰን ኣል-በናን ሊጎበኝና ሊያጽናና ወደ ቤቱ ከሄደ፥

ሓሰን ኣል-በና ፥ መንግስት ኣል-ተንዚም ኣል-ሲሪን ክጄ የኣባላቱ ስሞችና የመሳርያዎቻቸውን መደበቅያ ቦታ ኣሳልፌ እንድሰጥ ከኔ ይጠይቃል ። እኔ እንደሱ ለማድረግ ኣልችልም፡ ይገድሉኛል ( ድርጅቱ)!! እኔ ኣሁን የብራዘርሁድ መሪ ነበር ነኝ( ታላቁ መሪ በብቸኝነት ተውጦ በሃዘን ወደ ማልቀስ እየተቃረበ )!

ሓሰን ኣል-በና ፥ ጊዜ ወደ ጓላ ቢመለስ እኔ ኣንድ መቶ የሚሆኑ ሰዎች ኣስተምሬ ( ሃይማኖት: ስነ-ምግባር ) -- ከፖለቲካ ፍጹም ርቄ -- ስሞት ኣምላኬን ፊት ልቀርብ በወደድኩ ነበር ። ( በሰማይ የበጎ ስራ ሂሳብ ሲደረግ ማለት ነው ። )

ወጣቱ ፥ ጊዜ ወደ ጓላ ኣይመለስም ።

ሓሰን ኣል-በና ፥ ኣዎ ! ስለዚ ኣምላክ ነደም/ጸጸት ፈጠረ ።

ብክፍል ሁለት የጀማል ዓብድ ኣ(ል)-ናስርና ሰይድ ቑጥብ ( ለሞት የተፈረደው) ዘመን እንገናኝ !!!

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 11599
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ሌላው የግብጽ ተስፋየ ገብረ-ኣብ ውድ ነፍስ-ሄር ወሒድ ሓምድ ፥ ሙሰልሰል(series) ኣል-ጃማዓ (The Brotherhood) season 1,Episode 1

Post by Abe Abraham » 28 Jan 2022, 16:32


  • ከኑቕራሺ ባሻ ግድያ በጓላ በቦታው የመጣው ፕራይም ሚኒስተር ኢብራሂም ዓብዱልሃዲ በቁጣ ለየጸጥታ ሃይሎች በየኣይጥ ጉድጓድ ሳይቀር ለተገኙት የብራዘርሁድ ኣባሎች ወደ እስራት ለመውሰድ ባስተላለፈው ትእዛዝ ብዙ የኢኽዋን ኣል-ሙስሊሚን ኣባሎች ወደ ወህኒ-ቤት ተላኩ ።

    እዛ በነበሩበት ጊዜ - ብዙ ሳይቆዩ - የመሪያቸው ኣል-ሙርሺድ ሓሰን ኣል-በናን ኣሳዛኝ ሞት ደረሳቸው ። ዜናው እንዲህ ይላል ፥ ሓሰን ኣል-በና የኢኽዋን ኣል-ሙስሊሚን መሪ በጎደና በኣንድ ሰው በጥይት ተመትቶ ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በጓላ ከዚች ዓለም በሞት ተለየ ። ሁለተኛው ክፍል የ ኣል-ጃማዓ ከዛ ይጀምራል ።

    ኣል-ኢኽዋን በቀላሉ እጃቸው የሚሰጡ ሰዎች ስላልሆኑ ኣዲሱ መሪያቸውና የድርጅታቸው ኣካሄድ እንዴት እንደሚመስሉ በሚከተሉ የታሪኩ ሰንስለት ቀለቤቶች እናያለን ። ከዋና የሙሰልሰሉ ገጸ-ባህርያቶች ፥ ጀማል ዓብደልናስርና ሰይድ ቑጥብ( በየጤና ችግር እየተሰቃየ በገነባው የከረረ የሃይማኖት ኣስተሳሰብ ራሱን ወደ የሞት ቅጣት የመራ የስነ-ጽሁፍ ወዳጅ ። የሃይማኖት ኣተናተኑ የስነ-ጽሁፍ መልክ ይዞ ኢያለ ደራሲው ሰይድ ቑጥብ ራሱ እንደ የእስልምና ፈላስፋ ይቆጥር ነበር ። ስነ-ጽሁፍና ሃይማኖት ሲደባለቁ እስከ ምን ያህል ኣደጋ እንደሚያስከትሉ ሰይድ ቑጥብ ትልቅ ምሳሌ ነው። የሰይድ ቑጥብና የ ኢብን ተይሚያ ጽሁፎች በየሃይማኖት ኣክራሪዎች የተወደዱ ናቸው። ሁለቱ ጸሃፊዎች ሳያገቡና ልጆች ሳይወልዱ ከዚች ኣለም በሞት ተሰናበቱ። )

ኣል-ጃማዓ SEASON TWO, Episode 01ኣል-ጃማዓ SEASON TWO, Episode 02ኣል-ጃማዓ SEASON TWO, Episode 03gearhead
Member+
Posts: 5351
Joined: 08 Jun 2014, 16:29

Re: ሌላው የግብጽ ተስፋየ ገብረ-ኣብ ውድ ነፍስ-ሄር ወሒድ ሓምድ ፥ ሙሰልሰል(series) ኣል-ጃማዓ (The Brotherhood) season 1,Episode 1

Post by gearhead » 12 Feb 2022, 13:28

Abe...too sad to see that the amhara psychosis has rubbed off on you!😂😂😂. At least they know their case and own it;but what does one make of shabia goons who were just as much a victim of this social pathology acting out crazy?

Tesfaye Gebreab's characters were profiled in a plethora of post-colonial studies, long before he put them in amharic books. These are not characters of his own making but characters that exist in reality.

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 11599
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ሌላው የግብጽ ተስፋየ ገብረ-ኣብ ውድ ነፍስ-ሄር ወሒድ ሓምድ ፥ ሙሰልሰል(series) ኣል-ጃማዓ (The Brotherhood) season 1,Episode 1

Post by Abe Abraham » 12 Feb 2022, 14:23

gearhead wrote:
12 Feb 2022, 13:28
Abe...too sad to see that the amhara psychosis has rubbed off on you!😂😂😂. At least they know their case and own it;but what does one make of shabia goons who were just as much a victim of this social pathology acting out crazy?

Tesfaye Gebreab's characters were profiled in a plethora of post-colonial studies, long before he put them in amharic books. These are not characters of his own making but characters that exist in reality.
Gearhead,

The characters of Wahid Hamid to use your words " are not of his own making but characters ( of the brotherhood ) that existed in reality. " That is to say : I am sharing with you the reality.

The reality is so real that a group of Eritreans once visited ማእሙን ኣል-ሁደይቢ ( the son of ሓሰን ኣል-ሁደይቢ, legal scholar and the leader of the brotherhood portrayed in the second part of the series ..) to talk about tegadalay/al-mounadil Issaias Afeworki Abraham ( my uncle ). The great man asked them : what is Issaias Afeworki doing ? When they replied that he was fighting for the liberation of Eritrea he advised them : you should join him.


.

Post Reply