Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Naga Tuma
Member+
Posts: 5006
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ግብፅ፣ ግብጥ፣ ገበጣ፣ ገበታ፣ ማረም ጅጆ ገበታ

Post by Naga Tuma » 25 Dec 2021, 23:48

ማረም ጅጆ ገበታ ሲባል ስሰማ ነዉ ያደኩኝ። ግብፅ የሚለዉ ቃል የመጣዉ ግብጥ ከሚለዉ ነዉ ሲባል በቅርቡ ያነበብኩኝ ይመስለኛል።

በልጅነቴ ጠጠሮችን ስምንት ወይም ስምንት አከባቢ ጉድጓዶች ዉስጥ የመለዋወጥ ጫወታን መጫወቴን ኣስታዉሳለሁ። ስሙ የገበጣ ጫወታ መሆኑን በዉል ኣላስታዉስም።

ትላንትና ኣንድ ዶክመንታሪ ሳይ ኣንድ ሜሪኣን የምትባል የጥንት ግብፅ መሪ እንደነበረች ሰማሁ። ወድያዉ በልጅነቴ ማራም ጅጆ ገበታ ሲባል የሰማሁትን ኣስታወስኩኝ። ከዛም ግብጥ እና ገበታ የሚሉትን ቃላት መመሳሰል ኣሰብኩ።

ስለዚህ ማረም ጅጆ ገበታ ማን ነበረች የሚለዉን ጥያቄ ማቆም ኣልቻልኩም።

Abe Abraham
Senior Member
Posts: 11599
Joined: 05 Jun 2013, 13:00

Re: ግብፅ፣ ግብጥ፣ ገበጣ፣ ገበታ፣ ማረም ጅጆ ገበታ

Post by Abe Abraham » 25 Dec 2021, 23:54

Naga Tuma,

  • Is there a website that teaches the Oromo language preferably with audio or video material ?

Naga Tuma
Member+
Posts: 5006
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ግብፅ፣ ግብጥ፣ ገበጣ፣ ገበታ፣ ማረም ጅጆ ገበታ

Post by Naga Tuma » 26 Dec 2021, 01:47

Abe Abraham,

Is there a website that teaches Tigrigna preferably with audio and video?

Ok, I am kidding.

I don't know of one that is currently online. Then again, I haven't taken the time to explore if one exists currently. However, I continue to ask myself why those of us who are Afan Oromo speakers that participate in this forum do not make Afan Oromo a presence like Amharic and Tigrigna speaking participants.

On another note, kidding aside, I was seriously wondering about Eritrean culture when I came across this thread yesterday: Question For Eritrean Brothers - what kind of cultural event is this?

Of particular interest to me was the word ሀማዉቲ which sounded similar to አማቲ. Add to that the words ማቲ፣ ኣዴ፣ ጉራመሌ/ጉራማይሌ፣ እልልታ, and so on.

Having said that, perhaps if there are specific lines that you wish to learn, I hope I will be able to share how to say them.

Horus
Senior Member+
Posts: 23263
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግብፅ፣ ግብጥ፣ ገበጣ፣ ገበታ፣ ማረም ጅጆ ገበታ

Post by Horus » 26 Dec 2021, 03:32

ናጋ ቱማ
አፋን ኦሮሞ በላቲን እና በማይታወቅ ሰዋስው (ሲንታሽ) ና እስፐሊንግ (አናባቢ) እስከ ተጻፉ ድረስ በቋንቋው አፍ ያልፈቱና ቁቤን ያልቆጠሩ በፍጹም ወደ ቋንቋው መግቢያ መስኮት የላቸው ። ሌላ ቦታ እንደ ነገርኩህ ምልክት አለትርጉም ዋጋ የለውም 'ጨው' የሚለው ምልክት አንድ ነጭ የሚጣፍጥ ማ ዕድን ስላመለከተ ብቻ ነው ጨው የሚለው ቃል ስሜት የሚሰጠን። ስለዚህ ይህን ችግር የምፈታው ካልቸር ነው ። ሌላው ምልክቶቹ የጋራ ሲሆኑ ነው ። አማርኛና ትግርኛ የሚግባቡ ቋንቋዎች አይደለሉም ግ ን ሁለቱን በግ ዕ ዝ ፊደል ስለተጻፉ ላዲስ ተማሪ መግቢያ መስኮት አለው ። እዚህ ላይ ምልክት እሳኝ ነው ። አንዱ በትርጉም መግባባት ነው ፣ ሌላው በምልክት መግባባት ነው። ለምሳሌ በላቲን ፊደል ያደገ ሰው 'boy' & 'booyy' ሲል ፍጹም የተለያዩ ነገሮች ናቸው ። ባንድ ቃል በላቲን ድግግሞሽ ሰውስው የተጻፈ አፋን ኦሮሞ በፍጹም ማንበብ አስቸጋሪና ሌላው ሰው ቋንቋውን እይዳይማር የደረገ ግዙፍ ስህተት ነው።

