Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የወልቃይት ጠገዴ የሰላም አምባሳደር፣ የማህበረ ሰላም ልደታ ቤተክርስቲያን የምግባረ ሰናይ ዋና ጸሐፊ፤ እንዲሁም የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአራተኛ ዓመት የዲግሪ ተማሪ ዘመቱ

Post by sarcasm » 03 Dec 2021, 20:49

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ግንባር ላይ እንገናኝ” ያሉትን ጥሪ የተቀበሉ የሃይማኖት አባት ይናገራሉ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የወልቃይት ጠገዴ የሰላም አምባሳደር፣ የማህበረ ሰላም ልደታ ቤተክርስቲያን የምግባረ ሰናይ ዋና ጸሐፊ፤ እንዲሁም የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአራተኛ ዓመት የዲግሪ ተማሪ ናቸው። መምህር አባ ዳዊት አማረ።



“ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ግንባር ላይ እንገናኝ ብለው ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት እኔ ምንም እንኳ መሳሪያ ጨብጬ ጠላትን የመግደል ስልጣን የሌለኝ መነኲሴ ብሆንም፤ ጠላትን ማሸነፍ የሚቻለው ከሁሉ በላይ በሆነው የእግዚአብሔር ኃይልን አጋዥ በማድረግ ነውና፤ ሠራዊቱን በጸሎት፣ በቃለ እግዚአብሔርና በሞራል እያገዝኩ፤ እንዲሁም የዘለዓለም ጠላታችን ዲያብሎስ የተወገደበትን መስቀል በመያዝ ግንባር ተገኝቼ ሠራዊቱን ለማበረታታት ዘምቻለሁ” ይላሉ።



መምህር አባ ዳዊት፤ በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ምክንያት ኢትዮጵያ እና ቤተክርስቲያን ለረጅም ዓመታት በመከራ ውስጥ እንደነበሩ ይናገራሉ። ይህ መከራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቶ አገርንና የሃይማኖት ተቋማትን እስከመጨረሻው ለማጥፋት ጫፍ ላይ እንደደረሰም አስታውቀዋል። በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህዝብ አገራቸውን፣ የእምነት ተቋማቱን እንዲሁም ታሪካቸውን ..
Please wait, video is loading...