Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የሶማሌ ጉዳይ ኮንግረስ (ሶ.ጉ.ኮ) Congress for Somali Cause አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ

Post by sarcasm » 01 Dec 2021, 09:20

ህዳር 21፣ 2014
አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ

የሶማሌ ጉዳይ ኮንግረስ (ሶ.ጉ.ኮ) መግለጫ


የዛሬ 67 ዓመታት ህዳር 29፣ 1954 (እኤአ) የእንግሊዝ መንግስት የመጨረሻዎቹን የሶማሊ ክልል መሬቶች የሶማሊን ህዝብ ሳያማክር ህገ ወጥ በሆነ ምስጢራዊ ስምምነት ለኢትዮጵያ መንግስት ማስተላለፉ ይታወሳል። ይህ የታሪክ ክስተት የሶማሊ ህዝብ ለብዙ ዓመታት በቅኝ ተገዥነት ቀንበር ውስጥ እንዲወድቅ የተደረገበት አሳማሚ ቀን ሆኖ ይዘከራል፡፡

እኛ የሶማሊ ጉዳይ ኮንግረስ (ሶ.ጉ.ኮ)መስራች አባላት፣ በዛሬዋ ታርካዊ ዕለት ለሶማሊ ክልል ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ያለመ የሶማሊ ክልል ንቅናቄ መጀመሩን በታላቅ ደስታ እናበስራለን። የእኛ ተልዕኮ ሰፊ መሰረት ያለው የሶማሊ ቡድን በማደራጀት ህብረተሰባችን የነጻነት፣ የኮንፌዴሬሽን ወይም የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ስምምነት ላይ የሚደርስበትን የሽግግር ወቅት ማዘጋጀት ነው።

የሶማሊ ጉዳይ ኮንግረስ (ሶ.ጉ.ኮ)ምስረታ ድንገት የተፈጠረ ጉዳይ ሳይሆን ሂደቱ ለዓመት የዘለቀ፣ የበርካታ ድርጅቶች ማለትም የሶማሊ አመራር ለጋራ ጉዳይ (SLCC)፣ ሴቭ ሶማሊ ስቴት ግሎባል ኮንግረስ (SSSGC)፣ ሶማሊ ዓለም አቀፍ ኮንግረስ (SWC)፣ የሶማሊ ብሄራዊ ኮንግረስ (SNC) እንዲሁም የሌሎች ታዋቂ የሶማሊ ምሁራን ውይይትና ምክክር ውጤት ነው፡፡ በአፍሪካ ቀንድ የሚኖሩ ሶማሊዎች በምንም አይነት የፖለቲካ አቋም እና መልክዓ ምድራዊ አቀማመጦች ሳይገደቡ፣ ወደ አንድ የሶማሊ ግንባርን ለማምጣት የሚተጋው፣ የአፍሪካ ቀንድ የፖሊሲ ማዕከል (HAPC) አብዛኛውን የውይይትና የምክክር መድረክ በማዘጋጅት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ እንደሃገር አጠቃላይ ህልውናዋ አደጋ ላይ በወደቀበት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሳለች፡፡ ይህን ወቅታዊ ሁኔታ ያላገናዘበው አለማስተዋል የሚታይበት የክልሉ መንግስት፣ ህዝቡን ከሚመጣው አደጋና ከተጋረጠበት የድርቅ ችግር ከመታደግ ይልቅ፣ ሀብትና ንብረት በማሸሽ፣ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” ከሚል ግብዝ ሃሳብ በመነሳት በሶማሊ ጎሳዎች መካከል ግጭቶች እንዲቀሰቀሱና ህዝቡ ደም እንዲቃባ ለማድረግ ሌት ከቀን እየሰራ ይገኛል፡፡

በክልሉ ህዝብ ዘንድ እንዲሁም በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተዓማኒነቱን ያጣው የክልሉ አስተዳደር የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲል ብቻ የሶማሊን ህዝብ ደህንነትና ጸጥታ ስጋት ላይ እንዲወድቅ እያደረገ ይገኛል። በመሆኑም በህዝባችን ላይ የተጋረጠውን አስከፊ አደጋ ለመቀልበስና የህዝባችንን የወደፊት እጣ ፈንታ በተደላደለ፣ አስተማማኝ ቁመና ላይ ለማኖር ዛሬ ነገ ሳንል ሁለንተናዊ ሁኔታውን በጥልቀትና በብስለት በመገምገም አስፈላጊውን ስራ መስራት ሀላፊነቱ በጫንቃችን ላይ ወድቋል፡፡

