Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 33284
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

^^^(((BREAKING NEWS)))^^^Videos Of:ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የመጀመሪያ ዙር ዘመቻቸውን አጠናቀው ወደ ቢሮ ተመለሱ!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 08 Dec 2021, 08:42


==========================================================================================================

==========================================================================================================
Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/
alS7306u76ho0fcltled ·
“በድል የታጀበው የመጀመሪያው ምእራፍ” በሚል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ያስተላለፉት መልዕክት ዋና ዋና ነጥብ ‼
👉 ኢትዮጵያን መገዳደር ይሞከር ይሆናል። ተገዳድሮ ማሸነፍ ግን ትናንትም አልተቻለም፤ ዛሬም አይሆንም፤ ነገም አይቻልም፤
👉 ኢትዮጵያ የሚለው ስም ሁሌም ከአሸናፊነት ጋር የተያያዘ ነው፤
👉 ከጥቂት ጊዜያት በፊት ኢትዮጵያን ሊወጋ የተነሳውን ጠላት በጋራ ሆነን እንድንመክት ጦር ግንባር ላይ የያዝነው ቀጠሮ ጠላትን አንገት ሲያስደፋ ኢትዮጵያን ቀን አድርጓታል፤
👉 ሀገራችን ታፍራና ተከብራ እንድትኖር ለማድረግ በጦር ግንባር እየተከፈለ ያለው መስዕዋትነት የኢትዮጵያን የአሸናፊነት ስም የሚመልስ መሆኑን አበስራለሁ፤
👉 ያቀረብኩትን ጥሪ ተቀብላችሁ ሕይወታችሁን፣ ጉልበታችሁን፣ ሀብታችሁን፣ ዕውቀታችሁን፣ ጊዜያችሁንና ሞያችሁን ለሠጣችሁ ሁሉ በኢትዮጵያ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ፤
👉 የመጀመሪያውን ምእራፍ አጠናቅቄ ለተወሰኑ ጊዜያት ወደ ቢሮ መመለሴን እገልጻለሁ፤
👉 ዛሬም ሆነ ወደፊት ጠላቶቻችን ጉልበታቸው ዝሎ፣ የጥላቻና የጠበኝነትን መንገድ ጥለው፣ የፍቅርና የሰላምን መንገድ እስኪመርጡ ትግላችን ይቀጥላል፤
👉 የእኛ ፍላጎት ሁሌም ሰላምና ፍቅር ነው፤
👉 ነገሮች ያለቁና የተጠናቀቁ እስኪመስሉ ድረስ ኢትዮጵያን የማያውቁ ሁሉ በሥጋትና በፍርሐት ተውጠው ነበር፤
👉 ሠግተው ሊያሠጉን፤ ፈርተው ሊያስፈራሩን የሞከሩ የውስጥና የውጭ አካላትም ነበሩ፤
👉 የኢትዮጵያን የአሸናፊነት ምሥጢር የሚያውቁት ብቻ በጽናት እስከ መጨረሻው የቆሙበት አጋጣሚም ተፈጥሮ ነበር፤
👉 ወደ ትግል የገባነው ሐቅን ይዘን ነውና የኢትዮጵያ አምላክ እንደ ወትሮው ከእኛ ጋር ነበር፤
👉 ልባችንን አጀግኖ የኢትዮጵያን አሸናፊነት በዓይናችን አሳይቶናል፤
👉 ውድቀታችንን ሲመኙ የነበሩትን ሁሉ አሳፍሮ ዳግም የኢትዮጵያን ስም በወርቅ ቀለም እንድንጽፍ አስችሎናል፤
👉 ማንም ተነስቶ ኢትዮጵያን ማውረድ ከማይችልበት ማማ ላይ እየሰቀልናት ነው፤
👉 ከገጠመን ፈተና ይልቅ በዕድሎቻችን ላይ አተኩረን ከሠራን ኢትዮጵያን ኃያልና ራሷን በሁሉም መስክ የቻለች ሀገር እናደርጋታለን፤
👉 ከፈጣሪ ቀጥሎ በፈተናችን ጊዜ አብረውን ለቆሙ እና በዓለም አደባባይ ለተማገቱልን ሁሉ ኢትዮጵያ ከፍ ያለ ምስጋና ታቀርባለች፤
👉 በህልውና ዘመቻው ወቅት ያየነውን የኢትዮጵያውያንን አንድነት እስከ ዓለም ፍጻሜ ሀብታችን አድርገነው መቀጠል አለብን፤
👉 ትግሉ ገና አልተጠናቀቀም። ነጻ ያልወጡ አካባቢዎች አሉን፤
👉 የተበተነው ጠላት እንዲማረክ ማድረግ አለብን፤
👉 አካባቢያችንን ከበፊቱ በበለጠ ነቅተን የመጠበቂያ ጊዜው አሁን ነው፤ ፍተሻና አሰሳዎችን አጠንክረን መቀጠል ይገባናል፤
👉 አሁን የፈተነን ኃይል ዳግመኛ የኢትዮጵያ ፈተና ሆኖ እንዳይመጣ የሚያስችል ዘላቂ መፍትሔ ልንሰጠው ይገባል፤
👉 በተጋድሏችን ያገኘነውን ነገር ለማቅለል የሚፈልጉትን ፊት እንንሣቸው፤
👉 በጋራ ታግለን በጋራ ያስገኘነውን ድል፣ እንደ ቅርጫ ሥጋ ሊመድቡ የሚነሡትን አቃራጮች እናነውራቸው፤
👉 ያሸነፈችው ኢትዮጵያ ናት፤ ከዚህ የወረደ ነገር አንቀበልም፤

tarik
Senior Member+
Posts: 33284
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

Re: ^^^(((BREAKING NEWS)))^^^Videos Of:ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የመጀመሪያ ዙር ዘመቻቸውን አጠናቀው ወደ ቢሮ ተመለሱ!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 08 Dec 2021, 10:52


==========================================================================================================

Post Reply