Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"በግሌ በለውም በሎምም አልልም! ሺ ሚሊዮን አይነት ስም ስጠው የእርስበርስ ጦርነት ነው! መፍትሄው ሲመርህ ሲጎፈንንህ ይክረም እንጂ ድርድር ብቻ ነው!" ዮሴፍ የየሱስወርቅ

Post by sarcasm » 27 Nov 2021, 20:30

ይሄ የግሌ የኔብቻ አቋም ነው!!
የእስክንድር ደጋፊ የባልደራስ አባል ሆነህ ምናምንእያልክ
አታላዝንብኝ!!
የግሌ የኔ የዮሴፍ ሃሳብና አቋም ነው!!
ከጦርነቱ የመጀመሪያው ቀን አንስቶ ያልተቀየረ እምነቴ ነው!
በዚህ ጦርነት የሚያሸንፍ አካል የለም!
ሺ ሚሊዮን አይነት ስም ስጠው የእርስበርስ ጦርነት ነው!!
ወያኔ የሰጣይን ቁራጭ ብቻ ሳትሆን የሰይጣንም አባት ነች!!
አብይ አህመድና ብልፅግና ደግሞ የሰይጣኗ ወያኔ የበኩር ልጆች ናቸው!
ስይጣን አባትና ልጅ አሳምነው አስፈራርተው ከጎናቸው ያሰለፋቸው በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ የዋህ ምስኪን ዜጎች በሁለቱም ወገን አሉ!!
የሚሞቱትና የሚጋደሉት ምስኪኖቹ ናቸው!!
እንደውም አሁን ጦርነቱ የአማራና የትግሬ ሆኗል
የሚፈለገውም ይሄው ነበር!!
ትግሬ ወያኔ ፋኖ አማራ ብትላቸው ተጨማሪ መገለጫቸው እንጂ ሰዎች ናቸው!!! ባንዳም ጀግናም ቅፅል እንጂ የወል ስማቸው ሰው ነው!
ገዳይም ሟችም ኢትዮጵያውያን ናቸው!!
መፍትሄው ሲመርህ ሲጎፈንንህ ይክረም እንጂ ድርድር ብቻ ነው!!
አብይ አህመድ ለአሜሪካው የአፍሪካ ጉዳዮች ተወካይ
Jeffrey Feltman " ያለ የሌለ አቅሜን ተጠቅሜ ከአማራና ከአፋር ክልል ካስወጣኃቸው በሃላ ለመደራደር እችላለሁ"
ብሏል!!!
ወያኔም አስተማማኝ ርዳታ ለትግራይ ህዝብ የሚደርስበት ኮሪደር ከተከፈተልኝ እደራደራለሁ ብላለች!!
ከድርድር ውጭ በጊዚያውነት በሺዎች ሞት አንዱ አንድ ቦታ ሊይዝ ይችላል ሌላው በሌላ ጊዜ ሊያስለቅቅ ይችላል!!
አብይ እህመድ ወያኔን ከመቀሌ አስወጥቶ በትግራይ ተራሮች ብቻ ተወስነው ነበር!
ዛሬ ውጊያው ደብረብርሃን ነው! ነገ ተመልሶ መቀሌ ሊደርስ ይችላል:: ከነገወዲያው ሸዋሮቢት የማይመለስበት ምክንያት የለም!!
ከዚህ ጦርነት የምታተርፍ አገር የለችም!!
እዘምታለሁ የሃገሬ የህልውና ጉዳይ ነው የሚልን ሰው ምርጫውን አከብራለሁ!!
በግሌ በለውም በሎምም አልልም!!
ለአብይአህመድና ለደብረፂዮን የስልጣን ጥማት ምስኪን
ኢትዮጵያውያን ባይሞቱና ባይጋደሉ ምርጫዬ ና ምኞቴ ነው!!
እስከዛሬ እንደማደርገው በግል ገፄና " ድል ለዲሞክራሲ" በሚለው የgroup አምዴ ላይ ምንም አይነት የጦርነት ዘገባ
አላስተናግድም!!!

Please wait, video is loading...

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "በግሌ በለውም በሎምም አልልም! ሺ ሚሊዮን አይነት ስም ስጠው የእርስበርስ ጦርነት ነው! መፍትሄው ሲመርህ ሲጎፈንንህ ይክረም እንጂ ድርድር ብቻ ነው!" ዮሴፍ የየሱስወርቅ

Post by sarcasm » 07 Jan 2022, 20:44

ምድረ አሽቃባጮች ለምን ስብሃት ተፈታ እያሉ ነው!!
ጃዋር መፈታቱንም እኮ ያውቃሉ! ችግራቸው ከፈፀሙት ወንጀል ሳይሆንከዘራቸው ነው!
Please wait, video is loading...

Post Reply