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: ግብፅ፣ ግብጥ፣ ገበጣ፣ ገበታ፣ ማረም ጅጆ ገበታ

Post by Guest1 » 28 Dec 2021, 10:08

እንደገና
የጥንት ስሟ ሂኩፕጣ ነበር። ግሪኮች ሲቸግራቸው ኤግብቶስ አሉ ትርጉም ጥቁር መሬት። በእንግሊዞች ኢጂፕት ሆነ ይባላል። ዊኪ ወክውክው የጥቁር ህዝብ ስም አያነሳም። ጁዎችንም። ከስሜን አፍሪካ ጋርም ግንኙነት እንደሌላቸው ለማስረገጥ ይፈልጋል። ጥቁር የተባለው ምክንያቱ በአባይ አካባቢ ያለው ጥቁር መሬት ነው ምንም እንኳን ግብጽ ቀይ መሬት ቢትሆንም ይላል ክክክክክክክ

መስር ከወሰን ጋር የተያያዘ ነው። ከአባይ በስተምስራቅ የነበሩት መስር፤ በስተምእራብ ሊቢያንስ ይባሉ ነበር። ራሳቸውን ከግብጽ ለመለየትም ሳይሆን አይቀርም። ዛሬም መስር ነን ይላሉ። መስሪ ሰው የሆነ ማለትም ነው ይባላል። ለኑቢያን የሚጠቀሙት ተራ ስድብም አለ። የግብጽ ታሪክ ጸሃፊዎች በጠቅላል ማለት ይቻላል የጻፉት ውሸት ነው። ገበታ እንደ ገበጣ ጎድጓዳ የሆነ ሳህን በሸክላ ወይም በእንጨት የተሰራ። ይልቅ የገበታን ጉዳይ ከግእዝ መፈለጉ ይበጃል።

ከጊዜ ብኋላ በናሽናሊዝሞ ሁሉም መስሪ ሆኑ። በዝህ ከቀጥልን ወደ ሃይማኖትም ልንገባነው! አሁን ማጆሪቲ። ማይኖሪቲ የሚባሉት ክርስቲያን ኮፕቲኮች ግሪኮች በስደተኝነት ሱዳኖች እና ኢትዮና ኤርትራዊያን ይጠቀሳሉ። ኒቢያንስ መስሪ ሆነዋል ክክክክክክክክክክክክክ

መጨረሻ ላይ ቀለሜዋ ነው ጉዳዩ ምን? ዋናው ነገር ገበጣ እየቆጠሩ ከእውነት ከመራቅ አገርን ማስፋት ነው። ወቸ ጉድ!!!

Naga Tuma
Member+
Posts: 5006
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ግብፅ፣ ግብጥ፣ ገበጣ፣ ገበታ፣ ማረም ጅጆ ገበታ

