Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ከወሎ ደሴ እና ኮምቦልቻ በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ መንገደኞች ጣፎ ሲደርሱ በኦሮሚያ ክልልና በትራፊክ ፖሊሶች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረጉ።" የኛ ቴሌቪዥን

Post by sarcasm » 25 Oct 2021, 19:55

ከሰሜን እና ከደቡብ ወሎ ደሴ እና ኮምቦልቻ በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ መንገደኞች ጣፎ ሲደርሱ በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና በመንገድ ትራፊክ ፖሊሶች መንገደኖቹ ወደ መጡበት እንዲመለሱ መደረጉን መንገደኞቹ ለየኛ ቴሌቪዥን ተነግሩ።

ንገደኞችን የጫኑ አውቶብሶች እና ሚኒባሶች ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዐት ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ጣፎ ሲደርሱ በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና በመንገድ ትራፊክ ፖሊሶች እንዳያልፉ ተደርገው መንገድ ላይ ማደራቸውንም መንገደኞቹ ለየኛ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 13 /02/ 2014 ዓ/ም መንገደኞቹን የጫኑ ተሽከርካሪዎች በፖሊስ ታጅበው እስከ ሰንዳፋ ከተማ ድረስ ተሸኝተዋል።

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና የመንገድ ትራፊክ ፖሊሶች ሲጠየቁ ተፈናቃዮች ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንዳይገቡ የሚል ትዕዛዝ ደርሶን ነው የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ተናግረዋል።

የኛ ቴሌቪዥንም ይህንኑ ለማጣራት ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ደውለን ነበር የማውቀው ነገር የለኝም ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

ከመንገደኞቹ አብዛሀኛዎቹ ሕጻናት እና እናቶች መሆናቸውን ለየኛ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
Please wait, video is loading...

sun
Member+
Posts: 9312
Joined: 15 Sep 2013, 16:00

Re: "ከወሎ ደሴ እና ኮምቦልቻ በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ መንገደኞች ጣፎ ሲደርሱ በኦሮሚያ ክልልና በትራፊክ ፖሊሶች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረጉ።" የኛ ቴ

Post by sun » 25 Oct 2021, 20:49

sarcasm wrote:
25 Oct 2021, 19:55
ከሰሜን እና ከደቡብ ወሎ ደሴ እና ኮምቦልቻ በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ መንገደኞች ጣፎ ሲደርሱ በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና በመንገድ ትራፊክ ፖሊሶች መንገደኖቹ ወደ መጡበት እንዲመለሱ መደረጉን መንገደኞቹ ለየኛ ቴሌቪዥን ተነግሩ።

ንገደኞችን የጫኑ አውቶብሶች እና ሚኒባሶች ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዐት ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ጣፎ ሲደርሱ በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና በመንገድ ትራፊክ ፖሊሶች እንዳያልፉ ተደርገው መንገድ ላይ ማደራቸውንም መንገደኞቹ ለየኛ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 13 /02/ 2014 ዓ/ም መንገደኞቹን የጫኑ ተሽከርካሪዎች በፖሊስ ታጅበው እስከ ሰንዳፋ ከተማ ድረስ ተሸኝተዋል።

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ እና የመንገድ ትራፊክ ፖሊሶች ሲጠየቁ ተፈናቃዮች ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንዳይገቡ የሚል ትዕዛዝ ደርሶን ነው የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ተናግረዋል።

የኛ ቴሌቪዥንም ይህንኑ ለማጣራት ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ደውለን ነበር የማውቀው ነገር የለኝም ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

ከመንገደኞቹ አብዛሀኛዎቹ ሕጻናት እና እናቶች መሆናቸውን ለየኛ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
Please wait, video is loading...
Amara regional leaders said that these people should not vacate and leave their loved homes and homesteads for the tplf outlaws to takeover and populate it. So what is your complaint? That you couldn't empty these people from their homes and takeover their properties? It is more than right that they should not leave their homes but stay there and defend themselves with the support of the Federals and various militias. BINGO! :P

TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: "ከወሎ ደሴ እና ኮምቦልቻ በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ መንገደኞች ጣፎ ሲደርሱ በኦሮሚያ ክልልና በትራፊክ ፖሊሶች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረጉ።" የኛ ቴ

