Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 33235
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

^^^(((JUST IN)))^^^የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት በሱዳን ጦር ላይ ጥቃት ሰነዘረ የተባለ የሚነዛው ወሬ መሰረት ቢስ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሰት አስታወቀ!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 28 Nov 2021, 13:43

Natnael Mekonnen
0u4lic119stol30m1teh95 ·
የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት በሱዳን ጦር ላይ ጥቃት ሰነዘረ እየተባለ የሚነዛው ወሬ መሰረት ቢስ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሰት አስታወቀ።

#Ethiopia : የኢትዮጵያ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ሱዳን ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ሀይሎች ጥቃት ሰንዝረውብኛል በሚል በምታቀርበው ቅረየታ ላይ ለኢቲቪ ምላሽ ስጥተዋል።ዶ/ር ለገሰ በምላሻቸውም፣ ህወሓት በተለያየ መልኩ ሱዳን ውስጥ የሚያሰለጥናቸውን ሰርጎ ገቦች በተለያየ ቦታ በተለይም በመተማ አካባቢዎች በተለያየ ጊዜያት ያስገባል ፤ በተለያየ ጊዜ ኢትዮጵያን የሚተናኮሉ ሰርጎ ገቦች ይገባሉ ብለዋል።

በዚህ መሰረት "በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰርጎ ገቦች፣ ሽፍታዎች እና አሸባሪዎች በዛ መስመር ገብተው ነበር በዛ መስመር የገባውን ኃይል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የአካባቢው ሚሊሻ መቷቸዋል፤ ደምስሷቸዋል" ብለዋል።የተለያዩ ሚዲያዎች እንደሚነዙት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሱዳን ጦር ላይ ጥቃት ፈፅሟል የሚለው መሰረተቢስ ነው ሲሉም አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የትኛውም ሉአላዊ ሀገር ላይ ጥቃት የመፈፀም አጀንዳ የለውም ሲሉም አስረድተዋል። See less