Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Abere
Member
Posts: 3655
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ደሴ እና ኮምቦልቻ በቀለበት ውስጥ ናቸው። ወያኔዎች ሩጫቸውን ጨረሱ።

Post by Abere » 24 Nov 2021, 16:28

ደሴ እና ኮምቦልቻ በቀለበት ውስጥ ናቸው። ወያኔዎች ሩጫቸውን ጨረሱ። የእነ ደብረፅዮን ሞት ክፉኛ መደናገጥ መፍጠሩ የመንጋውን ወኔ አላሽቆታል። በተቃራኒው የዐብይ ኣአህመድ መዝመት በጎ አስተዋፆኦ አበርክቷል።

.....
በደሴ ውስጥና በደሴ ዙሪያ ሽምቅ ውጊያ እያደረጉ ካሉ የወሎ ፋኖዎችና ሚሊሺያዎች ጋር በመሆን ሙሉ ሙሉ ወያኔዎችን ከደሴና ከደሴ አካባቢ የመልቀም ስራ ይሰራል ተብሎም ነው የሚጠበቀው፡፡
3ኛ ወያኔዎችና ኦነጎች፣ የአፋር ግንባር ማዘዣቸውን በኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ባቲ አድርገው፣ ሚሌን ለመያዝ በካሳጊታና ቡርቃ በኩል ከ15 ቀናት በላይ፣ እጅግ በጣም ከፍተኛና በርካታ ዉጊያዎች አድርገዋል። በባቲ አካባቢ ያሉ ተራራማ አካባቢዎች ላይ ምሽጎች በመስራት፣ ከባባድ መሳሪያዎችን በመትከል፣ የከባድ መሳሪያዎች ድብደብ ሲያደርጉ ነበር።
ነገር ግን ከ15 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ከመገበር ውጭ ያገኙት አንዲት ነገር የለም። የትግራይ ሜዲያ ሃዉሶች፣ እነ ስታሊን ገብረስላሴ ሚሌ ገባን ብለው ሲቀደዱ የነበረ ቢሆንም፣ ሚሌ መድረስ አልቻሉም።
የወገን ጦር ማጥቃት እንዲጀመር ትእዛዝ ከተሰጠ በኋላ በመከላከል ላይ ያተኮረው የአፋር ጀግኖችና መከላከያን ያካተተው የወገን ጦር፣ በባቲ አካባቢ ያሉ ምሽጎችን በመደርመስ የወያኔ/ኦነግ የአፋር ግንባር ማዘዣ የነበረችውን የባቲ ከተማ ሊቆጣጠር ችሏል፡፡
ያ ብቻ አይደለም የወገን ጦር ገፍቶ በመሄድ በኮምቦቻልና ባቲ መካከል ፣ ከኮምቦልቻ የ30 ኪሎሜትር ወይንም 45 ርቀት ላይ ብቻ ያለችውን ገብራን ነጻ በማውጣት ወደ ኮምቦልቻ እየገሰገሰ ነው፡፡
4ኛ ሌላዋ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ከተማ፣ ከሚሴ በስሜን ሸዋ ግንባር የተሰማራው የኦነግና የሕወሃት ጦር ማዘዣ ከተማ ናት፡፡ የወገን ጦር በከሚሴና በኮምቦልቻ መካከል ያለችውን የሃርቡ ከተማን ቆርጦ በመቆጣጠር ከሚሴን ጨምሮ ወደ ሸዋ የተሰማራው የወያኔ/ኦነግ ጦር ሙሉ ለሙሉ እንዲቆረጥ አድርጓል። ከወሎ ወደ ስሜን ሸዋ የተሰማሩ የወያኔ ታጣቂዎች ከመሞት ወይንም እጅ ከመስጠት ውጭ ሌላ አማራጭ አይኖራቸውም።
ሃርቡ ከኮምቦቻል 22 ኪሎሚተር ወይም በ30 ደቂቃ ረቀት ላይ ያለች ከተማ ናት፡፡ የወገን ጦርም ከሃርቡ ወደ ኮምቦልቻ እየገሰገሰ ነው፡፡

Source:- Girma Kassa

Post Reply