Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
pushkin
Member+
Posts: 9527
Joined: 23 Jul 2015, 06:10

የኤርትራ፣ የሶማሊያንና የኢትዮፕያ ባንዲራ ይዞ በዝናብም በጸሃይም ደጅ እያደረ ድምጹን ያሰማው ኤርትራው ጀግና ያቆብ!

Post by pushkin » 01 Dec 2021, 19:47

ሶማሊያን ጨምሮ አፍሪካውያን እየመጡ እንዲናገሩ ያደርጋል፡፡ አንዲት ሜጋፎን ይዞ የለንደንን ጎዳናዎችን ሲንጠው ይውላል፡፡ ሲመሽ እዚያው ያድራል፡፡ ቀላል ቢመስልም ቀላል ቁጥር የማይባሉ አላፊ አግዳሚውን ያነቃቃል ያስተምራል፡፡ እደጅ እያደር ስለ አፍሪካውያን የሚሞግተውን ሰው ለማየት ከየአቅጣጫው ሰው ይጎርፋል፡፡የብዙዎቹን ቀልብ ከመያዙ የተነሳ እየተጠራሩ ይጎበኙታል፡፡ምግብም ያመጡለታል፡፡

ያቆብ ለለንደን ጎዳናዎች አዲስ አደለም፡፡ የትህነግ ተላላኪነና በእንግሊዝ መንግስት የሚደገፍ የሜዲያ ፕሮፓጋንዲስት የሆነው ሰውና ማርቲን ፕላውት ላይ፡ አገር ደህና ብለው ሲወጡ የእንቁላልና የዱቄት ውህድ ደፍቶባቸው ፍርድ ቤት ተከሶ ያውቃል፡፡ እንግሊዝ የሚኖሩትን አፍሪካኖች የትግል ፋና ወጊ ሆኖ የተኛ ህሊናቸውን ሲያነሳሳና ሲያነቃቃ ይውላል፡፡ በተለይ ማርቲን ፕላውት ላይ ውህዱን ሲደፋ ዝናው በለንደን አፍሪካውያን ላይ ነጩን ጠላት መድፈርና መታገል እንደሚቻል ትልቅ ትምህርት ሰጥቱዋል፡፡ መብታቸውን መጠየቅ ላይ ብዙ አሰተምሩዋል፡፡

የ#nomore Movement አድማስ መስፋት እንዲሁ የተገኘ ድል አደለም፡፡ ብዙ ቅድመ ማነቃቃት ተሰርቶበታል፡፡በአሜሪካ ታዋቂ የሆኑ ኤርትራውያን አሜሪካን በየራዲዮንና ቴሌቭዥን ጣቢያ እየሄዱ ብዙ ሰርተዋል፡፡በተለይ የኒፕሲ ቤተሰቦች ኔት ወርክ ከባድ ሚዛን ይደፋል፡፡ የአፍሪካን አሜሪካን ማህበረሰብ ላይ ትልቅ አብዮትን ፈጥሩዋል፡፡
ኤርትራ እንደሆነች ነጻነቱዋን ካወጀች 80 አመታት አልፈዋል፡፡ ከምእራባውያን አገዛዝ ስር ነጻ ሆና ስንዴ የማይመጸወትላት ብቸኛዋ ከአፍሪካ ኩሩና ነጻ አገር ናት፡፡ ኤርትራ ዛሬ የምትታገለው የአፍሪካኖችን ትግል ነው፡፡

ዛሬ ያቆብ በብሪታኒያ ጠቅላይ ሚንስትር ፊት ለፊት ገጥሞ ሲያበቃ የፊጥኝ ታስሮ ወህኒ የገባው ለአፍሪካኖች ነጻ መውጣት ነው፡፡እኛማ እኮ ምስጋና ለህዝባዊ ግንባር ይግባና ነጻነታችንን እራሳችን ወስደነዋል፡፡ እህል አይሰፍሩልን ንጉስ አይሾሙልን የምንጠይቀው ነገር የለንም፡፡

ትግላችን ለአፍሪካውያን እድገት በህብረት ነው ፡፡ ወዲህም ምእራባውያን ያጠቁን የነበረው ከኢትዮፕያ አሽከር እየገዙ ስለሆነ ከመገዳደል እንተባበር ነው ጥያቄያችን ሌላ የምንፈልገው የለም፡፡ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ነው ነገሩ፡፡

ኮርተው ያኮሩን፡ የህዝባዊ ግንባር ለዲሞክራሲና ለፍትህ አሁንም ለአፍሪካ ችግር መድህን ናቸው፡፡ቀጠናችንን ከሽብርተኛ የሚጠብቁት የኤሪትሪያ ዲፌንስ ፎርስ ከፍለን የማንጨርሰው እዳ አለብን፡፡

በየትኛውም የትግል መስክ የማታሳፍሩን ትንታግ የኤሪትሪያ ልጆች አደ ወሊዳ ትምከን፡፡የወንድ ዘር መገኛውን አሳይታችሁናል፡፡

የ#nomore አስተባባሪ መስራች ከመጋረጃ በስተጀርባ ብዙ ሰዎቸ አሉ ሲል ለማውራት ያህል ወይም ለታሪክ ሽሚያ አደለም ስለተሰራ ነው፡፡እንዲያም ሆኖ የሁሉም ትብብርና አስተዋጽኦ በጣም አስደናቂ ነው፡፡ መጨረሻውን እኮ ሰፊ ትግል የሚጠብቃቸው እያንዳንዱን የአፍሪካ አገር በቤታቸው ነው፡፡ስንዴ መለመን እስካላስወገዱ ድረስ ነጻነት የለም፡፡ ትግሉ ረጂምና ውስብስብ ነው፡፡ ሰልፍ ደጅ የሚቀር ድምጽ ነው መሬት ላይ ወርዶ መስራትን ይጠይቃል፡፡

እንደ ሃገረ ኤሪትሪያ፡፡፡፡፡፡
እናትም አባትም አገራችን ኤርትራ ለዘላለም ትኑር!
ዓወት ንሓፋሽ!

Meleket
Member
Posts: 3044
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: የኤርትራ፣ የሶማሊያንና የኢትዮፕያ ባንዲራ ይዞ በዝናብም በጸሃይም ደጅ እያደረ ድምጹን ያሰማው ኤርትራው ጀግና ያቆብ!

Post by Meleket » 02 Dec 2021, 05:05

“የጀግና” ተብሎ ይታረም! የወንድ ትምክሕተኛነትን ኤርትራዉያን በጋራ ትግላችን ድሮ ስለቀበርነው! የሴት እንቍላሎቻችንን ጀግንነትም ችላ ያለ ስለሚመስል ብለናል ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች! :mrgreen:
pushkin wrote:
01 Dec 2021, 19:47
በየትኛውም የትግል መስክ የማታሳፍሩን ትንታግ የኤሪትሪያ ልጆች አደ ወሊዳ ትምከን፡፡የወንድ ዘር መገኛውን አሳይታችሁናል፡፡

እናትም አባትም አገራችን ኤርትራ ለዘላለም ትኑር!
ዓወት ንሓፋሽ!


Post Reply