Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30658
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ካረን ባስ የኢትዮጵያ ሕዝብ የመረጣት የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል ሳትሆን በኢትዮጵያ ጉዳይ የመወሰን መብት ማን ሰጣት? ይህ ቆሻሻ ኮሎኒያሊዝም የሚቆመው መቼ ነው?

Post by Horus » 25 Oct 2021, 12:32

በዚህ ዘመን የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ እንደነ ምኒልክ ማሰብ አቁመዋል። ምኒልክ በሕይወት ቢኖር ካረን ባስ የምትባል አሜሪካዊት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የማያውቃት፣ በኢትዮጵያ የማትኖር፣ የኢትዮጵያ ሰው ምሪ ብሎ ያልመረጣት፣ ያልሾማት የባዕድ ባይተዋር 10 ሺ ኪሎ ሜትር ርቃ ባለ በራሷ አገር ሆና፣ ኢትዮጵያዊያን ባልመረጡት፣ ባልወከሉት ድርጅት ውስጥ ቁጭ ብላ በኢትዮጵያ አገርና ሕዝብ ላይ ውሳኔ ሆነ ድንጋጌ ልታሳልፍ ከቶም ከቶም ጣይቱ አትፈቅድም ነበር ።

የዚህ ዘመን አበሻ ምነው ሸና፣ ምነው ደነቆረ፣ ምነው ቀልቡ፣ ምነነቱ፣ ማንነቱ ተሰለበ? መቼ ነው የኢትዮጵያ ፓርላማ ባሜሪካ ጉዳይ፣ ባሜሪካ ነገር፣ አሜሪካኖች ምን ማድረግ እንዳለባቸው፣ እንዴት መኖር፣ እንዴት መብላት፣ እንዴት መፍሳት እንዳለባቸው ህግና ውሳኔ አሳልፎ የሚያውቀው?

ታዲያ ለምንድን ነው ያሜርካ ፓርላማ ባልመረጠውና በማያውቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የቅኝ አገዛዝ ሕግና ውሳኔ ሲጭን አበሻ ሁሉ እንደ ባሪያና ቅኝ ተገዥ አንድ እጅግ ቀላልና ለህጻን የሚገባ ጥያቄ የማይጠይቀው? ይህም ጥያቄ ያሜሪካ ፓርላማ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የመወሰን መብት ማን ሰጠው? እንደዚህ ያለ ታሪካዊ ድፍረት በኢትዮጵያ ሉአላዊነት ላይ ሲፈጸምስ ያበሻ ልጅ ምነው እንደ ባሪያና ቅኝ ተገዥ አሺ አው ብሎ መቀበል ለመደ?

በእውነት ዛሬ ምኒልክና ጣይቱ የኢትዮጵያ መሪ ቢሆኑ ይህን ድፍረት በዝምታ ያዩት ነበርን? ስለሆነም መቼ ነው የኢትዮጵያ ልሂቅ ነኝ ባልይ የከሸፈ ክብሩ የተቀማ ባዶ የማያስብ ቅኝ ተገዥ ባሪያነቱን አምኖ ከንቅልፉ የሚነቃው? ወደ ማንነቱ የሚመለሰው? መቼ ነው?

ያሳዝናል! ያሳፍራል! አንድ መስመር ቃል ካረን ባስን በኛ ላይ የመወሰን መብት የለሽም! የኢትዮጵያ ፓራላማ ተመራጭ አይደለሽም የሚላት አበሻ እንዴት ይጠፋል?



Post Reply