Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 10901
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ደሴ ልጇቿን ለመቀበል ሽር ጉድ ላይ ነች። ግን ጎረቤታሞች አህሪቡ ኑ! ቡና እንጠጣ ይሉ ይሆን - የጥንት ልማዳችውን?

Post by Abere » 02 Dec 2021, 15:28

ደሴ ልጇቿን ለመቀበል ሽር ጉድ ላይ ነች። ግን ጎረቤታሞች አህሪቡ ኑ! ቡና እንጠጣ ይሉ ይሆን - የጥንት ልማዳችውን? የወደመውን ማሰብ እጅግ ናላ ያዟራል። ቦሩ ሜዳ፣ አላሻ፣ ኩታበር፣ ገራዶ፣ መሃል ፒያሳ በከንቱ ያለውቀን ሰው የሚያውቀው እግዜር እና ወላጅ እናት ብቻ ናቸው። የደብረሲናን መውደም ያዬ ደሴ ሰላም ናት ማለት ሞኝነት ነው። ከሁሉም በላይ ደግሞ ከንብረትም ከሰው ህይወትም በላይ ደሴ ላይ የወደመው አብሮ መኖር እና መልካም ጉርብትና ነው። መተማመን አብሮ መብላት እንደት ይመለስ ይሆን? የንጉስ ሚካዔል አይጠየፍ አዳራሽ እንግዳውን በአንድ ላይ ሳይመርጥ በአንድነት ይቀበል ይሆን? ወይስ የሼህ ውሴን ትንብይት ተፈፀመ - ወደ መልካሙ ዘመን ተሸጋገርን? ወሎ የሁሉ ነገር በታሪክ እምብርት ናት እና ችግራችን በከርሷ ተቀብሮ ቢሆንስ።

ለማንኛውም የወያኔም ይሁን የታላቋ ኢትዮዽያ ደጋፊዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ - ኢትዮዽያ አሸንፋለች!!!
የወያኔ ሞት የሁላችን ድል ነው!!!