Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4204
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

ጋሸና እና ጭፍራ አልቆላችዋል: ቀጣዮቹ ደሴ እና ኮምቦልቻ ናቸው

Post by Abaymado » 28 Nov 2021, 12:49


ጋሸና እና ጭፍራ በቁጥጥር ስር መሆናቸው ሰራዊቱ ወደፊት እንዲገፋ ያረገዋል::

ደሴ እና ኮምቦልቻ ብዙ የሚባል የትግሬ ሰራዊት ስሌለ በቀናት ውስጥ ይያዝል ተብሎ ይጠበቃል::

ከመንዝም ወያኔ ተባሮ ወጥቷል



Mesay Mekonnen
የጦር ሜዳ ውሎዎችን በተመለከተ የሚደርሱንን መረጃዎች በአስቸኳይ አዋጁ ምክንያት በዝርዝር ከማካፈል እንቆጠባለን። በአጭሩ ግን ጀግኖቹ ስራቸውን በስኬትና በፍጥነት እያከናወኑ ነው። ጋሸና፣ ጭፍራ፣ ደሴ-ኮምቦልቻ፣ ማይጠብሪ፣ የምንሰማው ነገር መጪውን ጊዜ የድል ዜናዎችን እየተበሰሩ የምናሳልፍበት ይሆናል። የጋሸና ዋናው የህወሀት ምሽግ ተሰብሯል። ጋሸናና ዙሪያው ስትራቴጂክ አከባቢ ነው። ህወሀት አርሚ ሁለት የተሰኘውን ትልቁን የሰራዊቱን ክፍል ያሰለፈበት ጋሸና ላይ መሆኑ ያለምክንያት አይደለም። ጋሸናን ካጣ መቆሚያው መቀሌ ይሆናል። እሱንም ማምለጥ ከቻለ። ጋሸና ለስድስት ወሳኝ አቅጣጫዎች ቁልፍ መገናኛ በመሆኗም እንደፍልፈል ጉድጓድ ሲቆፍር ከርሞ ግዙፍ ምሽጎችን ሲገነባ ነበር። ሰሞኑን በኢትዮጵያ ሰራዊት በተወሰደ ብርቱ የማጥቃት እርምጃ ምሽጎቹ፣ ዋናውን ጨምሮ ተሰብረው በወገን እጅ ተይዘዋል። የጋሸና ጉዳይ ያከተመ ይመስላል። የህወሀት ጀሌ ወደ መቀሌም መሸሽ እንዳይችል መሀል ላይ ተቆርጧል።
በአፋር በኩል ጭፍራም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ሆኗል። ዙሪያውን ለሁለት ቀናት ከቦ የቆየው የወገን ሃይል በዛሬው ዕለት ጭፍራ ገብቶ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ሰቅሏል። ወታደራዊ ባለሙያዎች እንደነገሩኝ ጭፍራም እንደጋሸና ወሳኝ ቦታ ነው። የመቀሌን መስመር ለመቁረጥ የጭፍራ ነጻ መሆን ትልቅ ሚና ይኖረዋል። ሚሌን ቋምጦ የአፋር በርሃ ላይ እንደቅቤ የቀለጠው የህወሀት ጀሌ የተረፈው ወደ መቀሌ ለማምለጥ እንኳን እንዳይችል ሆኗል። በጭፍራ በኩል ያለው ግንባር በወገን የበላይነት ተያዘ ማለት የወልዲያን ነገር በቀናት ውስጥ እንዲለይለት ያደርገዋልም ተብሏል። በነገራችን ላይ የጋሸናውም መስመር ለወልዲያ ጨምሮ እስከ አላማጣ-ኮረም ድረስ ለኢትዮጵያ ሰራዊት አልጋ በአልጋ እንደሚሆንለትም ነው ያነጋገርኳቸው ወታደራዊ ባለሙያዎች ያጫወቱኝ።
የደሴ-ኮምቦልቻም እጣ ፈንታ ከእነዚህ አከባቢዎች ጋር የተያያዘ ነው። እንደሰማሁትና ቀድሞም እንደነበረኝ መረጃ በደሴና ኮምቦልቻ የህወሀት ሀይል ብዙም የለም። አጠቃላይ የማጥቃት ውሳኔ በመንግስት በኩል እስኪሰጥ መጠበቁ ግድ ስለነበረ እንጂ የሚገዳደር የህወሀት ሃይል በሁለቱም ከተሞች እንደሌለ መረጃው አለኝ። ምናልባት ሰርገው የገቡና በነዋሪነት ዓመታትን የቆዩ የህወሀት ሰዎችን የማጥራቱ እርምጃ በራሱ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። ከዚያ ባለፈ ለሚሌው ግንባር አብዛኛውን ሃይል ወደባቲ በማንቀሳቀሱ ደሴና ኮምቦልቻ በአብዛኛው ከህወሀት ነጻ ናቸው። በሚቀጥሉት ቀናት የሁለቱ ከተሞች ጉዳይም መቋጪያ ያገኛል። በነገራችን ላይ ህወሀት እንደምንም የሞት ሞቱን በሱዳን በኩል መተማ አከባቢ ጥቃት ከፍቶ እንዳይሆን ሆኖ ተመትቷል። የህወሀት መደምሰስ ያሳመማት ሱዳን ኢትዮጵያ አጠቃችኝ ስትል አለቃቅሳለች። አፍንጫ ሲመታ ዓይን ያለቅሳል ሆኖባት ነው።
ሰሜን ሸዋ ያለው ወቅታዊ ሁኔታም ስጋት ላይ የሚጥል አይደለም። በትንሽ ሃይል ሾልኮ በመግባት ከአንዳንድ የሸኔ ታጣቂዎች ጋር የተገናኘው የህወሀት ጀሌ ግስጋሴው ተገትቶ ግራ በተጋባ ሁኔታ በየጥሻውና ዋሻው ሲሯሯጥ ይታያል። መንዝ አከባቢ ሰሞኑን ሊፈራገጥ ሞክሮ ወገቡ ሲቀነጠስ ጊዜ እግሬ አውጪኝ መፈርጠጡ ተሰምቷል። በሞላሌ አንገቱን ቀና ከማድረጉ የድሮን ሲሳይ መሆኑም ታውቋል። ይሁንና አሁንም በጥቂት ቁጥር አንዳንድ ቦታዎች መታየታቸው አልቀረም። ተበጣጥሰው የተበተኑ በመሆናቸው የመልቀሙ ስራ ትዕግስትንና ጥንቃቄን ይጠይቃል። በሰሜን ሸዋ የተጀመረው የማጥቃት እርምጃ በቅርቡ የዚያን አከባቢ ሁኔታ የሚቀይረው እንደሚሆን ይታመናል።
በአጠቃላይ ያለው የየግንባሩ ወቅታዊ ሁኔታ ለጠላት ሃይል የጨለማው ዘመን ከደጃፉ መድረሱን ያመላክታል። በአንጻሩ ለኢትዮጵያውያን የእፎይታ ጊዜ እየመጣ እንደሆነ ማረጋገጫ ይሰጣል። አሁንም እንጠይቃለን። ሌ/ጄ ጻድቃንን የበላ ጅብ ምነው አልጮህ አለ? በደህና ይሆን የጠፉት?
እንበርታ!