Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

በደሴና ኮምበልቻ ከተሞች የሚኖረው ህዝብ፤ የትግራይ ሰራዊት የህዝቡ ደህንነት እንደሚያሳስበው አውቆ፤ ከቤቱ እንዳይወጣና እንዳይፈናቀል፣ ንብረቱንም እራሱ እንዲጠበቅ ወታደራዊ ኮማንድ ያሳስባል

Post by sarcasm » 25 Oct 2021, 07:55

የድል ዜና ከትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ

ጀግናው የትግራይ ሰራዊት ጠላት የጀመረው ማጥቃት በፀረ ማጥቃት በማክሸፍ፤ በፀይ መውጫ ዘመቻ የጀመረውን የማጥቃት ጀግንነት አጠናክሮ በመቀጠል፤ በደሴ ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኘውን ትልቅ ወታደራዊ ጥቅም ያለው የኩታበር ከተማና በርሜዳ እንዲሁም በረቲ፣ ዶሆይ፣ ዋኢማ፣ ተለያየን እና ተሪን የተባሉ ቁልፍ ወታደራዊ ቦታዎችን በመቆጣጠር፤ እዛ የነበረውን ሀይል በመደምሰስ፤ ጀግናው የትግራይ ሰራዊት አንፀባራቂ ድል ተቀዳጅቷል።

በዚህ ውጌያ የኦርሞ ተወላጅ የሆነው ኮ/ል እንዳለ ታደሰ የተባለው የ91ኛ ክፍለጦር ዋና አዛዥ ተማርኳል። ከዚህ በተጨማሪ የኮምበልቻ አየር ማረፊያ በቅርብ የመድፍ ርቀት የገባ በመሆኑ፤ የሲቪል አውሮፕላኖች በአየር ማረፊያው እንዳያርፉ እና እንዳይንቀሳቀሱ የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ በጥብቅ ያሳስባል!

ከዚህ በተጨማሪ በደሴና ኮምበልቻ ከተሞች የሚኖረው ህዝብ፤ የትግራይ ሰራዊት የህዝቡ ደህንነት እንደሚያሳስበው አውቆ፤ ከቤቱ እንዳይወጣና እንዳይፈናቀል፣ ንብረቱንም እራሱ እንዲጠበቅ የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ያሳስባል!

በዚህ ግምባር የሚገኙ የፋሽስቱ ወታደሮች፤ በግልም ይሁን በህብረት ለትግራይ ሰራዊት እጃቸውን እንዲሰጡ፤ አልያም ወደፈለጉት ቦታ በመሄድ፤ ህይወታቸውን እንድያድኑ የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ ያሳስባል!

ትግራይ ታሸንፋለች !
የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ

https://www.facebook.com/kassa.hailemar ... 3885607884