Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
netsi
Member
Posts: 135
Joined: 06 Oct 2019, 04:29

ሰበር ዜና፡ አሜሪካ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ላይ የጦር መሣሪያ ግዥ እገዳ ጣለች

Post by netsi » 02 Nov 2021, 10:51

ሰበር ዜና፡ አሜሪካ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ላይ የጦር መሣሪያ ግዥ እገዳ ጣለች
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ላይ የጦር መሳሪያ እና የጦር ቴክኖሎጂ ግዥ እገዳ መጣሉን የሐገሪቱ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ዲፓርትመንት አሳውቋል፡፡ እገዳው የተጣለው ከትግራይ ጦርነት ጋር በተገናኘ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ከጥቅምት 22 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ተወስኗል። የአሜሪካ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ዲፓርትመንት መረጃ እንደሚያመላክተው በኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሚገኙ እና ከጦርነቱ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት የሌላቸው በሥም ያልተጠቀሱ ኃይሎችም በእገዳው ተካተዋል ተብሏል፡፡
እገዳው ከማንኛውም የአሜሪካ ግዛት ውስጥ ከሚገኝ አምራች እና የንግድ ተቋም የጦር መሳሪያና የጦር ቴክኖሎጂ ግዥ እንዳይፈፅሙ የሚያዝ ነው፡፡

23/02/2014

ጠቃሚ የጤና መረጃ
የልብ ድካም መንስኤዎችና መከላከያ ወሳኝ መንገዶች። ለጥንቃቄ መታየት ያለበት። መፍትሄዉ በእጃችን ነዉ:: ለማየት ሊንኩን ወይም ምስሉን ይጫኑ