Post by Naga Tuma » 30 Dec 2021, 04:12

Horus wrote:
26 Dec 2021, 03:32
ናጋ ቱማ
አፋን ኦሮሞ በላቲን እና በማይታወቅ ሰዋስው (ሲንታሽ) ና እስፐሊንግ (አናባቢ) እስከ ተጻፉ ድረስ በቋንቋው አፍ ያልፈቱና ቁቤን ያልቆጠሩ በፍጹም ወደ ቋንቋው መግቢያ መስኮት የላቸው ። ሌላ ቦታ እንደ ነገርኩህ ምልክት አለትርጉም ዋጋ የለውም 'ጨው' የሚለው ምልክት አንድ ነጭ የሚጣፍጥ ማ ዕድን ስላመለከተ ብቻ ነው ጨው የሚለው ቃል ስሜት የሚሰጠን። ስለዚህ ይህን ችግር የምፈታው ካልቸር ነው ። ሌላው ምልክቶቹ የጋራ ሲሆኑ ነው ። አማርኛና ትግርኛ የሚግባቡ ቋንቋዎች አይደለሉም ግ ን ሁለቱን በግ ዕ ዝ ፊደል ስለተጻፉ ላዲስ ተማሪ መግቢያ መስኮት አለው ። እዚህ ላይ ምልክት እሳኝ ነው ። አንዱ በትርጉም መግባባት ነው ፣ ሌላው በምልክት መግባባት ነው። ለምሳሌ በላቲን ፊደል ያደገ ሰው 'boy' & 'booyy' ሲል ፍጹም የተለያዩ ነገሮች ናቸው ። ባንድ ቃል በላቲን ድግግሞሽ ሰውስው የተጻፈ አፋን ኦሮሞ በፍጹም ማንበብ አስቸጋሪና ሌላው ሰው ቋንቋውን እይዳይማር የደረገ ግዙፍ ስህተት ነው።
ሆረስ፥

የላቲን ኣልፋቤት ከእኛዉ ፊደሎች ጋር መመሳሰል ኣስተዉዬ ኣልሸሹም ዞር ኣሉ ብዬ ኣፋን ኦሮሞን በእኛዉ ፊደል መፃፍ ከጀመርኩ ሰንብቻለሁ። ያም ብቻ ሳይሆን ኣፋን ኦሮሞን የምንናገር እዚህ መድረክ ላይ በእኛዉ ፊደል ብንጽፍ ኣማርኛን፣ ትግርኛን፣ ጉራግኛን፣ እና ሌሎችንም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የሚናገሩ ኢትዮጵያዊያን ቋንቋዉን ለመማር የበለጠ ይቀናቸዋል ብዬ ኣስባለሁ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 5006
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ግብፅ፣ ግብጥ፣ ገበጣ፣ ገበታ፣ ማረም ጅጆ ገበታ

Post by Naga Tuma » 30 Dec 2021, 04:26

Guest1 wrote:
28 Dec 2021, 10:08
እንደገና
የጥንት ስሟ ሂኩፕጣ ነበር። ግሪኮች ሲቸግራቸው ኤግብቶስ አሉ ትርጉም ጥቁር መሬት። በእንግሊዞች ኢጂፕት ሆነ ይባላል። ዊኪ ወክውክው የጥቁር ህዝብ ስም አያነሳም። ጁዎችንም። ከስሜን አፍሪካ ጋርም ግንኙነት እንደሌላቸው ለማስረገጥ ይፈልጋል። ጥቁር የተባለው ምክንያቱ በአባይ አካባቢ ያለው ጥቁር መሬት ነው ምንም እንኳን ግብጽ ቀይ መሬት ቢትሆንም ይላል ክክክክክክክ

መስር ከወሰን ጋር የተያያዘ ነው። ከአባይ በስተምስራቅ የነበሩት መስር፤ በስተምእራብ ሊቢያንስ ይባሉ ነበር። ራሳቸውን ከግብጽ ለመለየትም ሳይሆን አይቀርም። ዛሬም መስር ነን ይላሉ። መስሪ ሰው የሆነ ማለትም ነው ይባላል። ለኑቢያን የሚጠቀሙት ተራ ስድብም አለ። የግብጽ ታሪክ ጸሃፊዎች በጠቅላል ማለት ይቻላል የጻፉት ውሸት ነው። ገበታ እንደ ገበጣ ጎድጓዳ የሆነ ሳህን በሸክላ ወይም በእንጨት የተሰራ። ይልቅ የገበታን ጉዳይ ከግእዝ መፈለጉ ይበጃል።