የጠ/ሚ አብይ አህመድ ወደስልጣን መምጣት ታላቅ ተስፋ አሳድሮ እንደነበር እሙን ነው፡፡ ኾኖም ግን ጠ/ሚኒስትሩ ይህን ታላቅ ዕድል፣ በሀገሪቱ የሚገኙ ሕዝቦች ወደ ዲሞክራሲ የሚያደርጉትን ትልምና ጉዞ ለማሳለጥ ከመጠቀም ይልቅ የግልና የተወሰነን ቡድን ህልምና ጥቅም ለማሳካት ሲባል ብቻ ፍጹም በተሳሳተ መንገድ አገሪቱ ወደ አዘቅት እንድትወርድ አልፎ ተርፎም የርስ በርስ ጦርነት እንዲቀሰቀስና መላውን የሀገሪቱ ህዝብ ህልቆ መሳፍርት ለሌለው መከራና ስቃይ በመዳረግ የተሰጠውን ታላቅ ዕድል መና አስቀርቶታል፡፡

እንደ አለመታደል ሆኖ ጠ/ሚ አብይ አህመድ የኦሮሞ፣ የሶማሊ፣ የአፋር፣ የትግራይ፣ የሲዳማ፣ የወላይታ፣የቅማንት፣ የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ የሀረሪ፣የጉራጌ፣የስልጤ እና ሌሎች ህዝቦች ዋጋ የከፈሉበትን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብትን ከማክበርና ከማስከበር ይልቅ አገሪቱ የአንድ-አይነትነትና የጠቅላይ ገዥነት አስተሳሰብ፣ ርዕዮት ባላቸው አድሃሪያን ኃይሎች እጅ እንድትወድቅ አድርገዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በኦሮሚያ፣ በትግራይ ፣በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ፣እና በቅማንት ህዝቦች ላይ ግልጽና ከዓመት በላይ የዘለቀ ጦርነት ታውጆባቸዋል፡፡

ዛሬ ላይ የአብዛኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መሰረታዊ ጥያቄ የስልጣን ክፍፍል ሳይሆን ዘለቄታዊ ደህንነታቸውንና ጥቅማቸውን ሊያስጠብቅላቸው የሚችል፣በተግባር ተፈጻሚ የሚሆን ውጤታማ የፌደራሊዝም ስርዓት ወይም ኮንፌዴሬሽን እንዴት መመስረት እንችላለን የሚል ነው።

የሶማሊ ጉዳይ ኮንግረስ (ሶ.ጉ.ኮ)የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ከተጫነባቸው የባርነት ቀንበር ለመላቀቅ በሚያደርጉት የውይይትና የምክክር መድረኮች ሁሉ ለመሳተፍ እንዲሁም የትግል አጋር ለመሆን ዝግጁ መሆናችንን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

በአንድ ብሄር፣ ሃይማኖት እና ቋንቋ የበላይነት ላይ የተመሰረተ ያለፈውን እንዲሁም አዲስ ውልድ የጠቅላይ ገዥነት ሥርዓት ለመመለስ የሚደረገውን የሴራ ፓለቲካ አጥብቀን እንቃወማለን።


ህዝባችንን ከተጫነበት ታሪካዊ ተገዥነት ለማላቀቅ እና አሁን ባለው ህሊና-ቢስ አመራር ከተቀነባበረበት አይቀሬ ግጭት ለመታደግ ከምንም በላይ ጥረታችን አስፈላጊ ሆኖ በተገኘበት የጸጥታ፣ የሰብዓዊ እርዳታ ስራ፣ የመልካም አስተዳደር እና የመሪነት ሚናችንን ለመወጣት እንዲሁም የልማት ፍላጎቶችን ለማሳካት ተግተን እንሰራለን፡፡

የሶማሊ ጉዳይ ኮንግረስ (ሶ.ጉ.ኮ)

Congress for Somali Cause
Please wait, video is loading...


Post Reply