Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
QB
Member
Posts: 1470
Joined: 05 Dec 2012, 15:14

ከትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ የተሰጠ መግለጫ ሕዳር 15, 2014 ዓ/ም

Post by QB » 24 Nov 2021, 14:57

ከትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ የተሰጠ መግለጫ
----
የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው የትግራይ ሰራዊት እያካሄደ ባለው ፍትሃዊ ትግል ወደ መጨረሻው ምእራፍ እየተዳረሰ ነው፡፡ መላው የትግራይ ህዝብ በአንድነት ሰምሮ ጠላቶቹን ለመደምሰስ እያደረገ ባለው ሁለንተናዊ ርብርብ ወደ ወሳኝ ምእራፍ እየተሸጋገረ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ስንዴ እና እንክርዳድን የሚለየው ህዝባዊው የትግራይ ሰራዊት እስከአሁን እያካሄደ ባለው ደምሳሽ ማጥቃት ፋሽስታዊ ስርአቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለመቅበር በሚቻልበት ወሳኝ የድል ምእራፍ እንገኛለን ብሏል፡፡

እየተካሄደ ባለው ውጤታማ ወታደራዊ ዘመቻዎች በሁሉም አካባቢዎች ሰላማዊ ህዝብ እንዳይጎዳ ሀብት ንብረት ጉዳት እንዳይደርስበት በተለይ ደግሞ የአማራና የአፋር ክልል ከተሞች የውጊያ ማእከል እንዳይሆኑ አስፈላጊ ጥንቃቄ እየተደረገ መምጣቱን ወታደራዊ ኮማንዱ አስታውቋል፡፡ በተግባርም ይህን እያረጋገጠ ያለው የአማራ እና የአፋር ህዝብም የሰራዊቱን ህዝባዊነት ምስክርነቱን ከመስጠት አልፎ ከሰራዊታችን ጎን ተሰልፎ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ትብበር እያደረገ ነው ብሏል፡፡

ቢሆንም ግን የሁሉም ህዝቦች ጠላት የሆነው የፋሽስቱ ስርአቱ ውጊያው በህዝቦች መካከል እንዲሆን እና በከተማ ውስጥ እንዲሆን እያጠረ ነው፡፡ በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ጥበብ በቁጥጥር ያዋልናቸው የአማራ እና የአፋር ከተሞችን በአየር እና በድሮን እየደበደበ ህዝብ እንዲያልቅ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ይህ ፀረ ህዝብ የፋሽስት ሰርአት እስትንፋሱ እስክትወጣ ድርስ ተመሳሳይ ተግባር ከመፈፀም ወደ ኃላ የሚል አይደለም ያለው የትግራይ ሰራዊት ወተሃደራዊ ኮምንድ መግለጫ በዚህ ምክንያት የሚደርስ በርካታ ጉዳት ለመቀነስ እና የስርአቱ እድሜ ለማሳጠር የትግራይ ሰራዊት ከፈተኛ ርበርብ በማድረግ ላይ ነው ብሏል፡፡

በአንጻሩ ደግሞ ስርአቱ እየፈረሰ ሲሄድ ስርአቱ አልበኝነት ሌብነት የህዝብ እና የመንግስት ንብረት መወረር እና ሌሎች ወንጀሎች ሊያጋጥም ይችላል ያለው መግለጫው በቅርቡ ጠላት የውጊያው ቀጠና እንድትሆን ያደረጋት የሽዋሮቢት ከተማ የትግራይ ሰራዊት በከፍተኛ ጥንቃቄ በቁጥጥሩ አውሎ ወደ ፊት በሚገሰግስበት ወቅት ይህን እንደ እድል ተጠቅመው በተደራጀ መልክ የግለሰብ ሀብት ንብረት ሳይቀር ሊዘረፍ ችሏል፡፡