ከጊዜ ብኋላ በናሽናሊዝሞ ሁሉም መስሪ ሆኑ። በዝህ ከቀጥልን ወደ ሃይማኖትም ልንገባነው! አሁን ማጆሪቲ። ማይኖሪቲ የሚባሉት ክርስቲያን ኮፕቲኮች ግሪኮች በስደተኝነት ሱዳኖች እና ኢትዮና ኤርትራዊያን ይጠቀሳሉ። ኒቢያንስ መስሪ ሆነዋል ክክክክክክክክክክክክክ

መጨረሻ ላይ ቀለሜዋ ነው ጉዳዩ ምን? ዋናው ነገር ገበጣ እየቆጠሩ ከእውነት ከመራቅ አገርን ማስፋት ነው። ወቸ ጉድ!!!
Guest1:

እንኳን ጥያቄዬ ግምቴ የተሳሳተ ከሆነ ለመታረም ሁሌም ዝግጁ ነኝ። ሂኩጥጣ በምን ቋንቋ እንደሆነ ብታስረዳን የበለጠ ይረዳል።

Guest1
Member
Posts: 1926
Joined: 28 Dec 2006, 01:02

Re: ግብፅ፣ ግብጥ፣ ገበጣ፣ ገበታ፣ ማረም ጅጆ ገበታ

Post by Guest1 » 30 Dec 2021, 11:29

ህውትካፕታ ሆነ ግብቶስ የጥቁር መሬት/አገር ግብቶስ ግብትስ ግብጥ ኮፕት Coptic ግብጾች የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ። እስልምና ተስፋፋ። መስሪ የመጽሃፍ ቅዱስም ይባላል። በቅዱስ ቁርአንም ሳይኖር አይቅርም። ግሪኮች /ጅ/ አልፋቤት የላቸውም እንግሊዞች አመሳስለው ኢጂብት አሉ።

አረቦች ወይም ነጮች ወደ ኢጂፕት የመጡት መቼ ነው? በጣም ረጅም ጊዜ ነው። ቱርኮች ፍርኦኖች ይሏቸዋል። ክክክክክክ ሆኖም ዲኤንኤ ወዘተርፈ... የተባለው አንዱንም ማመን አይቻልም። መርማሪዎቹ ይዘበራርቁታል። ታሪኩም እንደዝሁ።

ማረም ጆጅ ገበታ የጨዋታው ስም ከሆነ አንተ ያልከውም ትክክል የማይሆንበት ምክንያት የለም። ከግብጽ=ግብትስ= ግብት=ገበጣ=ገበታ። በሰሜትካዊ ቋንቋ መስሪ ጎርፍ ማለትም ነው። አገራችን እንደጎርፍ ገብተው በማጥለቅለቃቸው ሳይሆን አይቀርም በኦቶማን ወረራ ዘመን ክክክክክክ

የግል አስተያየት
ግብጽ ጥቁር መሬት እንደተባለው የጥቁሮች መኖሪያ ነበር። ነጮች ወረው ንጉሶቻቸው ሆኑ። ስሜን አፍሪካ ጠረፍ ወሃው ያለበት ሁሉ ያዙ። ከመካከለኛው ምስራቅ ግሪክና ሮማዊያንና ፐርዢያን/ኢራንና አሁዶች። ፊኖዢያንስ አይሁዶች ነበሩ አላውቅም። ጥቁሩ ወደ በረሃው ሱዳንና ኢትዮጵያ ተሰደደ። ለፕርዥያው ንጉስ ባሮች ይላክለት ነበር በግሪኩ? ንጉሳቸው ይሆን? የኑቢያ አጻጻፍ የግሪክ አልፋቤት ይመስላል የአፍሪካ የኑቢያ ተብሎ ጎግል ማድረግ ይቻላል። በነገራችን ላይ ግዕዝም የተገለበጠ የግሪክ አልፋቤት ነው የሚሉ አሉ። ወይ ጉድ! ክክክክ

