Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12583
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የዶ/ር እሌኒ ገብረ መድኅንን የክብር ዶክትሬት ነጥቆ ለታማኝ በየነ ሊሰጥ ነው ተባለ

Post by Thomas H » 30 Nov 2021, 22:33



ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእሌኒ ገብረ መድኅንን የክብር ዶክትሬት ሰረዘ
University of Gondar Revokes Dr. Eleni Zaude Gabre-Madhin's Honorary Doctorates
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ለዶ/ር እሌኒ ዘውዴ ገ/መድኅን የኢትዮጵያ ምርት ገበያን በማቋቋምና በመምራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ (Honorary Degree of Humane Letters (DHLitt)) የሰጣቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በወቅቱ የክብር ዶክትሬቱን የሰጣቸው የህብረተሰባችንን አኗኗር እና የሀገራችን የውጭ ንግድ ስርዓት እንዲሻሻል ባበረከቱት መልካም አስተዋጽኦ እና ለወደፊቱም በተሰጣቸው የክብር ዶክትሬት ልክ ሀገራችን ያለአድሎና በእኩልነት እንዲያገለግሉ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲያችንን ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ አምባሳደር ሆነው እንዲያገለግሉ ነበር፡፡
ይሁን እንጅ ዶ/ር ኢሌኒ ሰሞኑን የዓለም አቀፍ ሰላምና ልማት ማዕከል ተብሎ ይጠራ በነበረው ድርጅት አማካኝነት በድብቅ በተዘጋጀ የበይነመረብ ስብሰባ ላይ ሙያዊነትን ያልጠበቀ፣ አድሏዊ፣ የአንድን ቡድን ፍላጎት ብቻ ያንጸባረቀ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲያችንን ዋና ዋና እሴቶች የሚፃረር ሀሳብን በማራመዳቸው ዩኒቨርሲቲያችን ለዶ/ር ኢሌኒ ዘውዴ የሰጠውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በድጋሚ ሲያጤን እና ሲመረምር ቆይቷል፡፡
በዚህም መሠረት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1152/2011 አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 4 እና በዩኒቨርሲቲያችን የሴኔት ደንብ አንቀጽ ቁጥር 6 ንዑስ አንቀጽ 16 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ህዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ለዶ/ር ኢሌኒ ዘውዴ ገ/መድሕን ሰጥቶት የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ (Honorary Degree of Humane Letters (DHLitt)) እንዲሰረዝ መወሰኑን እናሳውቃለን፡፡
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
ሕዳር 21/2014ዓ.ም

Thomas H
Senior Member
Posts: 12583
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Re: ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የዶ/ር እሌኒ ገብረ መድኅንን የክብር ዶክትሬት ነጥቆ ለታማኝ በየነ ሊሰጥ ነው ተባለ

Post by Thomas H » 30 Nov 2021, 22:52

በነገራችን ላይ ዶ/ር እሌኒ ጎንደሬዎችን ላለማሳፈር ብላ ነበር የክብር ዶክትሬቱን የተቀበለችው :: በወቅቱ ግን እዛ ለመሄድ ስላልተመቻት የቤት ሠራተኛዋን ነበር የላከችው አሉ።

Post Reply