አንድን ህዝብ ከሌላው ህዝብ በማጋጨት ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት የማይተኙ ሃይሎችም አልታጡም ያለው መግለጫው እንዲህ ያለ ተግባር በፍፁም ተቀባይነት የለውም ብሏል፡፡ በቀጣይም እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ጥፋት እንዳይፈፀም የሚካሄዱ ውግያዎች ከከተማ ውጭ ለማድረግ እና በህዝብ ላይ የሚደርስ ጉዳት ለመቀነስ አስፈላጊው ጥንቃቂና ጥረት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

ይሁን እና በትግራይ ሰራዊት ጥረት ብቻ ውጤታማ ማድረግ የሚቻል ባለመሆኑ ህዝቡ በየአካባቢው ተደራጅቶ ንብረቱንና ፀጥታውን ካልጠበቀ ውጤታማ ማድረግ አይቻልም ብሏል።
በተላይ የደብረብሃን በሎሌች ከተሞች ህዝብ በተደራጀ መንገድ ከተማችሁንና ድርጅታችሁን ልትጠብቁ ይገባል ያለው የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ፋብሪካዎች እና የንግድ ተቋማት ጉዳት እንዳይደርሰባቸው ሁሉም ኗሪ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል። የነዚህ ደርጅቶች ሰራተኞችና ጥበቃ አባላት ያላንዳች ስጋት ድርጅታችሁን በመጠበቅ ሃላፊነታችሁን ልትወጡ ይገባል ሲል የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ አሳስቧል።

ከዚህ በተጨማሪም በትግራይ መንግስት በኩል እንደተገለፀው በቀበሌ ፣ በወረዳ እና ማዛጋጃ ቤት ያላችሁ አመራሮች እየፈረሰ ያለው ስርዓት እግር በእግር ከምትከተሉ ተረጋግታችሁ ህዝባችሁን ልታገለግሉ እንዲሚገባ ወታደራዊ ኮማንዱ አስገንዝቧል። ህዝቡን አስተባብራችሁ የከተማው የእለት ተእለት እንቅስቃሴ እና ፀጥታ በማሰጠበቅ ሃላፊነታችሁን እንደትወጡ በድጋሚ አሳስቧል።

ይህ ፀረ ህዝብ የሆነ ሃይል አሉ በሚላቸው ጀነራሎቹ የተመራው መደበኛ ሰራዊቱ ሊያስቆመው ያልቻለውን ጦርነት እኔ ዘምቼ አስቆመዋለው በማለት ህዝብን በማደናገር ሲቪሉ የማህበረሰብ ክፍል ቢላ እና ገጀራ አስይዞ ለማዝመት እየጣረ ነው ያለው ወታደራዊ ኮማንዱ በሚቻለው ሁሉ የደብረብርሃን ከተማንና ሌሎች ከተሞችን የውጊያ ማእከል ለማድረግ እየጣረ ይገኛል ብሏል።

የሰላም አማራጭ ሙሉ በሙሉ ዝግ በማድረግ እስከ አዲሰ አበባ ለመዋጋት ምሽግ በመቆፈር ላይ የሚገኘው የፋሸሰቱ ቡድን እየቆፈረው ያለው ምሽግ ይዋጋበታል ወይንስ መቀበርያው ይሆናል የሚለው በቅርቡ የሚታይ ቢሆንም መላው የኢትዮጵያ ህዝብን ግን ይህን እኩይ እና የጥፋት ተግባሩ ይብቃህ ሊለው ይገባል ሲል የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ጥሪው አቅርበዋል።

የትግራይ ሰራዊት ወታሃደራዊ ኮማንድ
ትግራይ ትስዕር!
ሕዳር 15, 2014 ዓ/ም

https://www.facebook.com/tigrai.tv2/pos ... 2796236135

euroland
Member
Posts: 3378
Joined: 08 Jun 2018, 12:42

Re: ከትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ የተሰጠ መግለጫ ሕዳር 15, 2014 ዓ/ም

Post by euroland » 24 Nov 2021, 17:08

Ayte Junta
Did they give the announcement from the hell where they were sent the other day? :lol: :lol:
I am sure, now your beloved junta could set up a command center in hell.

QB wrote:
24 Nov 2021, 14:57

Post Reply