Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 3057
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

ኮ/ል ኢያሱ መንገሻ “የመለስ ዜናዊ እና የህወሓት የትግል ጉዞ” ፀሓፊ ስለ ተከዜ ስለ ትግራይና ወልቃይት ምን እያሉን ነው?

Post by Meleket » 27 Nov 2021, 03:59

ኮ/ል ኢያሱ መንገሻ “የመለስ ዜናዊ እና የህወሓት የትግል ጉዞ” ፀሓፊ ስለ ተከዜ ስለ ትግራይና ወልቃይት ምን እያሉን ነው?

ኮ/ል ኢያሱ መንገሻ “የመለስ ዜናዊ እና የህወሓት የትግል ጉዞ” የሚል መጸሐፍ አዲስ አበባ ውስጥ በመጋቢት 2002 ዓ.ም ለንባብ አብቅተው ነበር። ኮለኔሉ ህወሓትን ኣብጠርጥሬ አውቃታለሁ፡ ለህሊናዬና ለእምነቴ ብቻ ነው የምገዛዉ፡ ከፊቴም ሆነ ከጀርባዬ ሰው እንዲኖር አልሻም፡ የኔ መነሻና ጉዳይ ከታሪክ ጋር እንጂ ከሰዎች ጋር አይደለም፡ ታሪካችንን በትክክልና በነበረው መንገድ መግለፅ መቻል አለብን ብዬ አምናለሁ፡ ወዘተ ባዪ ናቸው። በመጸሐፋቸው ምዕራፍ ዘጠኝ፡ የተስፈኞች ተስፋና አልሞት ባይ ተጋድሎ በሚል ርእስ ስር የተረኩት ጉዳይ ስለ ተከዜ ስለ ትግራይና ወልቃይት አንዳች ፍንጭ የሚሰጥ ሆኖ አገኝተነዋል፡ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች። :mrgreen:

ኮለኔሉ እንዲህ ሲሉ ምን ማለታቸው ይመስላችኋል? :mrgreen:

ኮ/ል ኢያሱ መንገሻ “የመለስ ዜናዊ እና የህወሓት የትግል ጉዞ” ፀሓፊ wrote:የተስፈኞች ተስፋና አልሞት ባይ ተጋድሎ - ምዕራፍ ዘጠኝ”

“የመሳፍንቶች ኃይል እንደ ኣዲስ ተጠናክሮና ተደራጅቶ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ህብረት (ኢዲዩ) የሚል ስያሜን በመያዝ በመስከረም አጋማሽ 1969 ዓ.ም. ተከዜን ተሻግሮ ወደ ትግራይ መዝለቅ ወልቃይት በተባለ አካባቢ ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ መሰባሰብ አደረገ። . . .” ገጽ 132 [መለስ ዜናዊ እና የህወሓት የትግል ጉዞ - ፀሓፊ ኢያሱ መንገሻ (ኮ/ል) መጋቢት 2002 ዓ.ም. አዲስ አበባ]