አረቦችና አይሁዶች ባሪያ ነጋዴም ነበሩ። በአውሮፓም የነጭ ባሮችም ነበሩ ነበሩ አሁንም አሉ ክክክክክ። ሁሉም በኣይድሎጂና ኢዲዮሎጂ ክክክክክ ወይም በአስትሮኖሚ እየተመሩ ክክክክክክክ የባሪያና የጌታ ስርኣት ፈጠሩ። ምን የተቀየረ ነገር አለ? ሶሻሊስቶች መጡ። እነሱም ከግል ጥቅም መውጣት አልቻሉም። ወደቁ።

የቃል አመጣጥ ወዘተ ታሪክም ጭምር ማጥናት እንችላለን። ባለፈው ታሪክ ጸሃፊ በተለይ የነዛን ማመን ወይም የበላዮቻችንን ማመን ያዳግታል። የአሜሪካ ጥቁሮች ብዙ ጥናቶች አላቸው። ይህ የታሪክ ተማሪ ስራ ነው። ታሪክም ከተዛባ ዲኤንኤም ማዛባት ከተቻል ምን ቀረ? ቀለም። ዛሬም እህቶቻችን የአረብ ማዳም ገረዶች ናቸው። ቀጥሏል። የጊዜው ጥያቄ እስከመቼ? ከጥቁር ህዝብ ጋር ትሰለፋለህ አትሰለፍም? ማነው ተጠያቂ የተማረው ክፍል ነዋ! እንዴ!

Naga Tuma
Member+
Posts: 5006
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ግብፅ፣ ግብጥ፣ ገበጣ፣ ገበታ፣ ማረም ጅጆ ገበታ

Post by Naga Tuma » 30 Dec 2021, 21:07

ለማብራርያህ ኣመሰግናለሁ።

ማረም ወይም ማራሚ የሴት ስም ነዉ። ማርያም፣ መሬማ፣ ሜሪ እንደሚባለዉ።

ማረም ጅጆ ገበታ በታሪክ ዝና ያተረፈች ሴት ናት። ያን ከአፈታሪክ ከልጅነት ጀምሮ ኣዉቅ ነበር።

እስከኣሁን ራሴን ስጠይቅ የኖርኩኝ ማረም የሚለዉ ስም መፅሓፍ ቅዱስ ማርያም ከሚለዉ ኣንድ መሆኑ የተወረሰ ነዉ ወይ ያሚል ነበር።

የጠቀስኩኝ ዶክመንታሪ ሜሪኣን ከክርስትና በፊት የወጣ የዝናኛ ግብጣዊት ሴት ስም መሆኑን ያመለክታል። ስለዚህ ኣዲሱ ጥያቄዬ ማረም ጅጆ ገበታ የመፅሓፍ ቅዱሱ ማርያም በፊት ወይስ በሁዋላ የኖረች ናት ነዉ። በኣጭሩ ጥያቄዬ የክሮኖሎጂ ጥያቄ ነዉ።

ትንታኔህ የትኛዉ ዘመን ላይ ያተኮረ መሆኑን በደንብ መለየት ኣልቻልኩም። ፕራሚዶች ሲገነቡ የነበረ የፈረኦኖች ዘመን ነዉ? ስደተኛዉ ፈረኦን ሙሴ ሆኖ ቶራን ካወጀበት እስከ ክርስትና ሰበካ መጀመር ዘመን ነዉ? ከክርስትና ሰበካ መጀመር እስከ ኣዉሮፓ የዛሬ ኣንድ ሺህ አመታት ገደማ የዕዉቀት ቅስቀሳ በሁዋላ ያለዉን ዘመን ነዉ?