Post by TGAA » 25 Oct 2021, 21:27

የአዞ እንባህን ተወው ፤ ስንተዋወቅ አንተናነቅ ፡፡ መጀመርያ ጦርነት ላይ ሁሉንም ቦታ ለወያኔ የሚያስረክቡ የወያኔ ምርኮኛ የነበሩ ጀነራሎች ከቦታው ባይኖሩ ኖሮ ህጻናትና ሴቶች ንብረታቸውን ለቀው አይሰደዱም ነበር፤ ሁለተኛ ሀገራቸው ውስጥ ወደየትም መሄድ መብታቸው ነው ፤ የወገብ አጥንት ያለው ወታደር አስቁምና ፤ ህብረተሰቡን አስታጥቅና ከዚያ በኋላ ማንም ከቤቱ ጥሎ የሚሸሽ ስው አይኖርም ፤ ከህዝቡ በፊት ወታደሩ እየለቀቀ እየወጣ ፤ ህዝቡ በወያኔ እየተረሸነ ፤ አንተ እዚህ ትመጻደቃለህ" Amara regional leaders said that these people should not vacate and leave their loved homes and homesteads for the tplf outlaws to takeover and populate it" ስለዚህ ወያኔ ገድሉ በራሱ ወታደር መንደሩን ቢሞላው ነው የሚሻለው? መንግስት ማድረግ ያለበት ኮምፕ አዘጋጅቶ የልጆች እናት የሆኑትን እርዳታ ማቅረብ ፤ ወያኔን ጠራርጎ ካወጣ በኋላ ወደ ቤታቸው መመለስ፤ ነው :

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: "ከወሎ ደሴ እና ኮምቦልቻ በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ መንገደኞች ጣፎ ሲደርሱ በኦሮሚያ ክልልና በትራፊክ ፖሊሶች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረጉ።" የኛ ቴ

Post by sarcasm » 26 Oct 2021, 06:20

sun wrote:
25 Oct 2021, 20:49
Amara regional leaders said that these people should not vacate and leave their loved homes and homesteads for the tplf outlaws to takeover and populate it. So what is your complaint? That you couldn't empty these people from their homes and takeover their properties? It is more than right that they should not leave their homes but stay there and defend themselves with the support of the Federals and various militias. BINGO! :P
TDF is saying don't leave your homes. But turning back women and children running from conflict areas begging for a refuge is a new low.

በደሴና ኮምበልቻ ከተሞች የሚኖረው ህዝብ፤ የትግራይ ሰራዊት የህዝቡ ደህንነት እንደሚያሳስበው አውቆ፤ ከቤቱ እንዳይወጣና እንዳይፈናቀል፣ ንብረቱንም እራሱ እንዲጠበቅ ወታደራዊ ኮማንድ ያሳስባል

posting.php?mode=quote&f=2&p=1237552

የድል ዜና ከትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ

ጀግናው የትግራይ ሰራዊት ጠላት የጀመረው ማጥቃት በፀረ ማጥቃት በማክሸፍ፤ በፀይ መውጫ ዘመቻ የጀመረውን የማጥቃት ጀግንነት አጠናክሮ በመቀጠል፤ በደሴ ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኘውን ትልቅ ወታደራዊ ጥቅም ያለው የኩታበር ከተማና በርሜዳ እንዲሁም በረቲ፣ ዶሆይ፣ ዋኢማ፣ ተለያየን እና ተሪን የተባሉ ቁልፍ ወታደራዊ ቦታዎችን በመቆጣጠር፤ እዛ የነበረውን ሀይል በመደምሰስ፤ ጀግናው የትግራይ ሰራዊት አንፀባራቂ ድል ተቀዳጅቷል።

በዚህ ውጌያ የኦርሞ ተወላጅ የሆነው ኮ/ል እንዳለ ታደሰ የተባለው የ91ኛ ክፍለጦር ዋና አዛዥ ተማርኳል። ከዚህ በተጨማሪ የኮምበልቻ አየር ማረፊያ በቅርብ የመድፍ ርቀት የገባ በመሆኑ፤ የሲቪል አውሮፕላኖች በአየር ማረፊያው እንዳያርፉ እና እንዳይንቀሳቀሱ የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ በጥብቅ ያሳስባል!

ከዚህ በተጨማሪ በደሴና ኮምበልቻ ከተሞች የሚኖረው ህዝብ፤ የትግራይ ሰራዊት የህዝቡ ደህንነት እንደሚያሳስበው አውቆ፤ ከቤቱ እንዳይወጣና እንዳይፈናቀል፣ ንብረቱንም እራሱ እንዲጠበቅ የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ያሳስባል!

በዚህ ግምባር የሚገኙ የፋሽስቱ ወታደሮች፤ በግልም ይሁን በህብረት ለትግራይ ሰራዊት እጃቸውን እንዲሰጡ፤ አልያም ወደፈለጉት ቦታ በመሄድ፤ ህይወታቸውን እንድያድኑ የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ያሳስባል!

ትግራይ ታሸንፋለች !
የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ

https://www.facebook.com/kassa.hailemar ... 3885607884

Post Reply