Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 33099
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

***(((JUST IN)))***China's FM Wang Yee:Ethiopia Can Solve It's Own Internal Problems!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 01 Dec 2021, 06:36

Natnael Mekonnen
u1t0a4Spo75mnmsmh00u4tla ·
"ኢትዮጵያ የገጠማትን የውስጥ ችግር በራሷ የመፍታት አቅም አላት" የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ

#Ethiopia : ኢትዮጵያ የገጠማትን የውስጥ ችግር በራሷ የመፍታት አቅም እንዳላት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ሚኒስትሩ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን እና ሚስተር ዋንግ ዪ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱን ተከትሎ ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የጋራ ጋጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ሚስተር ዋንግ ዪ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ የራሷን የውስጥ ችግር በራሷ አቅም መፍታት እንደምትችል ቻይና ታምናለች ብለዋል።

አቶ ደመቀ በበኩላቸው ቻይና ከኢትዮያ ጋር በመርህ ላይ የተመሰረተና የማይዋዥቅ የቆየ ግንኙነት እንዳላት ተናግረዋል፡፡