Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 33099
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

***(((QUOTE OF Z DAY)))***ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ:በምሥራቅና በምዕራብ የተገኘው ድል በመሐል ሀገር እንደሚደገም!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 02 Dec 2021, 10:05

Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/
i1701t0aSpoc1nh1552grd ·
ሰበር ዜና‼️
በምሥራቅና በምዕራብ የተገኘው ድል በመሐል ሀገር እንደሚደገም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።
****************
(ኢ ፕ ድ )
በምሥራቅና በምዕራብ የተገኘው ድል በመሐል ሀገር እንደሚደገም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት በሦስተኛው ቁልፍ ግንባር ተገኝተው ከሠራዊቱ ጋር በመከሩበት ጊዜ ነው።
ከሰሞኑ በሚሠሩ ኦፕሬሽኖች በወራሪው አሸባሪ የተያዙ ተጨማሪ ከተሞች ነጻ እንደሚወጡ የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለወረራ የገባው አሸባሪ ምንም ነገር ይዞ እንዳይወጣ ሕዝቡ ተደራጅቶ ማስቀረት እንዳለበት ጥሪ አድርገዋል።
ጠላት ፈርሷል፤ ተበትኗል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ አሁን ጠላት ያለው አማራጭ የሰረቀውን አስረክቦ እጁን መስጠት ነው ብለዋል። የሰረቀውን አስረክቦ እጁን ከሰጠ ምርኮኞችን ተንከባክቦ መያዝ የጀግና ባህላችን ነው ብለዋል።
ከአሸባሪው ህወሓት ነጻ በወጡ አካባቢዎች በአስቸኳይ መስተዳድሩን በቶሎ መልሶ ማቋቋም እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሳስበዋል።
ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነዋል። ወታደሩ በከፍተኛ ሞራል ላይ ነው ሲሉም የወገን ኃይል ያለበትን ገልጸዋል።
ሕዝቡ እስካሁን ላደረገው ተሳትፎ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን አንድነታችን የተጠበቀ ይሁን፤ የአሉባልታ ወሬ ወጀብ አይውሰደን፤ አንድ ሆነን የማትደፈር ሀገር ለልጆቻችን እናስረክብ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መልእክት አስተላልፈዋል።
አካባቢህን ጠብቅ‼️
ወደ ግንባር ዝመት‼️
ሠራዊቱን ደግፍ ‼️
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን
ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
ቴሌግራም
https://t.me/ethpress
ትዊተር
https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ
https://www.press.et/