Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የተሸጠው ነገ ... | ነዳጅ በሊትር 6 ብር መጨመሩ በታሪክ ከፍተኛው ነው - እያንዳንዱ ሸቀጦች ላይ በቀጣይ የዋጋ ጭማሪዎች ይጠበቃሉ

Post by sarcasm » 08 Dec 2021, 20:11

የተሸጠው ነገ ...

ነዳጅ በሊትር 6 ብር መጨመሩ በታሪክ ከፍተኛው ነው 🤔 በትራንስፖርት ሴክተር ላይ ጥገኛ የሆነው የሀገራችን ኢኮኖሚ እያንዳንዱ ሸቀጦች ላይ በቀጣይ የዋጋ ጭማሪዎች ይጠበቃሉ። ህብረተሰቡ በቀን ቀን የሚጠቀማቸው ቅንጦት ያልሆኑ ሸቀጦች ላይ ደግሞ የዋጋ ንረቱ ጣሪያ ይነካል።

ሁሉም የኢኮኖሚ ሴክተሮች በጦርነቱ ምክንያት ሞተዋል። ለመቀስቀስ እንኳን አንዱ ከአንዱ የተሻለ ሁኔታ የለውም። አቡቹ እንደምንም የጦርነቱን የሿሿ ውጤት ተጠቅማ የደስደስ አንድ ሚሊየን ዳያስፖራ አስገብታ ለማለብ ጥሪ አቅርባለች።

እንግዲህ የዲያስፖራው አመጣጥ የቱሪዝም ሴክተሩንና የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ካቃለል የሚል ስሌት አለው። ነገር ግን የህፃን ልጅ ውሳኔ ይመስላል።
አንድ ሚሊየን አይደለም 50 ሺህ ዳያስፖራ ሊመጣ አይችልም። የቱሪዝሙ ሴክተር በሀገራችን አጠቃላይ ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ይመሰረታል እንጂ በሰዎችን የጉዞ እንቅስቃሴ ብቻ መሻሻሎችን ሊያመጣ አይችልም።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ደግሞ ሀገሩን የሚወደው አደባባይ ላይ ባንዲራ በማውለብለብ ብቻ ነው። ዶላሩን ከጀርባ በጥቁር ገበያ ነው የሚያጣራው።

ብቻ ጦርነቱ እየቆመ ሀገሪቷ እየተረጋጋች ስትመጣ ከፖለቲካው ቀውስ በላይ ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ጆሮገብ እየሆኑ ይመጣሉ።

በተለይ ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶች ሲጨምሩ ይህንን የሚሸከም ብሔራዊ ኢኮኖሚ ስለሌለን ወይም በጦርነቱ ምክንያት ስለደቀቀ በአቅርቦትና በፍላጎት መካከል የሰማይና የምድር ልዩነቶች ይፈጠራሉ። የውድድር ሳይሆን የሽሚያ ኢኮኖሚ እየተፈጠረ ሲሄድ የዋጋ ንረቶች ዘግናኝ ይሆናሉ።
ይህንን በምን እንደምንቋቋመው የኢትዮጵያ አምላክ ነው የሚያውቀው 😂 ... "እሱ የከፈተውን ጉሮሮ እሱ ይደፍነዋል" .. የሚልና ኢኮኖሚያዊ ጣዕሞችን ከመብላትና በሰላም ከመተኛት ጋር የሚያያይዘው አብዛኛው ህዝብ ምንም ላይመስለው ይችላል።

በእርግጥ .. "እንበላለን እንተኛለን" ...ነገር ግን ያማረ የህይወታችንን ዛሬና ነገአችንን ብሎም ለልጆቻችንና ለቀጣይ ትውልድ ማስረከበ የነበረብንን ምቹ ሀገራዊ ሁኔታዎችን መስጠት አንችልም።

Finfinme Times
Please wait, video is loading...

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: የተሸጠው ነገ ... | ነዳጅ በሊትር 6 ብር መጨመሩ በታሪክ ከፍተኛው ነው - እያንዳንዱ ሸቀጦች ላይ በቀጣይ የዋጋ ጭማሪዎች ይጠበቃሉ

Post by sarcasm » 09 Dec 2021, 12:07

አንድ ሰዉ 3 ብር እየከፈለ ቤንዚን ሊትር 32 ብር ገዝቼ አልችልም ባጃጅ ሚገዛ ካለ በፈጠራቹ 😥

Please wait, video is loading...

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: የተሸጠው ነገ ... | ነዳጅ በሊትር 6 ብር መጨመሩ በታሪክ ከፍተኛው ነው - እያንዳንዱ ሸቀጦች ላይ በቀጣይ የዋጋ ጭማሪዎች ይጠበቃሉ

Post by sarcasm » 10 Dec 2021, 09:30

😂
Please wait, video is loading...


Post Reply