እነዚህን ዘመናት በዉል ያልለየ ታሪክ ኣስተዉለህ እንዳልከዉ መዘበራረቁ ኣይቀሬ ነዉ። ዘመናቱን በዉል የለየ ታሪክ ወጥ መሆኑ የምያጠራጥር ኣይመስለኝም።

Horus
Senior Member+
Posts: 23263
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ግብፅ፣ ግብጥ፣ ገበጣ፣ ገበታ፣ ማረም ጅጆ ገበታ

Post by Horus » 30 Dec 2021, 21:56

ናጋ ቱማ፣
ስለ አፋን ኦሮሞ መጻፊያ ግዕዝ ፊደል መምረጥህ በጣም ትክክል ነው ። በጣም ግዜ ቆጥብና ፈጣን መሳሪያ ነው ። ለምሳሌ Gaammaaccu ውሰድ፤ የተኞቹ ፊደሎች መደገም እንዳለባቸው የሲንታክስ ሕግ የለም፤ ቃሉ ረጅም ነው ፤ አናባቢው (ቫውሉ) A ይሁን O የድምጽና አክሰንት ሕግ የለም ። አሁን አስገራሚው ግዕዝን ተመልከት፤ ገመቹ (3 ፊደል) ጋማቹ (3 ፊደል) In the Ge'ez system sounds are immutable. There is only 1 ገመቹ sound or 1 ጋማቹ sound! This is powerful even compared the syntax of English words. The Ge'ez system is the only one with no spelling and pronouncing problems at all. For those uniquely Oromo sounds, add certain marks on the existing Fidel same as Tigrgna, Guragegna Fidel tables.

As for the meaning of the name 'Egypt', there only two to decide from one is 'The House of the Spirit of Ptah. Ptah was the god of creativity. This is precisely the Ethiopic word ፈጣሪ with exactly the same meaning to this day. The other is ' Land of the Nile'. This is also very strong possibility. The Egyptian god the Nile was called 'Hapi' from which our glorious አባይ ወንዝ comes from.

The existing philological challenge is this: 'land; or 'earth' in the ancient kebt was 'ghe, ge' the Ethiopic ጌ፤ አዲስጌ፣ ጉራጌ፣ ግርጌ .. which could be the ጀ in the word 'Egypt'. If this is true, then Egypt means Land of the Nile. On the other account, Ka means 'spirit, Soul or ghost'. If ka was 'ጀ' then Egypt would mean house of the Creative Spirit.

ከነዚህ ከሁለቱ ውጭ ለመገመት የሚያችል የቋንቋ መሰረት ወይም ኤቪደንስ የለም ፤ ማለት ከምት፣ ከፕት፣ ግብጽ፣ ጂፕት፣ አይጂፕት፣ ኢጂፕት የተባሉትን ቃላት ዲኮድ ስናደርግ ማለት ነው ።
በአ ሆረስ

Naga Tuma
Member+
Posts: 5006
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ግብፅ፣ ግብጥ፣ ገበጣ፣ ገበታ፣ ማረም ጅጆ ገበታ

Post by Naga Tuma » 20 Jan 2022, 20:18

Abe Abraham,

ለምሳሌ ያህል የሚከተሉት ቃላት በትግርኛ ቋንቋ ብዙ ወይም ብዙሃን (plural) የሚጠሩት ወይም የሚጻፉት እንዴት ነዉ?

አፋን ኦሮሞ (singular)
አባ
ወገነ
ሰበ
ጋረ

አፋን ኦሮሞ (plural)
አቦተ
ወገኖተ
ሰቦተ
ጋሮተ

ኣማርኛ (singular)
ኣባት
ወገን
ስብ
ጋራ

ኣማርኛ (plural)
ኣባቶች
ወገኖች
ሰቦች
ጋራዎች

Naga Tuma
Member+
Posts: 5006
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ግብፅ፣ ግብጥ፣ ገበጣ፣ ገበታ፣ ማረም ጅጆ ገበታ

Post by Naga Tuma » 18 Feb 2022, 19:48

Abe Abraham ወይም ሌሎች ትግርኛ ተናጋሪዎች፣

በትግርኛ አቦታት በኣማርኛ አባቶች እንደሚባለዉ ይመስለኛል። ልክ ነዉ?

ልክ ከሆነ አቦታት በኣማርኛ አባቶች ከሚለዉ ይልቅ በአፋን ኦሮሞ አቦተ ከሚለዉ ጋር የበለጠ ይቀራረባል ማለት የሚቻል ይመስለኛል። ለምን የሚለዉ ሌላ ጥያቄ ነዉ። የቦረና እና ግዕዝ መዝገበ ቃላት ቢኖር መመለስ የሚችል።

Post Reply