Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12608
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

ሰበር ዜና : የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረማርያም በአሜሪካ ጥገኝነት ጠየቀ

Post by Thomas H » 26 Nov 2021, 09:31






Axumite
6h ·
ዋና ስራ አስፈፃሚው የሚመሩት ተቋም በደም ከጨቀየ በኋላ ኮበለሉ
---------------------------------------------------------------
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ተወልደ ገብረማርያም ወደ አሜሪካ ካቀኑ አንድ ወር ሆኗቸዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚው ከወር በፊት ለህክምና ብለው ከምክትሎቻቸው አንዱን ወክለው ወይም እንዲወከል ተደርጎ (የጉራጌ ብሄር ተወላጅ ነው) ወደ አሜሪካ ከሄዱ በኋላ እስካሁን እንዳልተመለሱ እና በዛዉ መኮብለላቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትግራይ ላይ ጠርነት ከታወጀ ጊዜ ጀምሮ በሲቪል አውሮፕላኖች ወታደሮች እና የጦር መሳሪያዎች በሀገር ውስጥ ሲያመላልስ እንደነበረ ይታወቃል። ከኤርትራም በተመሳሳይ ወታደሮችና የጦር መሳሪያዎች አምጥተዋል ወደዛም ኣጓጉዘዋል። በትግራይ ህዝብ ላይ ጆኖሳይድ የተፈጸመባቸው ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የተገዙት የጦር መሳሪያዎችም እንዳጓጓዘ የሚታወቅ ነው።
አቶ ተወልደ ገብረማርያም በትግራይ ህዝብ ላይ ጆኖሳይድ ላወጀ መንግስት የጦር መሳሪያና ወታደር አጓጓዥ ሆኖ እየሰራ ያለውን ግዙፍ ተቋም የመሩ ትግራዋይ ናቸው። እስከ ቅርብ ጊዜ በሃላፊነት እያሉ የአየር መንገዱ አውሮፕላኖች ሰራዊትና የጦር መሳሪያ እንዲያጓጉዙ ሲደረግ እሳቸው ፈቅደው ይሁን ተገድደው የታወቀ ነገር የለም። ምናልባት አሁን የሆነውን ነገር ሁሉ ለተጎጂው ህዝብ እና ለዓለም ማሕበረሰብ ይፋ ሊያደርጉ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።
እንደሳቸው ሁሉ በነ አብይ አሕመድ እና የአማራ ሊሂቃን የታቀደውን ጆኖሳይድ አውቀው ይሁን ሳያውቁ፣ አልያም ተገድደው ያስፈጸሙ የብልፅግና ፓርቲ ተጋሩ እና ሌሎች የትግራይ ተወላጅ ግለሰቦችም እንዳሉ ይታወቃል
ኣኽሱማይት ሚዲያ