Educator wrote: ↑07 Dec 2021, 14:47
Everything you see unfolding is a result of the deal just negotiated in secrecy. The major obstacle now is disclosing the deal to the people of both Tigray and Amhara. The people are against negotiations so very hard to implement the deal. That is why TPLF pretends to be losing in order to vacate the Amhara land as per the deal. And Abiy needs to convince his people that he defeated TPLF so he can smoothly hand over Wolkait and Raya again as per the deal.
" By Finfinne Times
ዛሬ በክ/ከተማችን ከPP መሪዎች ጋር ተሰበሰብን።ሰበሰቡን ማለት ይቀላል
ሰብሳቢው የክ/ከተማው pp ፅ/ቤት ሀላፊ መጀመሪያ ስለጦርነቱ እና ጀግናው አብይ አህመድ ወደግንባር ዘምቶ ያሰገኘውን ድል በሰፊው ደሰኮረልን ቀጥሎ በየአካባቢው ለመከላከያ ሰራዊቱ እየተደረገ ያለው ድጋፍ አኩሪ እንደሆነ ህዝቡም አደረጃጀት ፈጥሮ እየፈፀመ ያለው አካባቢውን ከሰርጎ ገቦች የመጠበቅ ተግባር አስደናቂ መሆኑ ...
እና መንግስትም ኩራት እንደተሰማው ከገለፀ በኋላ ዲያስፖራውም በውጭ ሀገራት ለሀገሩ ድምፅ በመሆን እየፈፀመ ካለው አኩሪ ተግባር በተጨማሪ ለገና በአል በሚሊዮኖች የሚቆጠር ወገናችን እንደሚመጣ ለዚህም ጠ/ሚኒስትሩ ያደረጉት ጥሪ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳደረገ እና እኛም እነዚህን ዲያስፖራዎች በመንከባከብ ተጨማሪ ታሪክ እንድንሰራ ካሳሰበ በኋላ ወደ ዕለቱ አጀንዳ ተሸጋገረ።
በዚህ ሰአት መንግስታችን ጦርነቱን በአሸናፊነት እያጠናቀቀ ቢሆንም የPP ዋና አላማ ዘላቂ ሰላምን የትኛውንም ዋጋ ከፍሎ ማምጣትና ፊታችንን ወደ ብልፅግና ጉዞአችን ማዞር በመሆኑ እንዲሁም የተለያዩ የውጭ ሀገራትም በተለያየ ጊዜ ሰላም አስፍኑ የውስጥ ፖለቲካችሁን በተረጋጋ መንገድ ፍቱ እያሉ እየጨቀጨቁን በመሆኑ ይህንን ጉዳይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
በመሆኑም ወንጀል የሰሩ የህወሀት አመራሮችን ወደ ህግ የማቅረቡ ተግባር እንደተጠበቀ ሆኖ ሰላም ፈላጊ የሆኑ የፓርቲው እና የክልሉ ኤሊቶቾ ስላሉ እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደስልጣን ሲመጡ በገቡት ቃል መሠረት መሠረተሰፊ የዴሞክራሲ ባህልን ለማለማመድ ሲባል ከሁሉም የፖለቲካ ሀይሎች ጋር "ምክክር" ለማድረግ ወስነናል።
በተጨማሪም አሁን እየደረሰብን ያለውን እጅግ አስቸጋሪ የኢኮኖሚ ጫናና የምዕራባውያንን ማዕቀብ በተጠናና በብልሀት መፍትሄ መስጠት ካልተቻለ ሀገራችን ወደለየለት የኢኮኖሚና የፖለቲካ ምስቅልቅል እንዲሚከታት በመታመኑ ነገሮችን
በሆደሰፊነት ይዞ ..
አሁን እየተቋቋመ ባለው የምክክር ኮሚሽን አማካይነት ወደ ሁሉን አቀፍ ምክክር ለማቅናት ስራዎች እየተሰሩ ስለሆነ እናንተም እንደ ዜጋ እና እንደማህበራት አመራሮች በየአካባቢያችሁ እየተገኛችሁ ስለሰላም አስፈላጊነት እና ስለሁሉን አቀፍ ምክክር ለህብረተሰቡ እንድታስረዱ አደራ ለማለት ነው የጠራናችሁ ።
ስለዚህ ከአሁን በኋላ የትግራይ ወገኖቻችንን በጅምላ የመፈረጅ አካሄዶች እንዲሁም ጁንታ ወያኔ ወዘተ በማለት የመፈረጅ አካሄዶችን እንድታስተካክሉ እናሳስባለን ሲል በስብሰባው የተካፈሉ የአማራ ብሔር ሰዎች በስሜት እየተነሱ እኛ ድሮም ጠርጥረናል እነዚህ የብልፅግና አመራሮች የአማራውን ህልውና ለማዳከም ነው ጦርነቱን የቀሰቀሱት ከአሁን በኋላ ከትግሬ ጋር ደም ተቃብተናል ኦሮሞዎቹ ቁማር ተጫወቱብን ደካማ ጎናችንን ተጠቅመው አስበሉን ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኢ ወዘተ እያሉ ቢንጫጩም አብዛኛው ተሳታፊ ወይ ዝምታን መርጧል ወይ ድርድሩን ደግፏል ።
አንድ ሰው እንዲያውም የታሰሩ የኦሮሞ ፖለቲከኞችስ የOLA ጉዳይስ እንዴት ነው ብሎ ጠይቆ ሰብሳቢው ጉዳዩን በዝምታ አልፎታል ።ዞሮ ዞሮ ሁሉን አቀፍ ድርድር ማለት ከሰማይ በታች ባሉ የሀገሪቷ ችግሮች ዙሪያ በነፃነት መወያየት ነው የሚል ቃልም ሰብሳቢው ሲናገር ሰምቸዋለሁ።
የጦርነት መጨረሻው ፖለቲካዊ መፍትሄ ነው
Finfinne Times እስካሁን ግምትህ ልክ ነው ለማለት ነው ወዳጄ ይህን ፅሁፌን የፃፍኩት ከስብሰባው እንደወጣሁ ነው።