Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abdisa
Member+
Posts: 5754
Joined: 25 Apr 2010, 19:14

‼️ ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ ‼️

Post by Abdisa » 03 Dec 2021, 16:24



አዳም እና ሔዋን በመጀመሪያ ቃየልን እና አቤልን ወለዱ።

አቤልና ቃየል ካላቸው ነገር ለእግዚአብሔር ስጦታ ወይም መሥዋዕት አቀረቡ።

ቃየል ክፉ ልብ ነበረውና እግዚአብሔር አይበላው ብሎ ከአመረተው እህል ጥሩዉን ሳይሆን መጥፎዉ የማይረባውን መናኛውን እህል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረበ።

አቤል ልቡ ንፁህ ነበርና እግዚአብሔር ንጹሐ ባህርይ ማለት ነው ሲል ያላረጀውን በግ ፣ ጥርሱ ያልዘረዘረውን ንጹህ የአንድ አመት ጠቦት በግ ለእግዚአብሔር ንፁህ መሥዋዕት አቀረበ።

እግዚአብሔር ጥሩ ሥራን ስለሚወድ ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ። ነገር ግን ቃየል ጥሩ ሥራ ስላልሰራ ወደ ቃየልና ወደ መሥዋዕቱ አልተመለከተም።

በዚህም ምክንያት ቃየልም እጅግ ተናደደ ፊቱም ጠቆረ።

ከዚህም በኋላ ቃየል ተንኮል ስላሰበ ወንድሙን አቤልን ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየል ወንድሙን አቤልን በድንጋይ ገደለው።

እግዚአብሔር ቃየል ተደብቆ የሰራውን ስላወቀበት ፣ ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? ብሎ ጠየቀው። ቃየልም አላውቅም፤ የወንድሜ ጠባቂ እኔ ነኝን? ብሎ መለሰ።

እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተቆጣው። የወንድምህ የደሙ ድምፅና ነፍሱ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። አንተ የተረገምህ ነህ። በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ ትሆናለህ።

Digital Weyane
Member+
Posts: 8491
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: ‼️ ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ ‼️

Post by Digital Weyane » 03 Dec 2021, 16:56

ድንጋይ ተሸክሞ በሰራው እኩይ ተግባር ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ ንፁኃንን በድንጋይ ወግሮ መግደል ይቅር የማይባልበት ሃጢአት ነው። ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ :cry: :cry: :cry:

Weyane.is.dead
Member+
Posts: 6796
Joined: 19 Oct 2017, 11:19

Re: ‼️ ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ ‼️

Post by Weyane.is.dead » 03 Dec 2021, 21:31

Only tplf vermin could backstab someone who was helping them.

Fiyameta
Senior Member
Posts: 12627
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ‼️ ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ ‼️

Post by Fiyameta » 03 Dec 2021, 23:05


Abdisa
Member+
Posts: 5754
Joined: 25 Apr 2010, 19:14

Re: ‼️ ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ ‼️

Post by Abdisa » 08 Dec 2021, 18:54

:evil: :evil: :evil: :evil:

Post Reply