Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
ethioscience
Member
Posts: 3806
Joined: 01 Nov 2019, 17:37

Today was a bad day for Lucy and Eleni

Post by ethioscience » 30 Nov 2021, 17:43





የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ለዶ/ር ኢሌኒ ዘውዴ ገ/መድሕን ሰጥቶት የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰረዘ።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ለዶ/ር ኢሌኒ ዘውዴ ገ/መድኅን የኢትዮጵያ ምርት ገበያን በማቋቋምና በመምራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ (Honorary Degree of Humane Letters (DHLitt)) የሰጣቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በወቅቱ የክብር ዶክትሬቱን የሰጣቸው የህብረተሰባችንን አኗኗር እና የሀገራችን የውጭ ንግድ ስርዓት እንዲሻሻል ባበረከቱት መልካም አስተዋጽኦ እና ለወደፊቱም በተሰጣቸው የክብር ዶክትሬት ልክ ሀገራችን ያለአድሎና በእኩልነት እንዲያገለግሉ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲያችንን ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ አምባሳደር ሆነው እንዲያገለግሉ ነበር፡፡

ይሁን እንጅ ዶ/ር ኢሌኒ ሰሞኑን የዓለም አቀፍ ሰላምና ልማት ማዕከል ተብሎ ይጠራ በነበረው ድርጅት አማካኝነት በድብቅ በተዘጋጀ የበይነመረብ ስብሰባ ላይ ሙያዊነትን ያልጠበቀ፣ አድሏዊ፣ የአንድን ቡድን ፍላጎት ብቻ ያንጸባረቀ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲያችንን ዋና ዋና እሴቶች የሚፃረር ሀሳብን በማራመዳቸው ዩኒቨርሲቲያችን ለዶ/ር ኢሌኒ ዘውዴ የሰጠውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በድጋሚ ሲያጤን እና ሲመረምር ቆይቷል፡፡

በዚህም መሠረት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1152/2011፣ አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 4 እና በዩኒቨርሲቲያችን የሴኔት ደንብ አንቀጽ ቁጥር 6 ንዑስ አንቀጽ 16 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ህዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ለዶ/ር ኢሌኒ ዘውዴ ገ/መድሕን ሰጥቶት የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ (Honorary Degree of Humane Letters (DHLitt)) እንዲሰረዝ መወሰኑን እናሳውቃለን፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
ሕዳር 21/2014ዓ.ም